ስመ ‹‹መቲራ››ው ሲመተር! ቀንደኛው ፅልመታዊና ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገ/መድኅን ገ/ጊዮርጊስ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ ታገዱ!

 • ጀብደኛው ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በመንበረ ፓትርያሪኩ አሠራር ጣልቃ በመግባት  ከሥ ሓላፊዎችና ከጥበቃ አባላት ጋራ ሁከት በመፍጠር አቤቱታ ቀርቦባቸዋል

Picture 0272

 • ከምስጉን አቋማቸው በመንሸራተት ከሙሰኞች ጋራ ‹መሸፋፈን› የጀመሩት አቡ ሕዝቅኤል በሙሰኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ላይ የተላለፈውን እግድ በጣልቃ ገብነት መቃወማቸው አስገራሚ ኾኗል
 • ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በክልል ትግራይ ስድስት አህጉረ ስብከት በሕገ ወጥነት ከተፈረጀው ‹‹አቡነ ሰላማ ምትሕግጋዝ ማኅበር›› የተባለ የጥፋት ቡድን ጋራ በመቀናጀት÷ የኑፋቄ ትምህርት ሲያሰራጩ፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ካህናቱና ምእመናኑ መካከል ሰላም አደፍራሽ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ፣ የጥንታውያን አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችን በጥቅም በመደለል ቅርሶችን ለባዕዳን አሳልፈው ለመስጠት ዕቅድ ይዘው ሲሰናዱ የነበሩ ናቸው፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ገዳማት መምሪያ ዋና ሓላፊ ለመኾን እየተፍጨረጨሩ ያሉትም ይህን ተልእኳቸውን በማሳካት ሕገ ወጥ ጥቅም ለማካበት ነው!!
 • ከፕትርክና ምርጫው በፊት በነበረው የሽግግር ወቅት የዐቃቤ መንበሩን ቲተር በመያዝ በርካታ ሕገ ወጥ ደብዳቤዎችን አዘጋጅተዋል፤ በዚህ አጋጣሚ ጀብደኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ዐቃቤ መንበሩን በመደለል ባጻፉት አሠራሩን የጣሰ ሕገ ወጥ የቅጥር ደብዳቤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ገዳማት መመሪያ ዋና ሓላፊ ኾነው ለመሾም ያደረጉት ሙከራ በማኔጅመንት ኮሚቴው ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹መነኩሴ›› ነኝ ባዩ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን የማኔጅመንት ኮሚቴውን አባላት ስም በማጥፋት ከመጠመዳቸውም በላይ ዋና ሥራ አስኪያጁን ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን በተደጋጋሚ ዘልፈዋቸዋል!!
 • ኪራይ ሰብሳቢው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በምሥራቅ ትግራይ – ዓዲ ግራት ሀ/ስብከት በሚገኘው ለሀ/ስብከቱ በማይታዘዙበት የደብረ ዐላማ ኢሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም በሰበሰቧቸው ትጉሃን መነኰሳትና አሳድጋቸዋለኹ በሚሏቸው ምስኪን ጓለ ሙታን ሰበብ÷ ከዩኔስኮ፣ ዩኒሴፍ እና ሌሎች በጎ አድራጊዎች ያገኙትን ርዳታ ለግል ጥቅማቸው በማዋል በስማቸው የሸመቷቸውን ኮድ – 05 ላንድ ክሩዘር እና ዶልፊን ሞዴል መኪኖች በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ያሽከረክራሉ፤ በአምባሳደር ሕንፃ የመንግሥት አፓርታማ ቤት ቁልፍም በብር 350,000 እጅ መንሻ ገዝተዋል፤ በሲ.ኤም.ሲ ቪላ ቤት መሥራታቸውም ይነገርላቸዋል!!
 • በሀ/ስብከታቸው መዋቅር የማይታዘዝ ገዳም አበምኔት ነኝ የሚሉት ነውጠኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በሀ/ስብከታቸው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ላይ ሽጉጥ በመምዘዝ ፍላጎታቸውን በጉልበት ለማስፈጸም እስከ መሞከር ደርሰዋል!!
 • ርካሽ ተወዳጅነት ለማግኘት በማሰብ  በአዲሱ ፓትርያሪ  በዓለ ሢመት ወቅት ያለ አስመራጭ ኮሚቴው ዕውቅናና ያለተመራጩ ፓትርያሪ ፈቃድ በብር ኀምሳ ሺሕ ወጪ አሠርተው ያሰራጩት ፖስተር በፓትርያሪኩ ትእዛዝ ከመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር እንዲወገድ ተደርጓል
 • ጎጠኛው ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን የንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጉዳይ አስፈጻሚ በመኾን በከፍተኛ የፖሊቲካና የደኅንነት ባለሥልጣናት ስም መነገዳቸውንና ማስፈራራታቸውን ቀጥለዋል፡፡ በስማቸው ከሚነግዱባቸው ባለሥልጣናት መካከል÷ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕርግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሥዩም መስፍን እና የደኅንነትና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳይያስ ወልደ ጊዮርጊስ ይገኙባቸዋል፡፡
 • መነኵሴ ነኝ ባዩ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን÷ የቅዱሳን አበውን አርዑተ ምንኵስና በመናቅና በማቃለል   ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ካህናት አለባበስና ገዳማውያን ሥርዐት ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ በዋና ዋና ከተሞች በተለይም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ለመነኰሳት በማይገቡ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ምንኵስናንና ኦርቶዶክሳዊነትን በአጠቃላይ የሚያስነቅፉ በርካታ ስመ መነኰሳት ምሳሌ ናቸው፡፡
 • ‹‹አባ›› ነኝ ባዩ ገብረ መድኅን በመቐለ ከሁለት ሴቶች የወለዷቸውን ልጆች ረዳት ለሌላቸው እናቶቻቸው ጥለው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሴቶችን /ዝሙት አዳሪዎችንና መሰል መነኰሳዪያትን ጨምሮ/ በሕገ ወጥ መንገድ ባካበቱት ገንዘብ እየደለሉ ይማግጣሉ፡፡ ከመሰል ድሉል ስመ መነኰሳዪያቱ መካከል÷ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች የሚያቀብሉትን መረጃ በማሾለክ የምትተባበር አንዲት የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት የመዝገብ ቤት ሠራተኛ እንደምትገኝበት ተጠቁሟል፡፡ ‹‹አባ›› ነኝ ባዩ ግለሰ ምንኩስናው ይቅርና አሁኑ ወቅት ከኤች.አይ.ቪ ጋራ የሚኖሩና የመድኃኒት ተጠቃሚ መኾናቸውን እያወቁ ከሴሰኛ ተግባራቸው አለመቆጠባቸው ፍጹም ሓላፊነት የማይሰማቸው፣ ለአንዳችም ሓላፊነት የማይበቁ መኾናቸውን ያረጋግጣል!!

 

የዜናው ዝርዝር ከአባሪ ማስረጃዎች ጋራ ይቀጥላል፡፡

Advertisements

13 thoughts on “ስመ ‹‹መቲራ››ው ሲመተር! ቀንደኛው ፅልመታዊና ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገ/መድኅን ገ/ጊዮርጊስ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ ታገዱ!

 1. mengaw yetebek May 13, 2013 at 5:09 am Reply

  የሰውየው መጥፎ ስነምግባር ቢኖራቸውም ለቤተክርስቲያን ሲባል አንዳንዱን አገላለፆች ባትጠቀሙበት ለምሳሌ “በመቐለ ከሁለት ሴቶች የወለዷቸውን ልጆች ሜዳ ላይ በትነው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሴቶችን /ዝሙት አዳሪዎችንና መሰል መነኰሳዪያትን ጨምሮ/ በሕገ “፤”ከመሰል ድሉል ስመ መነኰሳዪያቱ” “በአሁኑ ወቅት ከኤች.አይ.ቪ ጋራ የሚኖሩና የመድኃኒት ተጠቃሚ መኾናቸውን እያወቁ ከሴሰኛ” ንዳንዶቹ ማስረጃ የሚያስፈልጋቸው ናቸው ውየው ችግር እነዳለባቸው ግን እኛም እናውቃለን

 2. hiruy May 13, 2013 at 6:38 am Reply

  i appreciate ur ardent followup. but u r still far behind in using moderate words and distinguishing b/n personal and official duties.doing that u r exposing (if it is true) not only z sin of Aba but also eroding z image of EOTC and eroding Its beloved followers’ trust towards monks,priests,deacons,preachers,bureau officials.u r truly sons of EOTC in terms of belief but not d/t from those anti-EOTC tehadso blogs in terms of ethical reporting. Pls learn how to report from Hamer,Smatsidk and MK’s official blogs.

 3. Anonymous May 13, 2013 at 9:36 am Reply

  PHOTO ACHEWEN POSTE ADEWGULEN

 4. Chiqunu May 14, 2013 at 6:07 am Reply

  This blog is also one of the Tehadiso blogs.

 5. Anonymous May 14, 2013 at 3:20 pm Reply

  መቼም የሐራ ተዋህዶ ነገር ወደቀ ሲሉ ተሰበረ ነው፡፡ ደብዳቤው ሁኔታው እስኪጣራ ለጊዜው ታገዱ ይላል እንጂ እስከወዲያኛው መታገዳቸውን አያሳይም፡፡ ደግሞም ማኅበረ ቅዱሳን ሤራ ሸርቦ እርሳቸው በሆነው ባልሆነው እንዲታገዱ አድርጎ ቢሆንስ ማን ያውቃል?

  • Ben May 15, 2013 at 12:51 pm Reply

   ልክ ተሃድሶዎቹና ጴንጤዎቹ ሴራ እንደሚሸርቡት ማለትህ ነው? ደሞ ለሴራ ከተሃድሶ በላይ ለአሳር ነው።

 6. Yirga May 14, 2013 at 8:12 pm Reply

  በመሠረቱ የተገለጠበት ቃል ለመነኩሴ ከበድ ያለ ቢሆንም ምዕመናን የግድ ሊያውቋቸው የሚገቡ ነገሮች ይኖራሉ፡፡ እነርሱ በግልጽ ካልተነገሩ በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በምዕመናን ሕይወት ላይ አደጋ ስለሚኖረው ነው፡፡ ከዚህ የሚበልጡ ብዙ ያልተገለጡ እውነታዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ልንዘነጋ አይገባም፡፡ ምዕመናኑ እኮ በቅድስና የሚኖሩትን እውነተኛ አባቶችን ምንም ምንኩስና ሳይኖራቸው እንደ ቢዝነስ በማየት ከመርካቶ የምንኩስና ልብስና ቆብ ለብሰው አባቶችን የሚያሰድቡትን ለይቶ ያውቃል፡፡የእኒህ ሰውየ መታገድ ለቤተ ክርስቲያን ለጊዜውም ቢሆን ድል ነው፡፡ ለጠላት አሳልፎ በመስጠት በቤተ ክርስቲያን ላይ ከመሰሎቻቸው ጋር እየተሠራ ያለውን ብትመለከቱ ይህን አስተያየት ለመስጠት አትገደዱም ነበር፡፡ ማለትም ምንም እንኳን ቃላቶቹ የተገለጠባቸው ከሚሠራው አደጋና ጋር ሲነጻጸር እውነታውን ለማውጣት ሲባል ግድ ይሆናል፡፡

 7. mengaw yetebek May 15, 2013 at 5:05 am Reply

  ቤተክርስቲያን እንዲህ ያለ አገላለፅ አላስተማረችንም። ወንጌልም ምን እንደሚል አስተውሉት እንጂ

 8. ARAYA May 15, 2013 at 8:01 am Reply

  no no no no no……..negere menekosat endale huno, ahun ahun EOTC(especially in addisababa) eyetebetebetech yalechiw mainly besenbet temari new. if u disagree with them u r either leba or tehadiso(who wait declaration of SYNODUS!!!!). no dissenting opinion,no need of evidence to label ‘leba’ or tehadso z hated one who goes against their wish(not wish of EOTC). I saw them chanting leba…leba…leba..in awdemihret against Aleqa and trying to snatch z speaker rather than solving problems in a legal and civilized manner. what an anarchy!!!using more than one bank account,unwillingness to report audit report,disobidience and lack of respect for the hierarchy of z church,disseminating misinformation for z public,prohibition of halls for z church internal matters such as for meeting and matrimony w/o a good cause,sometimes strike not to sing(as was in Lafto St.Michael for 2005Tahsas Beata,kidase bihon min liadergu new??!!!!!!). Anyway bizu nen bemil smet ena internet legna bicha bilen banmestadek. yB/Kirstian guday yagebanal gin degmo agelgayochuam endemiyagebachew anrsa. ye’tehadisow anson degmo egna EOTC’n akefnat blen endanankat.

 9. helen May 16, 2013 at 1:41 pm Reply

  በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሃዱ ኣምላክ ኣሜን።
  በጣም የሚገርም ዘመን ነው የደረስነው ምነው ሃራ ዘ ተዋህዶዎች ምነው ኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት እንዲህ ነው የምታስተምረው??? ኣባቶች እንዲህ ነው የሚያስተምሩት ??? ወንጌል እንደዚህ ነው የሚለው??? እንደኔ ኣስተያየት ይህ ሆን ተብሎ መነኮሳትንና የገዳም ኣባቶችን ለማጥላላትና በህዝብ ተቀባይነትና ኣመኔታ እንዳያገኙ ሆን ተብሎ የተዘጋጀ የመናፍቃን ወይም የተሃድሶዎች ቅንብር ይመስለኛል። ደግሞስ ማን ለማን ይፈርዳል ? ማን ለማን ይከሳል? ማን ንጹህ ኣለና ይህስ የእግዚኣብሄር ስራ መጋፋት መስሎ ይሰማኛል ። ይፍረድ እግዚኣብሄር ፈራጅ ነውና ለሃጥያተኞች ይውቀስ ከሃጥያት ነጻ ነውና እናንተ ግን ከሃጥያት ከበደል ነጻ ኣይደላቹሁምና ልትከሱም ልትፈርዱም ማን ስልጣን ሰጣቹ??? ለራሳቹ እነማን እንደሆናቹ እንዴት እናውቃለን መናፍቃን ትሆኑ ዋላ…………

 10. abrha mebrahtu May 17, 2013 at 6:49 am Reply

  ለንድ መኔኩሴ እዲህ ተብሎ መፃፉ አስገራሚ ነው ሃራ ዘ ተዋህዶዎች ምነው ኦርቶዶክስ ክርስትና ይህነው ??? ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ራሳቹ ናቹ ምክንያቱ ሁሌ መነኩሴ መንቀፍ ስለሆነ ስለሆነ ስራቹህ አይፈረድባቹሁም በቤተክርስትያን ገብታችህ አለመማራችህ ነው ምእመኑ መነኩሴ እዲጠላ ነው ስለዘህ እምነት ካላችህ የቤተክርስትያ አስተምህሮ ፃፉ

 11. aba berehane selassa asefewe April 2, 2014 at 6:51 pm Reply

  1ኛ የዮሐንስ መልእክት
  2፥9
  በብርሃን አለሁ የሚል ወንድሙንም የሚጠላ እስከ አሁን በጨለማ አለ።

  2፥11
  ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ አለ፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ የሚሄድበትንም አያውቅም፥ ጨለማው ዓይኖቹን አሳውሮታልና።

  3፥15
  ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።

 12. www April 2, 2014 at 6:56 pm Reply

  የዮሐንስ ወንጌል 8
  7 መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።
  KJV
  John 8
  7 So when they continued asking him, he lifted up himself, and said unto them, He that is without sin among you, let him first cast a stone at her.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: