ሰበር ዜና – ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ወንድሙ ላይ የተላለፈውን እግድ አጸና!

 • ውሳኔው የአጥማቂ ነኝ ባዩን ሥርዐተ አልበኝነት ሲቃወሙና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር ሲጋደሉ ለቆዩት የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ታላቅ ድል ነው፡፡
 • ሰንበት ት/ቤቱ እና ምእመናኑ የውሳኔውን አፈጻጸም በቀጣይነትና በጋራ ሊከታተሉ ይገባል
 • ሕገ ወጥ ሰባክያንና አጥማቂ ነን ባዮች ችግር የሚፈጥሩባቸው ሌሎች አጥቢያዎችስ ከዚህ ምን ይማራሉ?BeteKihnet banned Girma

የልዑል እግዚአብሔር ቸርነትና አዳኝነት ከሚገለጥባቸው ምክንያቶች ወይም መንገዶች አንዱ ጠበል ነው፡፡ በገዳማትና አድባራት ቅጽር፣ በቅጽሩ ዙርያና በአካባቢው ሰበካዎች ባሉ የጠበል ቦታዎች በፍጹም እምነት የሚቀርቡ ምእመናን በጠበል እየተጠመቁ ፈውስ ያገኛሉ፤ የእግዚአብሔር ደገኛ ተኣምራት እየተገለጸ ምሕረቱ የተደረገላቸው ሁሉ በየጊዜው ድንቅ ሥራውን እየመሰከሩ ይገኛሉ፡፡

በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ማጥመቅ የሚችለው የቅስና ሥልጣነ ክህነት ያለው አባት ብቻ ነው፡፡ ቅስና የሌለው ሰው አያጠምቅም፤ አይናዝዝም፤ አይባርክም /ፍት.ነ.ፍ.መ.አን.3 ቁ.21/ ቅዱሱን ቅባት መቀባት የሚችለው የክህነት ሥልጣን ያለው ብቻ ነው፡፡ /ያዕ.5÷14/ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በገንዘብ አይሸጥምና አጥማቂው ካህን መማለጃ መቀበል አይገባውም፡፡ /ፍ.ነ.ፍ.መ.አን.7/

በምሥራቅ አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የፈውስ ጸጋ አለኝ›› የሚለው ‹መምህር› ግርማ ወንድሙ፣ ‹‹ለደብሩ ልማት ገንዘብ ለማሰባሰብ›› በሚል ከአንዳንድ የደብሩ አስተዳደር አባላት ጋራ በጥቅም በመተሳሰር ሲያካሂድ የቆየው ‹‹የጠበል አገልግሎት›› ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚፃረር የግል ጥቅም ማካበቻ ነበር፡፡

የ‹‹መምህር›› ግርማን ሕገ ወጥነት ለማጋለጥ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር የተለያዩ ጥናቶችን ሲያደርግ የቆየው የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ያሰራጨው መረጃ እንደሚጠቁመው አጥማቂ ነኝ ባዩ ‹‹መምህር›› ግርማ:-

 • የቅስና ሥልጣነ ክህነት አልነበረውም /በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ፊት ቀርቦ ሲጠየቅ አለኝ የሚለው ከዲቁና ያለፈ አይደለም፤ እርሱም ቢኾን ሳይገባው ያገኘው ነው/፡፡
 • ከቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ውጭ በዓለም ፋብሪካ የተመረተ ለፀጉር ድርቀት መከላከያ የኾነውን የወይራ ዘይት ‹‹ቅባ ቅዱስ ነው›› በማለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዐጸ ውስጥ በማከፋፈልና በመሸጥ ቤተ ክርስቲያንን የንግድ ማእከል አድርጓታል፡፡
 • ለ‹‹መምህር›› ግርማ ፈውስ ሁሉ የሚከናወነው በጩኸት ነው፡፡ ጩኸት ከሌለ ፈውስ የለም ብሎ ያምናል፡፡ አጋንንት ያልጮኸለት ሰው ገና የፈውሱ ጊዜ እንዳልደረሰና በእርሱ ላይ ርኩስ መንፈስ እንዳለበት፣ እንዲገለጥና እንዲወጣለት ራሱን በራሱ በመቁጠሪያ እንዲደበድብ ይነግረዋል፤ ‹ትምህርት› ይሰጠዋል፡፡ አካል ጉዳተኛው ሁሉ አጋንንት እንደያዘው ሰው እንዲጮኸ ይደረጋል፡፡ ግርማ÷ ደዌ ዘዕሴት፣ ደዌ ዘአኮቴት፣ ደዌ ዘኀጢአት ለግንዛቤ ያህል እንኳ በውል ለይቶ አያውቃቸውም፡፡ ሕሙማን ከተፈወሱ በኋላ ደዌያት በኃጢአታቸው ምክንያት ብቻ እንደሚመጡ እንደ ምክር ይነግራቸዋል፤ እንዲህም እንዲያምኑ ይገደዳሉ፡፡
 • በተለያየ በሽታ ተይዘው መዳንን ሽተው የሚመጡ ሕሙማን ኃጢአታቸውን በዐደባባይ እንዲናዘዙ ያደርጋል፡፡ የብዙ ሕዝበ ክርስቲያንን ገመናና ኃጢአት ሕሙማኑ ዐውቀውም ይኹን ሳያውቁ ገቢ ማስገኛ እንዲኾን በቪዲዮ አስቀርጾ በቪሲዲ ለገበያ አውሎታል፡፡ አስገራሚው ነገር ‹‹ትዕይንቱን›› በቪዲዮ መቅረጽ የሚችለው እርሱ ያቋቋመው የግል ስቱዲዮ ብቻ ነው፡፡
 • ‹‹ጠበል ብቻውን መጠመቅ ዋጋ የለውም፤ በመቁጠሪያ ራሳችኹን ካልደበደባችኹ›› በማለት ምእመኑ ‹‹ቅባቅዱስ ነው›› ብሎ ከሚሸጠው የፋብሪካ ወይራ ዘይት በተጨማሪ መቁጠሪያ እንዲገዛ ያስገድዳል፡፡ እርሱ ከሚሸጠው መቁጠሪያ ውጭ ሌላው ዋጋ እንደሌለው ይሰብካል፡፡
 • የመዳን ተስፋ ይዘው ከየአህጉረ ስብከቱ የሚመጡ ምእመናን መጠለያ አጥተው በመጉላላታቸው ለተጨማሪ በሽታ የተጋለጡ፣ በመቁጠርያ በመደብደባቸውና የወይራ ዘይት ጠጡ እየተባሉ በመገደዳቸው ለኅልፈት የተዳረጉ ሕሙማን አሉ፡፡
 • መኖርያ ቤቱ ሀብተ ፈውስ እንዳላቸው ደገኛ አባቶች በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ተወስኖ ሳይሆን በ1.5 ሚልዮን ብር ወጪ የተገነባ ነው፡፡
 • ግርማ ሰይጣንን አስወጣለኹ ከሚልበት የ‹‹ፈውስ መንገድ›› አንዱ በፕሮቴስታንታዊ ዘይቤ ሕሙማንን በቦክስ እና በጥፊ እየተማታ ነው፡፡ የማጥመቁ መርሐ ግብር ሲጀመርም ኾነ ሲያበቃ በጸሎት ፈቃደ እግዚአብሔር ተጠይቆበት አያውቅም፡፡ አባቶቻችን ሲያጠምቁ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ በቃለ እግዚአብሔር አጋንትን በማቃጠል፣ በቅዱስ መስቀል በመዳሰስ፣ ጠበል በመርጨት ዳግመኛ ወደ ሕሙሙ እንዳይደርስ በማድረግ ነው፡፡ /ሉቃ.8÷26-33፤ 2ነገ.5÷8-19፤ 1.ቆሮ.1÷18/
 • ‹‹እኛ የምንጨነቀው ሰውን ለማዳን እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዐት አይደለም፤›› በማለት በሰንበት ቀን ስግደት ያዛል፤ በቤት መቅደስ ሥርዐተ ጸሎት እየተካሄደ /ቅዳሴ እየተቀደሰ፣ ማሕሌት እየተቆመ፣ የደብሩ ክብረ በዓል እየተደረገ/ እርሱ ሌላ መርሐ ግብር ያካሂዳል፤ ይጮኻል፤ እልል እንዲባል ያደርጋል፡፡
 • በማጥመቅ ወቅት÷ ‹‹ርኵስ መንፈስ ያደረባችኹ እገሌ ወይም እገሊት መተት አድርጋባችኹ ነው፤ በእገሌ ወይም እገሊት ዐይነ ጥላ ተደርጐባችኹ ነው፤ በእገሌ ወይም እገሊት አስማት ተደርጐባችኹ ነው›› እየተባለ ምእመናን ከብዙ ጊዜ ዘመዶቻቸው፣ ባልንጀሮቻቸው፣ ጎረቤቶቻቸው እንዲጣሉ፣ ቤት እንዲለቁ፣ ሥራና ትምህርታቸውን እንዲያቆሙ ተደርጓል፤ ሕጋዊ ባለትዳሮች ጋብቻቸው ፈርሶ ተለያይተዋል፤ ከፍተኛ ማኅበራዊ ቀውስ ፈጥሯል፡፡
 • በተሰጠው ጸጋ፣ እግዚአብሔርን ማክበር ሲገባው ‹‹እኔ እንደዚህ ነኝ›› በማለት ያወራል፡፡ በየመድረኩ የሚያስተምሩም ኾነ አጋንንት ያደረባቸው ሕሙማን እንዲመሰክሩለት ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ የእግዚአብሔር ክብር ከሚወራ ይልቅ አለኝ የሚለው ቅድስና እንዲለፈፍለት ያደርጋል፤ ራሱም ስለራሱ ይናገራል፡፡
 • በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ማንም ሰው በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ለግል ጥቅም የሚውል ምንም ዐይነት ንግድ ማካሄድ የለበትም፡፡ ‹‹መምህር›› ነኝ ባዩ ግርማ ግን በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ለራሱ ገቢ ማስገኛ የሚውሉ ሌሎች ንግዶችን ይነግዳል፡፡ በዚህም በአንድ ቀን ብቻ ከብር 25,000 – 28,000 ገቢ ይሰበስባል::
 • ከንግዱ ባሻገር ከጠበል አገልግሎት የሚገኘውና በስእለት፣ በስጦታ የሚሰበሰበው ገንዘብ በአግባቡ ለቤተ ክርስቲያን ገቢ መኾን ሲገባው ለአጥማቂ ነኝ ባዩ በፐርሰንት የሚሰጥበት አሠራር አስተክሏል፡፡
 • ግለሰቡ ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በሚፈጽማቸው በእኒህና በመሳሰሉት ሕገ ወጥ ተግባራት ከእርሱ ጋራ የጥቅም  ግንኙነት ካላቸው አንዳንድ የሰበካ ጉባኤ አበላት በቀር /በወር 8000 ብር እጅ መንሻ የሚታሰብላቸው እንዳሉ ይነገራል/ ስንኳን የደብሩን የልማት ጥረት በገቢ ሊደግፍ ማኅበረ ካህናቱን የሥራ ዋስትና በማሳጣት ስጋ ለመከፋፈል ሞክሯል፡፡
 • በደብሩ ሰንበት ት/ቤት የሚካሄደው ተከታታይ ትምህርት አጥማቂ ነኝ ባዩ በሚፈጥረው መሰናክል ምክንያት እየተቋረጠ ወጣቶች የመበተን ስጋት ውስጥ ገብተዋል፡፡
 • የደብሩ አስተዳደር በዚህ ጉዳይ ላይ የሚመጡ ማንኛውንም ጥያቄዎች አላስተናግድም በማለት በሩን ዘግቶ ቆይቷል፡፡ በምትኩ በሰ/ት/ቤቱ አባላት ጥረት በብዙ ልመና እንዲያናግሩ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ቢጠየቁም አሁንም እንደተለመደው ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋል – ጥበቃ በመጥራት፣ ከቢሮ በግዳጅ ለማስወጣት በመሞከርና ለፖሊስ እንደውላለኹ ብለው በማስፈራራት፡፡ በመጨረሻም ይለይላችኹ በማለት ‹‹ምንም የገቢ ምንጭ ስለሌለን አጥማቂውን ከነሕጸጻቸው እንቀበላቸዋለን›› በማለት በድፍረት አሳውቋል፡፡ ከደብሩ ሰ/ት/ቤት ተወክለው ያነጋገሯቸውን የሰ/ት/ቤቱን አባላት÷ ‹‹ጋጠ ወጦች፣ ዐላዋቂዎች፣ የቤተ ክርስቲያኑን ዕድሳት የምታስተጓጉሉ›› በሚሉ ዘለፋዎች ከሰበካ ጉባኤው አባላት ጋራ መልካም ግንኙነት እንዳይኖራቸው ተደርጓል፡፡
 • ከ‹‹ማጥመቅ›› አገልግሎቱ በኋላ በጎ ፈቃደኞች ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑን ሲያጸዱ የሚታየው የንጽሕና ጉድለት አስከፊ ነው፡፡ የደብሩ መጸዳጃ ቤት ከብልሽት አልፎ ለቤተ ልሔሙ አገልግሎት ዕንቅፋት ቢኾንም ይህ ‹‹መምህር›› ግርማን ጨርሶ አይገደውም፡፡
 • ሰንበት ት/ቤቱ ከላይ የተገለጹትንና ከደብሩና ሌሎች ስፍራዎች በቪዲዮ እና በድምፅ እንዲሁም በጽሑፍ የተገኙ መረጃዎችን በመያዝ ሙሉ ማስረጃውን ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ካቀረበና በጉዳዩ ላይ ከደብሩ አስተዳደር ክፍሎችና ከሰ/ት/ቤቱ አባላት ጋራ ለሰዓታት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት ‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙን በሰኔ ወር፣ 2003 ዓ.ም ጠርቶ ካነጋገረው በኋላ፣ ከዲቁና ያለፈ ክህነት ሳይኖረው የፈጸመው ተግባር ከፍተኛ ድፍረት የተመላበት ስለኾነ የማጥመቅ ሥራው በአስቸኳይ እንዲቋረጥ እንዲደረግና አፈጻጸሙ እንዲገለጽለት በቁጥር 4290/90/03 በቀን 8/10/2003 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ የደብሩን አስተዳደር አዝዞ ነበር፡
 • በትእዛዙ መሠረት የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ‹‹መምህር›› ግርማ ወንድሙ ከሕገ ወጥ ተግባሩ እንዲገታ በደብዳቤ ቢያሳውቀውም ውሳኔው በሙስና /የጥቅም ትስስር/ ተፈጻሚ ባለመኾኑ አገረ ስብከቱ ለአዲስ አበባ ከተማ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፣ ለደምበል ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ እና ለፌዴራል ፖሊስ በጻፋቸው ደብዳቤዎች ለማሳወቅ ተገዶ ነበር፡፡
 • እነኾ ዛሬ የሰንበት ት/ቤቱ፣ የሌሎች አገልጋዮችና ቀናዒ ምእመናን ጥረት ሠምሮ ደብሩ በቁጥር 339/ቀ/አ/ቤ/ክ በ28/8/2005 ዓ.ም በግርማ ወንድሙ ላይ በድጋሚ ያስተላለፈው እገዳ በመንበረ ፓትርያሪኩ የበላይ ውሳኔ ሊጸና ችሏል፡፡ አፈጻጸሙን ሁሉም አካላት በመተባበር ሊከታተሉት ይገባል፡፡ በሀገር ውስጥ ይኹን በውጭ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ሌሎች አጥቢያዎችም የሕገ ወጥ አጥማቂዎችንና ሰባክያንን ስምሪት በማጋለጥና በመግታት ረገድ ከደብሩ ሰንበት ት/ቤትና ምእመናን ሊማሩ ያስፈልጋል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን                  ቁጥር፡-9474/756/2005 ዓ.ም

መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት                                     ቀን፡- 8/9/2005 ዓ.ም

 

ለደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ ሰ/ጉ/ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

 

ጉዳዩ፡- በአስቸኳይ አጥማቂ መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ጉ/ጽ/ቤት በቁጥር 339/ቀ/አ/ቤ/ክ በ28/8/2005 ዓ.ም የተሰጠው እገዳ መ/ፓ/ጠ/ጽ/ቤት ያጸናው ስለመኾኑ ይመለከታል፤

መ/ር ግርማ ወንድሙ ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት በሕገ ወጥ መንገድ እስከ አሁን ድረስ በደብሩ እያጠመቁ ይገኛሉ፡፡

ይኹንና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከ1993 ዓ.ም እስከ 2002 ዓ.ም ድረስ በየወቅቱ በሕገ ወጥ መንገድ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት ሕዝበ ክርስቲያኑን በየደብሩ ቅጽር ግቢ በማሰባሰብ የሚያጠምቁትን በተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

 1. ከቤተ ክርስቲያኗ ቀኖና ሥርዐት ውጭ በሚፈጸም ስብከትና ጥምቀት
 2. የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሳይፈቅዱ የሚሰጥ የወንጌልና ጥምቀት አገልግሎት መስጠትን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነ ቢኾንም በሥርዐተ አልበኝነት በተለያዩ ቦታዎች የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሲጣስ ይታያል፡፡

በመኾኑም መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚፈጽሙት ሕገ ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና የወንጌል አገልግሎት መኾኑን እየገለጽን የእምነታችን ተከታይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከዚህ እግድ ጋራ በተያያዘ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥመው የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ እያሳሰብን የሚመለከታቸው የመንግሥት የጸጥታ አካላትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

ግልባጭ

 • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
 • ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ ልዩ ጽ/ቤት
 • ለአስተዳደር መምሪያ
 • ለሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
 • ለምሥራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
 • ለፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት
 • ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን
 • ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት
 • ለአ/አ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
 • ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ
 • ለአ/አ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮ
 • ለቂርቆስ ክ/ከ ፍት ጽ/ቤት

         አዲስ አበባ

 

የደብሩ አስተዳደር በ‹‹መምህር›› ግርማ ላይ የጻፈው ደብዳቤ

ni

Advertisements

166 thoughts on “ሰበር ዜና – ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ወንድሙ ላይ የተላለፈውን እግድ አጸና!

 1. ብልሐይ ኣምላኸይ October 31, 2015 at 11:52 am Reply

  ኣተ ራስህ ማነህ በስመ ቤተክርስትያን ሰው ምዘነጥል
  ኣነጋገርህ ስርኣት የሌለው ጋጠወጥ ነገር ነህ

  • Anonymous November 5, 2015 at 8:15 pm Reply

   ይህ ሁሉ ነገር የተደረገው እና እገዳ የተሰጠው ቀኑን የሚየመለክተን ከ 7 ኣመት በፊት ነው ።7 ኣመት ሙሉ እንዲህ ታግደው እያለ እንዴት ሊፈውሱ ቻሉ ????
   ነው ኣሁን ነው ሃሳቡን የመጣላቹ ኣትፍረድ ይፈረድብሃል ይላል ወንጔሉ
   ለእርስዎም ለ ኣንተም ጌታ ኤልሻዳይ ኣለና ዝዝዝምምምምን እስቲ እንበል ምንም ሳንነካ ኣንለፍልፍ ለምንድነው ሳያሳክክችሁ ምታኩት ኣላርፍ ያለ ጣት እየዘባረቃቹ ፃፉ ይህን ከማረግ ግን የጠፋው ትውልድ መመለስ ነበረባቹ

 2. tigist October 31, 2015 at 1:36 pm Reply

  manm bemanm hasyat bayferd teru new egzabhr. sayfkd manm awede mhrtu.lay komo mnager madanm aychlm enante manachu megmrya ye bete khnte sew admga,
  zerga, poltkga selhone amsmam

 3. Anonymous November 1, 2015 at 11:31 pm Reply

  ወሬ ብቻ

 4. Anonymous November 2, 2015 at 12:32 pm Reply

  የዘንዶው ልጆች።

 5. senu November 3, 2015 at 10:08 pm Reply

  Hara !!

  ante metetegna Debtera ,, werada !!!be Awde Negest eyedegemk new Qes or deyaqon-

  yetebalkew !!

  Long live Memher Girma Abatachin !!!!

 6. senu November 3, 2015 at 10:11 pm Reply

  werada Debtera!!! metetegna ante neh Miqegna !!

 7. Anonymous November 4, 2015 at 5:46 am Reply

  ለ MELAKE MENKIRAT GIRMA WONDIMU ተቃዋሚዎች በሙሉ OR ለሃራጥቃዎች
  እናንተ ማናችሁ????
  እናንተ ማን ናችሁ ክስ የመሰረታችሁ
  በመምህርራችን ላይ ጣት የቀስራችሁ
  ግርማን አታቁትም ብላችሁ አላችሁ
  አይ እና የተርገማችሁ አይ ማፀየፍችሁ
  ክብር ማሳጣት ነው መስሎ የታያያችሁ
  የትኛው መጽሐፉ ነው አዋርዱ ያላችሁ
  ውደ አባታችንን ልክ እንደይሁዳ አሳልፋችሁ ስጣችሁ
  እር ለመሆኑ እናተ እናማንችሁ
  እኛስ አወቅናችሁ በደም ግባታቹ
  ቃሉም እንደሚለው ከአለም ስለሆናችሁ
  ፉከራዋ ሽለላው ነበር ከሃላችሁ
  ሳምንታት ወርትን ቀን እየቆጠራችሁ
  እንደምትውልድ ሴት ዛሬ ነገ ነው ብላችሁ
  አላችሁ ደጉ አባታችንን ለስር ዳርጋችሁ
  ጠንቋይ ነው መተት ነው ብላችሁ አላችሁ
  የመምህራን ስም የመድርክ ሟሟቌ መክፍቻ አድርጋችሁ
  እውነትን ሳትይዙ በወሬ አለቃችሁ
  የምን ሽሽት የምን መደበቅ ነው
  እውነትን መናገር የክርስቲያን ደንብ ነው
  ውጡ ተናገሩ እውነት ነው ቃላችሁ
  ማተብ ካስራችሁ ከርስቲያን ካልልችሁ
  ብላችሁ አታውሩ ከደሙ ንጹህ ነኝ እንደ ቢላጧስ
  ፃድቁን አስራችሁ ደንብና ስራትን ህግን በመጣስ
  ይዛችሁልና በቀኝ እጅ መስራያ በግራ እጅ መጽሐፍ ቅዱስ
  በስጋ የሞተች አይ ይች ነብስ
  አረ ለመሆኑ እናተ ማናችሁ
  በመምህር ግርማ ጣት የቀስራችሁ
  ችግር ካለባችሁ እርዳታ ጠይቁ በመምህር ፀበል ኑና ተጠመቁ
  ትቦ ነው ውሀ ነው ቧንቧ ነው እያላችሁ ብላችሁአትልቀቁ
  ቃል የሚላችሁን ጠንቅቃችሁ እወቁ
  በርትታችሁ ቁም በሀይማኖት ንቁ
  ቃሉ እንድህ ነው የሚለው ውሀውን በስሜ ባርካችሁ አጥምቁ
  ይህን ነው ያረጉት መላክ መንክራት የኛ አባት ፃደቁ
  ነገር ግን እርሳችው በፍርድ ቤት ቆሙ
  እንደ ወንጀለኛ ስው ስላጠመቁ
  ቃሉ እንዲህ ይላል ልባችሁ ለምንድን በውሸት ይታበላል
  ከመሬት ተንስቶ በሬ ወለደ ይላል
  ክፍ ዘመን እና ክፍ ቀን ከመጣ እረ ምን ይባላል
  መላክ መንክራት ታላቅ አባት
  ፈውሳችው ቀጥሏል በማርፏ ቤት
  አጋንት በማስር ደሞም በማውጣት ስለታችው ደርሷ በእስር ቤት ያሉት
  የእስር ቤት ሰንሰለት ብረቱ ተፍታ
  በመንክራት ፀሎት በቃሉ በጌታ
  ሁሉንም ስምተናል ከአለም እንዳልሆነ
  ምንም አያስፈራም ከጌታ ካልሆነ
  እናንተ ማናችሁ????
  እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤ 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1-19
  የአፄ ሚኒልክ ልጅ —-ልጅ ሸዋረጋ
  የሸዋረጋ ልጅ ——– ልጅ ኢያሱ
  የኢያሱ ልጅ ——— ልጅ አለምፀሀይ
  የአለምፀሀይ ልጅ —-ልጅ አለምሰገድ
  የአለምሰገድልጅ ——ይህንን ግጥም የፃፈችልን እህታችን ፡ልጅ ሰብለወንጌል በእግዚያብሔር ስም እናመሰግናለን
  COPY PAST ማድረግ አይቻልም
  ግን SHARE ማድረግ ይቻላል

  • Anonymous November 5, 2015 at 2:34 pm Reply

   Yamral sebli…..God bless u

 8. Weditu Ethiopia November 4, 2015 at 6:01 am Reply

  አዎ በዘመናችን ያየነውን በሚሊዬኖች አንመሰክራለን!!!
  ለመላአከ መንከራት ግርማ ወንድሙ፣

  በደዌ ለተቸገረ ማንኛውም አትዩጰያዊ በእግዚአብሔር ሀይል በነፃ መዳን እነደሚቻል ና ትውልዱም ለወገኑ እና
  ለሀገሩ ቀና እንዲሆን አስተምረው ያስመሰከሩ ናቸው። ለአሰተዋለ ስው ሁሉ የዘመናችን የሠላም ሐዋሪያ ናቸው፣ እንጂ በምንም መለክያ መታሰር አይገባቸውም። አዎ ግን ሁሌ እናምናለን እግዚአብሔር ምክንያት አለው፣ የእውነት አምላክ፣ ፈራጅ አለ መድሃኒት አለም ክርስቶስ፣ የድንግል ማርያም ልጅ ክብር ለእርሱ ይሁን ሁሌ ያያል ፣አይተቸኛም ፣አያንቀለፈም። እኛ ግን ለአንድ ሴኮንድ በራሳችን መተንፈስ የማንችል ሰዎች ለፍርድ እንቸኩላለን። እግዚአብሔር ስራው ረቂቅ እና ድንቅ ነው። በቤተ ክርስቲያናችን ስርአት፣ በክርስቶስ ደም ላይ ቆመናል ፣ ያውም በዘመናችን በቀጭኑ እና ቀጥተኛ የተዋህዶ ጉዞ ላይ ነን።
  እግዞአ መሐረነ ክርስቶስ ይቅር ይበለን አሜን!!!

 9. abrehet November 4, 2015 at 7:51 am Reply

  ከሳቸው ይልቅ ለቤ/ክ ሥርዓት መቆም ይሻላል

 10. shitaye November 5, 2015 at 9:39 am Reply

  enante kumartegnoch nachihu yawum yemeskelu sir d/n(daniel kibret)
  lenegeru kirstosnm bihon ergtegna negn ende alefut wondmochachihu atkebelum neber mkniyat zerafiwech silehonachihu

 11. Temesgen November 5, 2015 at 11:19 am Reply

  በእውነቱ በጣም ያሳፍራል፣ በተጋድሎ የተቀበልናትን እምነታችንን በምድራዊ ማህተም ሹም ሽረት፤ በዕውነት እድለቢስነቴ በዚህ ዘመን መፈጠሬን ጠላሁት። ኦርቶዶክስ ማህተማ የክርስቶስ ደም ነበር፤ ዛሬ ግን ምድራዊ ማህተብ; ቅጥራ የመላዕክት ሰይፍ ነበር ዛሬ ግን ምድራዊው ጠባቂ። እግዞታ እግዞታ እኔ ያኔ በቤቱ ስናገለግል ትዝ ይለኛል ሰባኪው ስለ ከሳሽነት ያስተምር ነበር፤ ክስ የዲያቢሎስ ነው እያለ ዛሬስ ምን ተገኘና ሰውን ያውም አገልጋይን እምንከስ??? የሆነ ያልተመቸን ነገር ካለ በጥቅም፣ አገልግሎት መክሰስ፤ ሰንበት ት/ቤትን አድጌበታለው ስለፍቅር ይሰበካል ግን እርስ በርስ ፍቅር የለም፤ ስለሰላም ይነገራል ግን በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላም የለም። ግን ብናስተውል ይህ ሁሉ የጠላት አሰራር ነው፥ እስኪ ለአገልግሎትና አገልግሎት ብቻ እንቁም ያሁሉ ከንቱ መሆኑን ይገለጥልናል።
  ይህን ሁሉ ያልኩት ሰበት ት/ቤቱን እንካን ደስ አላቹህ የሚለውን ስመለከት ነው። ለመሆኑ ሰንበት ት.ቤትና ሰበካ ጉባኤው ሲጨመር ልማት ኮሚቴና ወዘተረፈ መቼ እንደልጅነት ፍቅር ይደማመጡ ይተዋወቁ ይረዳዱ ይሆን???? ያን ጊዜ አብልጬ ናፈኩኝ፥ የተሻለውን ግዜ ይምጣልን! አባታችንን በሰላም በጤና አገልግሎታቸውን ይባርክልን። አሜን!!

 12. Anonymous November 5, 2015 at 1:57 pm Reply

  የሰንበት ት/ምህርት ቤት ነው ያላችሁ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ምን እንደሚሰራ እናውቃለን እድሜ ለእናንተ ስንቱን ከቤተክርስቲያን አራቃችሁት፣ በእናንተ ምክንያት ሐይማኖታችን ሲሰደብ ይኖራል፤ ስንት እህቶቻችን ሰንበት ትምህርት ቤት ብለው እየሄዱ በእናንተ እየተታለሉ በውርጃ ወይም የቤተ ክርስቲያን ሰው እየተባልኩ አርግዤ ብገኝ ሰው ምን የለኛል እያሉ መርዝ እንዳለቁ ቤት ይቁጠረው ደግሞ ሰው ሁናችሁ በሰው ላይ ትፈርዳላችሁ፤ የጻፋችሁት ጽሁፍ ርዕስ እርዕሱ እራሱ ያስጠላል፡፡ እባካችሁ ፖለቲካችሁን ተውን ከቤተክሪስቲያን በናንተ ምክንያት ብንርቅ በፌስቡካችን መጣችሁብንሰ፤ እናንተ ስማችሁ ብዙ ተሐድሶ፣ ማህበረ ቅዱሳን/ቅዱሶቹ እባካችሁ ተውን ሰው ምንም የማያውቅ ታደርጋላችሁ መምህር ግርማ አጥፍተውም ከሆነ እግዚሐብሄር ይፈረድባቸው፡፡ ለእኔ ግን ቅናት ነው ተከታይ በዛላቸው በሚል፡፡ ልክ እየሱስ ክርስቶስን በሰንበተ ፈወስክ፣ እንደዚህ አደረገህ ብለው እንዳሰቀሉት የናንተ መሰሎች እናንተም እንደዚያው ነው ታሪክ ራሱን ደገመ…… የሰበካ ጊዜ አልቋል፣ ሰውም ነቅቷል እራሱ ያነባል ወደፈለጋችሁበት በጭፍን አይመራም የእናንተን እውቀተ ቢስ ሰበካን የሚሰማ የለም አሁን የእምነታችንን ጥንካሬ በተግባር የምናሳይበት ጊዜ ላይ ነን ይህ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ የዕምነት አባቶች እየተደረገ እያየን ነው፡፡ በእናንተ ምክንያት ይህ ከመሆን አይቀርም፡፡
  እባካችሁ ተናግራች አታናግሩን፡፡

 13. Anonymous November 5, 2015 at 2:31 pm Reply

  Egziabher Eko beman egnan liyadinen endefelege anawkim. …..mefred yikir

 14. beltesht12@gmail.com November 6, 2015 at 3:41 pm Reply

  Medhaniyalem kiristos temelso bimeta Tiseklutalachihu…….Aye Hara tewahido…..shame on you! Ye haimanot sinelibona enquan yelachihum…..Egna Yayen Enmesekiralen……Ye Egziabhern madan ayitenal….Long Live Memhir Girma!!!!

 15. senu November 6, 2015 at 8:53 pm Reply

  be Istifanos yeteserawen wenjel man yekses ???
  astedadarew ,ke leletu 7 seat ke Gibew awtito yetalat yene bete deha ,, Lijwal jib yasbelachu enante aydelachu ???
  le fird enaqerbachuwalen gena !!!YE ISTIFANOS YESENBET TEMAREWOCH BE gibew Chat tebelubet yelem ??

  qoy negeru yeder !!!!!

 16. Anonymous November 11, 2015 at 11:41 am Reply

  ኣይይይይ ኣሰፈርዎች ሰው ኢኮ ወንጀል ሰርተሃል ተብሎ ነው የምከሰሰ ሰው ኣዳንክ ብላቹ ትከሳላቹ እ/ር ይቅር ይበላቹ

 17. Anonymous November 12, 2015 at 12:50 pm Reply

  እናንተ አትበሉ አታስበሉ ። አልታወቃችሁም እንጂ በወሬ መንጋውን ለመፍታት የተነሳችሁ ጸረ ተዋህዶ ናችሁ

 18. Anonymous November 16, 2015 at 8:28 pm Reply

  እስኪ እናንተ ምን ዕድቅ ሰራችሁና ነው አባታችን። የምትከሱአቸው ” እኛ እንደናንተ መምህር ን ቀሚስ ለብሰው ሳይሆን ያየናቸው ውስጣቸውን ነው እናንተእንዳላችሁት ሳይሆን ከምንም የነዕጽ ታልቅ ሀዋርያ ናቸው እንደእናንተ በዘመናዊ ቀሚስናየወርቅ መስቀል አንገት ላይ አርጎ አጽያተኛን መካነን አይደለም። እስኪ አንድ ጥያቄልጠይቃችሁ። ከብጽአባቶች ጀምራችሁ አንድ ሴት ሱሪ ለብሳ ስትአያት ወይ ደግሞአንድ ወንድ ጸጉረን እንደሴት አድርጎ ሲሄድ ስትአዩት በክርስቶስ መስቀል ለመባረክ እንኮን የምትነፍጉ አይላችሀምን???አባታችን መምህራችን ግን እንደነዚህ ያሉትን ያስተሩ ያጠመቁ ለንሰሀ ያበቁናቅዱስቁርባን ያብቁ ናቸው!!!የራሳችሁን ጉድፍ በደንብ እዩ መጀመሪያ እሺ”:ከተዋህዶ ልጆች ከሳውዲ

 19. Anonymous December 10, 2015 at 11:13 am Reply

  ማን ፈራጅ አደረጋችሁ እናንተ ሰንበት ተማሪዎች

 20. የማርያም ልጅ December 13, 2015 at 10:48 am Reply

  የማርያም ልጅ

 21. Anonymous January 1, 2016 at 6:56 am Reply

  እናንተ ሾካኮት ድሮስ የሚሠራ አይወደድም ምቀኛ ምቀኛ ምቀኛ…………………

 22. Anonymous March 31, 2016 at 12:40 pm Reply

  I know this racist systematic stab. I am different from you is that clear balk and white. you stood for your father of devil so that we are genuinely understand you. you kenona make for your self that is not dogema

 23. Anonymous March 31, 2016 at 2:26 pm Reply

  for political leader *mathias* no man has a good memory to be successful liar (abrham lincoin)

 24. Anonymous May 25, 2016 at 6:43 am Reply

  እናንተ የ ሰይጣን ልጆች ማበላሸት እንጂ ማስተካከል አትችሉም

 25. Anonymous August 5, 2016 at 1:09 pm Reply

  Eyesuse bemeder lay mteto siyastemer tesedboal ,tewardoal lega hateyeat sile tesekaytoal ,tegerfoal ,tesekeloal,selezihe bezu ataweru sera yelachehum mekega hulu .men adereguachu kenat yasemeselebachual ,arfachehu tekemtu setanu new yemiyanagerachehu ,yelekes heduna danu were ataweru

 26. Anonymous October 14, 2016 at 12:54 pm Reply

  enkuan esachew E/r telat alew menem betelu Ayasdenkem yeker yebelachehu

 27. እስክንድር እንዳለ December 18, 2016 at 5:24 am Reply

  እረ እረ እስክመቼ እርስ በእርሳቹ ትባላላችሁ አጥማቂ ነኝ ባዩ ትላላችሁ እናንተ የቤተ ክርስትያን ልጆች ነን ባዮች መጽሀፍ ቅዱስ የሚለው እርስ በእርሳችሁ
  ተዋደዱ አይድለምን ?

 28. Ermias Abebe March 23, 2017 at 12:58 pm Reply

  መልካም ስራ የሚሰሩትን አባታችንን ስማቸዉን ያለ አግባብ እያጠፋችሁ ሰይጣንን አትተባበሩ እናንተ የእፉኝት ልጆች

 29. Anonymous May 29, 2017 at 2:53 pm Reply

  ሐራዎች፣ ዛሬ ደግሞ ከቤተ ክህነቷ ቀጥሎ በናንተ ላይ ሀፍረት ተሰምቶኛል፡፡ እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ይዛችሁ አባታችንን ልታዉቋቸዉ ከቶዉንም አትችሉም፡፡

 30. Kibrom Mesfin Asgedom July 13, 2017 at 2:01 pm Reply

  ይሄ ከ መልካም የ በ ተቤተ ክርስትያን አሳቢነት የሚመነች አይመስለኝም:: የተዘረዘሩ ምክንያቶች ከ ሃክ የራቁ ና ፈተራዎች ናችዉ:: መምህር ግርማ ረጅም እድሜይስትል ን::

 31. Gebere Mesekel November 3, 2017 at 6:50 am Reply

  እህቶቼወንድሞቼ ማስተዋሉን እግዚሀብሂር ይስጣችሁ ወደ ህይወታችሁ ተመለሱ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: