የኮሌጁ አስተዳደር የተቋረጠው ትምህርት መጀመሩን አስታወቀ፤ የደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ እስከ ዐርብ ምላሽ ያገኛል

ከመጋቢት ፴ ቀን ጀምሮ ተዘግቶ የቆየው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ከዛሬ ጀምሮ እንዲቀጥል መወሰኑን የኮሌጁ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ማስታወቁ ተገለጸ፡፡

ደቀ መዛሙርቱን ‹‹በአግባቡ ትምህርት አልጀመራችኹም›› በሚል አስተዳደሩ ‹‹ላልተወሰነ ጊዜ›› የዘጋው መርሐ ግብር እንደሚጀመር የተገለጸው፣ ደቀ መዛሙርቱ በአስተዳደሩ ላይ ያነሷቸውን ጥያቄዎች አጣርቶ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመው የጋራ ኮሚቴ፣ ዛሬ ጠዋት ከኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ጋራ እየተነጋገረ በነበረበት ወቅት መኾኑ ታውቋል፡፡  በጉዳዩ ላይ ከፓትርያሪኩ የተሰጠ መመሪያም እንዳለ ከአስተዳደሩ በወጣው ማስታወቂያ ላይ መመልከቱ ተዘግቧል፡፡

ከቀድሞውም የመርሐ ግብሩን መዘጋት የተቃወሙት የኮሌጁ መምህራን ለኮሚቴውና ለአስተዳደሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፣ ማስተማር እንዲያቆሙ በደብዳቤ የተላለፈላቸውን ትእዛዝ የሚሽር ሌላ ደብዳቤ በተመሳሳይ ሰዓት እንዲሰጣቸው መደረጉ ተገልጧል፡፡

ከመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በተወከሉ አራት ሓላፊዎች፣ ከመምህራንና ከደቀ መዛሙርት በተውጣጡ ሁለት ሁለት አስረጂዎች የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ ሥራውን የጀመረ ሲኾን  የማጣራት ተግባሩን የሚያከናውነው፣ በአራት ዋና ዋና ነጥቦች በተለዩ የደቀ መዛሙርቱ ጥያቄዎች ላይ በማተኰር ነው፡፡

በዚህም መሠረት ከትምህርት አስተዳደር ጋራ በተገናኘ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ተቃውሞ የቀረበባቸው ሁለቱ ሓላፊዎች፣ ከኮሌጁ አስተዳደር ጉባኤ ጋራ ተያይዘው የተዘረዘሩ የሙስናና ብልሹ አሠራር ችግሮች፣ የደቀ መዛሙርት መማክርት ጉባኤ የቢሮና ተያያዥ ጥያቄዎች እንዲሁም የካፊቴሪያውን አገልግሎት ማሻሻልና በዚህም ውስጥ ደቀ መዛሙርቱ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በተመለከተ የተነሡ ጉዳዮች እስከ መጪው ዐርብ፣ ሚያዝያ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ተጣርተው እልባት እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል፡፡

አጣሪ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ጠዋት በኮሌጁ እንደደረሰ የተነጋገረው ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ተወካዮች ጋራ ነው፡፡ በውይይቱ ደቀ መዛሙርቱ ርዳታ ለማሰባሰብ ለጥፈዋቸው የሰነበቱትን ጥቅሶችና ሌሎች ቁሳቁሶችን እንዲያነሡና እንዲሰበስቡ ተደርጓል፤ አገልግሎቱን ያቋረጠው የደቀ መዛሙርቱ ካፊቴሪያም ከምሽት የራት ሰዓት ጀምሮ ክፍት መደረጉ ተነግሯል፡፡

Advertisements

5 thoughts on “የኮሌጁ አስተዳደር የተቋረጠው ትምህርት መጀመሩን አስታወቀ፤ የደቀ መዛሙርቱ ጥያቄ እስከ ዐርብ ምላሽ ያገኛል

 1. Anonymous April 22, 2013 at 8:50 pm Reply

  temesgen

 2. belachew April 22, 2013 at 10:39 pm Reply

  ኮሌጁ የግል ካምፓኒ ነው እንዴ?

  ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አማኞች እና ተጠሪነቱ ለሲኖዶሱ የሆነው መንፈሳዊ ኮሌጅን ሲፈልጉ ሲዘጉ ሲፈልጉ ሲከፍቱ
  እንደግል ካምፓኒ የሚያሽከረክሩት ዓይናቸው ማየት ያቆመው ጳጳስ አባ ጢሞቴዎስ ዛሬ ደግሞ ኮሌጁን ልክፈት ብለዋል::
  ልክ እንደ እርሳቸው ዓይን አልባ የሆነው ሲኖዶስ እና አስተዳደር ጉዳዩን እንደ ድራማ ዝም ብሎ እያየ ነው::

  ኮሌጁ እንዲከፈት ቀጥተኛ የመንግስት ትእዛዝ እንዳለበት ይነገራል:: ተማሪዎቹ ለመብታቸው በጽናት እንደትናንቱ ከቆሙ
  ሁለቱን ዘማውያን እና ሃይማኖት አልባ አስተዳደሮች (አቶ ዘላለም እና አቶ ፈስሃን) ከኮሌጁ ተባረው ወደ ጀመሩት የቀበሌ
  ስራ እንዲጠቃለሉ ማድረጉ አይቀርም:: ከዚህ ቦኃላ ግን በዕሜ እና በህመም ምክንያት ማየት እና መስማት የተሳናቸው ጳጳስ
  ይህን የትምህርት ተቋም ሊመሩ አይችሉም::

 3. mengaw yetebek April 23, 2013 at 6:08 am Reply

  ተማሪዎቹ መደገፍ ሌላ ሊቀጳሱና ቅዱስ ሲኖዶስ መስደብ ሌላ ምን ቸገናኘውና ትርምስምሱን ማውጣት የለብህም አቶ በላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ አጣርቶ እንጂ ሳያጣራ መወሰን ስለመይችል ሊሆን ይችላል መፍትሄው የዘገየው በችኮላ ቢወስንም እንዳንተው አይነቱ ተሳዳቢ ቅር መሰኘቱና መወረፉ አይቀርም ነበር እንደኔ ዋናው ነገር ኮሌጁ መከፈቱ ነው።

 4. mengaw yetebek April 23, 2013 at 6:10 am Reply

  ተማሪዎቹ መደገፍ ሌላ ሊቀጳጳሱና ቅዱስ ሲኖዶስ መስደብ ሌላ ምን አገናኘውና ትርምስምሱን ማውጣት የለብህም አቶ በላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ አጣርቶ እንጂ ሳያጣራ መወሰን ስለመይችል ሊሆን ይችላል መፍትሄው የዘገየው በችኮላ ቢወስንም እንዳንተው አይነቱ ተሳዳቢ ቅር መሰኘቱና መወረፉ አይቀርም ነበር እንደኔ ዋናው ነገር ኮሌጁ መከፈቱ ነው።

 5. kidanu April 23, 2013 at 11:53 am Reply

  ከአስተዳደር መነሳት ብቻ አይደለም ጉዳዩ፣ ነገር ግን የኮሌጁን ትንሣኤ በጌታ ትንሣኤ ቀን ለማየት ኮሌጁን መጫወቻ ያደረጉት ሰዎች ከኮሌጁ መውጣት አለባቸው፡፡ እነኚህን ሰዎች ዋናውን ጨምሮ ገለል አድርጓቸው እና ኮሌጁ እንደ ስሙ ለቤተ ክርስቲያን ጠበቃ የሚሆኑ በአባቶቻቸው የሚተኩ ደቀ መዛሙርትን ያውጣ፡፡

  ይህም፣
  ለደቀ መዛሙርቱ ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው በቁም እየሞቱ ነውና፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: