ሰበር ዜና – ‹‹ለፓትርያሪኩ መመሪያ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል›› የተባሉት ኣባይ ፀሃየ ከደጅ ተመለሱ

 • በሦስት ኀይሎየተደራጀው የጨለማው ቡድን ‹‹የኣባይ ፀሃዬን አመራር›› ያቀናጃል
 • መመሪያው÷ የልዩ ጽ/ቤት፣ የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ ፕሮቶኮል፣ ጥበቃ ሓላፊዎችን ምደባዎች ይመለከታል ተብሏል
 • ‹‹ኣባይ ፀሃዬ ከስኳር ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን በበላይነት እንዲመሩ ከመንግሥት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በትግራዎት እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ ለሚኒስትሮች የሚፈለገውን ጥቅም እያቀረብን እናስፈጽመዋለን፡፡››

/ኣባይ ፀሃዬ ለፓትርያሪኩ የሚሰጡትን ‹‹አመራር›› ከእነ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ ያስተባብራሉ የተባሉት በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት አባ ገብረ መድኅን  ገብረ ጊዮርጊስ ዛሬ ጠዋት የተናገሩት/

 • ፓትርያሪኩ ‹‹አባ›› ነኝ ባዩን ከግቢው እንዲያርቁላቸው መመሪያ ሰጥተዋል፤ ተፈጻሚነት ይኖረው ይኾን?
 • መንግሥት፣ የቤተ ክርስቲያን አመራር፣ ካህኑና ምእመኑ ጉዳዩን ከምር አጢነው አቋም እንዲወስዱ ተጠይቋል፡፡
abai-tsehaye-tigraionline

አቶ ኣባይ ፀሃዬ

ከአምስተኛው ፓትርያሪክ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ፣ የመንበረ ፓትርያሪኩን ላዕላይ መዋቅሮች በመቆጣጠርና ለተቋማዊ ለውጥ የታቀዱትን ተግባራት በማምከን÷ 1)ቡድናዊና ግለሰባዊ ጥቅሙን አስጠብቆ ለመቆየት፣ 2)ኦርቶዶክሳዊ ማንነትን በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ደብዛውን ለማጥፋት በልዩ ኹኔታ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የጨለማው ቡድን÷ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን በጎጠኝነት፣ በፖሊቲካዊ ታማኝነትና በጥቅም ስቦ እና አቅርቦ ማሰለፍ መጀመሩ ተዘገበ፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎችና ድርጅቶች ውስጥ በሓላፊነት ደረጃ የተቀመጡ ጥቅመኞችን ጨምሮ የታወቀ ሹመት የሌላቸውን ነገር ግን የሁሉ ፈጣሪና ገባሪ ለመኾን ‹‹ሥልጣን›› ያገኙ ግለሰቦችን የሚያካትተው የጨለማ ቡድኑ÷ በፓትርያሪኩ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ላይ ማሰለፍ የጀመረው ‹‹የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ነው›› ተብሏል፡፡ ቡድኑ በዚህ ስትራተጂው የህወሓት/ኢሕአዴግን ባለሥልጣናት ተጽዕኖ በመጠቀም በማንኛውም ቦታ በተለይም በቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ላይ ተጽዕኖውን ለማጠናከርና ያሻውን ለመፈጸም ማቀዱ ነው የተነገረው፡፡

ይኸው ስትራተጂ ባለፉት ኻያ ዓመታት መንበረ ፓትርያሪኩ ለክፍፍልና ትርምስ የተዳረገበት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለጥቃትና ድብደባ የተጋለጡበት እንደነበር ያስታወሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ስልቱ በመልኩ አዲስ ባይሆንም በይዘቱ ግን ቡድኑ የተለየ ቁመና ይዞ የተደራጀበት መኾኑን ያስረዳሉ፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ፅልመታዊ ቡድኑ ለሦስት ኀይል ተከፍሎ በተለያዩ ግለሰቦች የሚመራ ሲሆን የተመረጡ የመንግሥት ባለሥልጣናትን እየተፈራረቀ በመወትወት/በማግባባት ተመሳሳይ ጉዳይን ከተለያየ አቅጣጫ እያስተነተነ ስለጉዳዩ አንድ ዐይነት ቀለም/ሥዕል ለመፍጠር ግፊት ያሳድራል፤ ለኾነ ርምጃ የሚያበቃ ውሳኔ እንዲተላለፍ ያደርጋል፡፡ በዚህም ቡድኑና አባላቱ ለመንግሥት ቀራቢና ተቆርቋሪ፣ ለቤተ ክርስቲያን አሳቢ መስለው ጋርዮሻዊና ግለሰባዊ ጥቅማቸውንና ሥልጣናቸውን ያስጠብቃሉ፡፡

ለሦስት ኀይል የተከፈለውን ‹‹የጨለማ ቡድን›› የሚመሩት ግለሰቦች፡-

 • አባ ገብረ መድኅን ገብረ ጊዮርጊስ – በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔ
 • አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል – በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ዋና ሓላፊ                              
 • ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ – በመዋቅር የማይታወቀው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ                           

በአሁኑ ወቅት በሦስት ኀይል የተደራጀው የጨለማ ቡድን ከውጭ ኀይል ያገኘዋል በተባለ አመራር፣ የመንበረ ፓትርያሪኩን ከፍተኛ መዋቅሮች ለመቆጣጠር በሚያደርገው መፍጨርጨር፣ ለዓላማዬ ዕንቅፋት ናቸው ብሎ በሚያስባቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎችና በቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ላይ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ እያካሄደ ነው፤ ለዚህም የፓትርያሪኩ ድጋፍ እንዳለው አስመስሎ ነው መቀሳቀስ የያዘው፡፡ እንዲያውም ከመረጃው ምንጮች አንዳንዶቹ÷ አዲሱ ፓትርያሪክ ‹‹ሳያውቁ በቡድኑ  ቁጥጥር  ውስጥ ገብተው በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርተው ለመወሰንና የውሳኔያቸውን አፈጻጸም ለመከታተል በማይችሉበት አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል›› እስከማለት ደርሰዋ፡፡

ምንጮቹ ለዚህ ድምዳሜያቸው በአብነት የሚጠቅሱት፣ ከየካቲት ወር አጋማሽ አንሥቶ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት እና በአስተዳደሩ መካከል የተነሣውን ውዝግብና አያያዙን ነው፡፡ እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ውዝግቡ በአጭር ጊዜ እልባት እንዲሰጠው አይፈለግም፡፡ ለዚህም ጣታቸውን የሚቀስሩት ‹‹ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በደብዳቤ የተሠየመኹትና የሚመለከተኝ እኔን ብቻ ነው፤›› በሚሉት የትምህርትና ሥልጠና መምሪያው ሓላፊ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ላይ ነው፡፡

ከደቀ መዛሙርቱም ከሓላፊዎቹም መካከል ምንጮቹ በስም የሚጠቅሷቸውን ግለሰቦች በማቅረብ  ውዝግቡን ሳብ ረገብ እያደረጉ ይዘዋል የተባሉት አባ ሠረቀ ብርሃን፣ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ ፓትርያሪኩን እንዲያነጋግር ከስኳር ኮርፖሬሽኑ ኣባይ ፀሃዬ ጋራ መክረዋል ተብሏል፡፡ አባ ሠረቀ ብርሃን ታዲያ ይህን የሚያደርጉት፣ በርግጥም አካዳሚያዊ መብታቸውንና መልካም አስተዳደርን በመጠየቃቸው በረኀብ እየተቀጡ ላሉት ደቀ መዛሙርት ከአንጀት በማዘን አይደለም፡፡

አባ ሠረቀ ብርሃን ችግሩም መፍትሔውም በግልጽ የሚታወቀውን የደቀ መዛሙርቱንና የአስተዳደሩን ውዝግብ ከዐውዱ ውጭ እያወሳሰቡ በስም የተጠቀሱትን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ወትውተዋል፡፡ በዚህም ጥንተ ጠላታቸው ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ተቋም እና ‹‹የማኅበሩን ተልእኮ የሚያስፈጽሙ ናቸው›› የሚሏቸውን የኮሌጁን ሓላፊዎች እንደ ግለሰብ በከፍተኛ ደረጃ ወንጅሎ (አንዱ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ እንደወሸከተው) ፖሊቲካዊም አስተዳደራዊም ርምጃ እንዲወሰድባቸው የማድረግ ፍላጎታቸው የናረ ኾኗል፡፡ እስከ መጪው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በማሰንበትም ጉዳዩ ተለጥጦና ዐቢይ አጀንዳ ኾኖ የፈለጉት ውሳኔ እንዲተላለፍበትም ነው ዕቅዳቸው፡፡

ሳይገባቸው በተቀመጡበት መምሪያ ረብ ያለው ቁምነገር ለመፈጸም አቅሙም ዝግጁነቱም የሌላቸው አባ ሠረቀ ብርሃን፣ ለዚህ አካይስት አድራጎታቸውና ዕቅዳቸው ተባባሪ አላጡም፤ በቀደሙት ዘገባዎቻችን  እንዳስነበብነው የደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ የተቋቋመው ኮሚቴ ሥራውን እንዳይጀምር በማሰናከል የሚያግዟቸው የፅልመታዊ ቡድኑ የበላይ ተቆጣጣሪ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ አሉላቸው፡፡ ንቡረ እዱ የፓትርያሪኩ አማካሪ መስለውና ራሳቸውን በአማካሪነት ሾመው በቀጣይ የፓትርያሪኩን ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት መመሪያ ለመቆጣጠር አቶ ኣባይ ፀሃየ ለፓትርያሪኩ ‹‹የሚሰጡላቸውን መመሪያ›› የሚጠባበቁ ናቸው፡፡

ሐራዊ ምንጮች በደረሰው ጥቆማ መሠረት፣ አቶ ኣባይ ፀሃየ ለፓትርያሪኩ መመሪያ እንዲሰጡ ማግባባት ያደረጉት በምሥራቅ ትግራይ የደብረ ኣላማ አሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም አበምኔት ነኝ የሚሉት አባ ገብረ መድኅን ገብረ ናቸው፡፡ ‹‹አባ›› ነኝ ባዩ ገብረ መድኅን አበምኔት ነኝ በሚል በስሙ ከሚነግዱበትና ለሀ/ስብከቱ ከማይታዘዙበት ገዳም ‹‹አበምኔትነት›› በቀር በመንበረ ፓትርያሪኩ ይህ ነው የሚባል ሹመት የሌላቸው ናቸው፤ በገዳማት ርዳታ ስም ከፍተኛ ፈንድ ለማጋበስ የቋመጡባትን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊነት ለቀም እስኪያደርጓት ድረስ!!

የአሲራ መቲራው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በሽግግሩ ወቅት ፊት በሰጧቸውና አለመጠን ባቀረቧቸው ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ተሸጋግረው ከቀድሞም ባደለቡት የዝርፊያ ሀብት ላይ አያሌ የግል ሀብት ለማካበት ኹኔታዎችን አመቻችተዋል፤ ራሱን በዳግም አደረጃጀት ባጠናከረው ፅልመታዊ ቡድን ውስጥም በቅድመ ግንባር የተሰለፉ፣ ስንኳን ለመነኲሴ ለሰብአ ዓለም አጸያፊ በኾኑ የድፍረት ኀጣውእ ተሰነካክለው በማሰነካከል የታወቁ፣ በሄዱበት የማይለዩትን ሽጉጥ በሠባራ ሰንጣራው ምክንያት ባገኙት ላይ (በሀ/ስብከታቸው ሊቀ ጳጳስ ላይ ሳይቀር) እየመዘዙ የሚደነፉ ግልፍተኛ ናቸው፡፡

NebureEd Elias Abreha

የሹመት ተስፈኛው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ

ዝርዝሩ ለኋላ ይቆየንና ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ባለፉት ሦስት ቀናት በአቶ አባይ ፀሃየ ላይ አካሂደውታል በሚባለው ውትወታ÷ በፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ፣ የፓትርያሪኩ መጋቤ ሥርዐት (ፕሮቶኮል)፣ የመንበረ ፓትርያሪኩ(የግቢ) ጥበቃ ሓላፊ መኾን የሚገባቸውን ሰዎች መልምለውና አሳምነው እንደጨረሱ ከራሳቸው አንደበት በዛሬው ዕለት ሲነገር ተደምጧል፡፡ ካለፉት ኻያ ዓመታት ልምድ ለመገንዘብ እንደሚቻለው እኒህ የሓላፊነት ቦታዎች (በቀጣይ እስካልተስተካከሉ ድረስ)÷ ፓትርያሪኩን በመቆጣጠር፣ ባለጉዳዮችን በማጉላላትና የቤተ ዘመድ ሰንሰለት በመዘርጋት አስከፊ ሙስናና በቤተ ክርስቲያን ስም ሕገ ወጥ ተግባራት የሚፈጽምባቸው እንደነበሩ አሌ አይባልም፡፡

ለአስረጅነት እንዲኾንሙስናውም ከሕገ ወጥ ተግባሩም አብነት እንጥቀስ፡፡ ፓትርያሪኩ እንደተሾሙ ሰሞን ‹‹አላምዳለኹ፤ አማክራለኹ›› በሚል ተጠግተው ቢሯቸውን በዚያው በጽርሐ መንበረ ፓትርያሪኩ ያደረጉት ንቡረ እድ ኤልያስ በቤተ ክርስቲያኗ ስም በሚደረግ ትብብር ሁለት ሰዎችን ገንዘብ ተቀብለው ወደ አሜሪካ ለመላክ ያደረጉት ሙከራ ተይዞባቸዋል፡፡

በመለያ ስሙ ‹‹ሃይለ ሰይጣን›› የሚባለውና በቀድሞው ፓትርያሪክ እገዛ በዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሹመቶች የተደራረቡለት ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ከፓትርያሪኩ ምርጫ ወቅት ጀምሮ በአዲስ አበባ ይገኛል፡፡ ሃይለ ሰይጣን የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ በኾኑት አቡነ ገሪማ አማካይነት ከአዲሱ ፓትርያሪክ ጋራ ዕውቂያውንና መቀራረቡን ማጠናከሩ ይነገራል፡፡ የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ ኦርቶዶክሳዊነት በሌለው ፕሮቴስታንታዊ ማንነቱ ያገኘው ሕገ ወጥ ሹመት ኾኖ ሳለ፣ በልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ግንኙነት የበላይ ሓላፊው ሊቀ ጳጳስ አስፈጻሚነትና በእነ ንቡረ እድ አስተናባሪነት የቀድሞው የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ሠራተኞቻቸው የደከሙበትን ሀ/ስብከትና መንበረ ጵጵስና ሳይገባው ለመረከብ የሚያስችለውን ደብዳቤ ሰሞኑን አጽፎ ወደዚያው ለመብረር ተዘጋጅቷል፡፡

ሃይለ ሰይጣን ለመልስ ጉዞ ሲዘጋጅ የያዘው ሰለባ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በቆይታው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የታገደውንና ደርሶ ማኅበረ ቅዱሳንን እገዳደራለኹ ባዩን ‹‹የጉባኤ አርድእት›› ጉዳይ ከግንባር ቀደም የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆችና ሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋራ በመኾን ለማንቀሳቀስ መሞከሩ ተዘግቧል፡፡ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በአዲስ መልክ እንደተዘጋጀ በተገለጸው የሃይማኖት ማኅበራት ምዝገባ አዲስ አሠራር ፈቃድ አግኝቶ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከመሰሎቹ ጋራ ጅር ጅር ሲል ሰንብቶ ነው የሚሄ፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፡፡ ሰሞኑን ‹‹አባ›› ገብረ መድኅንና ፅልመታዊው ቡድን በሚያካሂዱት ውትወታ ታዲያ የውጭ ግንኙነት መመሪያውንና የልዩ ጽ/ቤት ሓላፊነቱን ጠቅልለው በመረከብ ይመራሉ የሚባሉት ‹‹ሰይጣንን በዘመን እንጂ በተንኰል እንደሚወዳደሩት›› የሚነገርላቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ናቸው፡፡ የፓትርያሪኩ መጋቤ ሥርዐት (ፕሮቶኮል) እንዲኾኑ አሳምኜ መልምያቸዋለኹ የሚሏቸው ደግሞ አቶ ተወልደ በኀይሉ የተባሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ አሁን በዜግነትና ኤሚግሬሽን ጉዳይ ሠራተኛ መኾናቸው ይነገራል፡፡ ግለሰቡ በ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ምልመላና ማግባባት የመንግሥት ሥራቸውን ለቀው የፓትርያሪኩ ፕሮቶኮል ለመኾን እንደተስማሙ ከራሳቸው ከአባ ገብረ መድኅን በዛሬው ዕለት ተሰምቷል፡፡ ሌላው የአባ ገብረ መድኅን ምልምል ለጊዜው ስማቸው ተለይቶ ያልተገለጸና በወቅቱ ግቢው ጥበቃ ሓላፊ አቶ ብርሃኔ ኀይሉ ላይ/ምትክ የሚሾሙ ሰው ናቸው፡፡

በ‹‹አባ›› ገብረ መድኅንና በጨለማው ቡድን ዕቅድ መሠረት፣ እኒህ ሦስት የሓላፊነት ቦታዎች ተይዘው ሲያበቁ በቀጣይ ካነጣጠሩባቸው የአስፈጻሚው አካል (የጠቅላይ ቤተ ክህነት) የሓላፊነት ቦታዎች አንዱ የበጀትና ሒሳብ መምሪያው ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በዚህ መምሪያ ላይ እየሠሩ የሚገኙት ሓላፊዎች የማኔጅመንትና አካውንቲንግ ሥልጡኖች ናቸው፡፡ ከትውፊታዊውም ከዘመናዊውም ትምህርት የሌሉበት እነአባ ገብረ መድኅን ግን እኒህን ባለሞያዎች አስወግደው በምትካቸውመመለስ የሚፈልጉት ገብረ መስቀል ድራር የተባሉ የአስተሳሰብና ተግባር መሰላቸውን ነው፡፡ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የበጀትና ፋይናንስ መመሪያ ከተነሡ በኋላ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የቁጥጥር ሓላፊው ገብረ መስቀል ድራር የሁለት ቪላዎች ባለቤት ከመኾናቸውም በላይ ለዓመታት ያካበቱት ገንዘብ ‹‹ባንኩን አጣቦታል›› በሚል ይወራባቸዋል፡፡

እንግዲህ እነ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን÷ ‹‹የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በትግራዎት እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ ለሚኒስትሮች የሚፈለገውን ጥቅም እያቀረብን እናስፈጽመዋለን›› የሚሉት በእኒህ ስንኩል ግለሰቦች በሚዘወሩ የቤተ ክህነቱ ከፍተኛ መዋቅሮች አማካይነት ነው፤ ትግራዎት በእኒህ የአስተሳሰብና የተግባር ስንኩላን ሊወከሉም ሊጠሩም አይችሉም፤ አይገባቸውም እንጂ!

የዜናው ምንጮች፣ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅንና የጨለማው ቡድን በዛሬው ዕለት አቶ ኣባይ ፀሃዬን ከፓትርያሪኩ ጋራ በማገናኘትና ፓትርያሪኩን በማግባባት ይህን ፍላጎታቸውን ከዳር ለማድረስ  ዕቅድ ነበራቸው፡፡ አልያዘላቸውም እንጂ!

በእነ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ፕሮግራም መሠረት፣ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ዛሬ፣ ሚያዝያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡15 ላይ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ ገብተው በደጃፉ ቆመው ወዲያ ወዲህ ሲሉ ታይተዋል፤ እየመሯቸው የገቡትም ሲወተውቷቸው የሰነበቱት ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ናቸው፡፡ አመጣጣቸው ግን በመንገደኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ቀጠሮ እንጂ እንደ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ወጉን (ፕሮቶኮሉን) የጠበቀ አልነበረምና የፈለጓቸውን ‹‹መመሪያ ተቀባይ›› አላገኟቸውም፤ ‹‹መመሪያ ተቀባዩም ለስብሰባ ወጥተው በቢሯቸው አልነበሩም፤›› ይላሉ ምንጮቹ፡፡ በርግጥ አቶ ኣባይ ‹‹መመሪያ ሊሰጧቸው ተዘጋጅተውባቸዋል›› በተባሉት ቅዱስነታቸው ምትክ እዚያው በቆሙበት በአልፎ ሂያጅ ካገኟቸው ሁለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ተቀብለዋል፡፡ ከዚህ በቀር ጨዎታቸው ከግቢው ጥበቃ አባላት ጋራ ነበርና ከቆይታ በኋላ በመጡበት አኳኋን ተመልሰዋል፡፡

ይህም ስለሆነ የስኳር ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ኣባይ በዛሬው  ዕለት ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ መጥተው ከደጃፍ ስለተመለሱበት ጉዳይ በግልጽ የተረጋገጠው፣ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በተመለደ ግልፍተኝነታቸው ድምፃቸውን አሰምተው ሲናገሩ ካደመጧቸው እማኞች ነው፡፡ እማኞቹ ለሐራዊ ምንጮች እንደመሰከሩት፣ ኣባይ ፀሃየ በዛሬው ዕለት ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ የመጡት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ መመሪያ ለመስጠት እንደነበር ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በበስጭት ተናግረዋል፡፡ በአጭሩ በብዙ እማኞች የተረጋገጠው  የትግራዎትን አስተሳሰብና ፍላጎት ፈጽሞ ሊወክልና ሊያስጠብቅ የማይችለው አሳፋሪና አሳዛየ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ቀጥተኛና አሳዛኝ አነጋገር የሚከተለው ይዘት ነበረው፡፡

‹‹ለፓትርያሪኩ አመራር ሊሰጡ ነበር የመጡት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ በኋላ በትግራዮች እንጂ በአማራ አትመራም፡፡ የፓትርያሪኩን ፕሮቶኮል በቅርቡ አስመጥቼ ጨርሻለኹ፡፡ የጥበቃ ሓላፊውንም አስመጥቼ ጨርሻለኹ፡፡ ከዚህ በኋላ በኣባይ ፀሃዬ መሪነት ቤተ ክርስቲያን ትመራለች፡፡ መንግሥት ኣባይን ከስኳር ኮርፖሬሽን በተጨማሪ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን በበላይነት እንዲመሩ ትእዛዝ ተላልፏል፡፡ የትግራይ ተወላጆች የግቢውን አመራር ሙሉ በሙሉ እንረከበዋለን፡፡››

Abune Matyas Coronation

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ

በዕሥራ ምእቱ መባቻ ሙስናን፣ የዘመድ አዝማድና ዐምባገነናዊ አስተዳደርን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለማስወገድ ተደርጎ የነበረው ትግል ብፁዓን አባቶችን በመከፋፈል፣ ከዚያም አልፎ በማንገላታት መምከኑን ያስታወሱ የዜናው ምንጮች ‹‹አሁን ደግሞ አቶ ኣባይ ምን ቀራቸው?›› በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ጉዳዩን መንግሥት፣ የቤተ ክርስቲያናችን ከፍተኛ አመራር ካህናትና ምእመናን ሁሉ የምር ሊያዝኑበት እንደሚገባም ያሳስባሉ፡፡

በርግጥ በሐራዊ ግምገማ፣ ፓትርያሪኩ በጨለማው ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ መደምደሙ ከጊዜው የቀደመ ይመስላል፡፡ ለምን? ፓትርያሪኩ  የቅ/ሲኖዶሱን አቋምና የቤተ ክህነቱን አሠራር በጣልቃ ገብነት የሚያበላሹትን ‹‹ድሮም አሁንም እቃወማለኹ›› ሲሉ አረጋግጠዋልና፡፡

‹‹ሰውን መጥላትም መውደድም የምንችለው በዘሩ ሳይሆን በግብሩ ነው፤ አንድ ሰው ሊመሰገንም፣ ሊሾምም ሊሻርም ሊወቀስም የሚገባው በጠባዩ፣ በግብረ ገብነቱ፣ በትምህርቱ ብቻ እየተመዘነ መኾን አለበት፤›› በማለት ጎጠኝነትን በዐደባባይ አውግዘዋልና፡፡

‹‹የተሟላና የተቃና ሥራ ለመሥራት ከሁሉ አስቀድሞ ብቃትና ጥራት ያለው ሥራ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ሰው በሰው ላይ መደራረብ ሳይሆን ትምህርትና ችሎታ ያለው፣ ለተመደበበት ሥራ የሚመጥን ሰው መቀመጥ አለበት፡፡ ለዚህች ታላቅ መንፈሳዊ ተቋም የሚመጥኑ ሰዎች መቀመጥ አለባቸው፡፡ ቅ/ሲኖዶስ ለዚህ ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ይሰጠዋል የሚል እምነት አለኝ፤›› በማለት ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ በማስቀመጥ ተቋማዊ ለውጡን ወደፊት ለማራመድ መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋልና!!

Advertisements

17 thoughts on “ሰበር ዜና – ‹‹ለፓትርያሪኩ መመሪያ ለመስጠት ተዘጋጅተዋል›› የተባሉት ኣባይ ፀሃየ ከደጅ ተመለሱ

 1. Mebrat April 19, 2013 at 5:19 am Reply

  ቤተክርስቲያን ትልቅ ፈተና ውስጥ ናት:: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስንም እነኝህ ሰዎች ክፉኛ ሊፈታተኗቸው ነው:: ለአባታችን ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጽናቱን ይስጣቸው:: ሁሉም ክርስትያን ግን ከሳቸው ጋ መሆኑን ቢያውቁት ጥሩ ነው:: በፈተናው ለመጽናት ይረዳቸዋልና:: ነፍሳቸውን ይማረውና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን የጠላናቸው ለቤተክርስቲያን የቆሙ ባለመሆናቸውና የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ የሆኑ ሰዎችን አሳልፈው ለጠላት ይሰጡ ስለነበር እንጂ ህዝበ ክርስቲያኑ ሁላችንም ለቤተክርስቲያን የቆመ አባት ካገኘን እስከሞት ድረስ ከጎኑ እንቆማለን:: ክርስቲያኑ የዘርና የጎጠኝነት ችግር የለበትም:: ሁሉም ክርስቲያን በዳግም ምጽአት ጊዜ በዘርና በቀለም መለያየት እንደሌለ አበጥሮ ያውቃል:: ፖለቲከኞቹ እንጂ ስለዘር የሚያናፍሱት ክርስቲያኑ ጋ ያ ችግር የለም:: ብጹዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ሆይ እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ለሐይማኖትዎ የቆሙ አባት ይሁኑ:: ያንን ሲያደርጉ በሰው ዘንድ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔርም የተመሰገኑ ይሆናሉ:: እግዚአብሔርም ኅይልና ብርታቱን ይሰጦታል::

 2. Anonymous April 19, 2013 at 5:49 am Reply

  መንግስት በቤተክርስቲያን ውስጥ ደም መፋሰሱን ለምን ፈለገ? መብረጃ ወደ ሌለው ጦርነት ለምን እንገባለን

 3. Anonymous April 19, 2013 at 5:56 am Reply

  silehulum geta yawqal.

 4. Anonymous April 19, 2013 at 6:50 am Reply

  Ere yitewun eneh seytanoch metegeya leyasatun new endie!!! Behagerachin baytewar mehonachin sayansen begeta betim dihoch leyaregun new? Ere geta tabezhen egna eqo bagerachin menorim mesededim alchalnim, kidist Ethiopia wohine honabinalech!!!

 5. geezonline April 19, 2013 at 1:09 pm Reply

  “ፓትርያሪኩ በጨለማው ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ እንደገቡ መደምደሙ ከጊዜው የቀደመ ይመስላል” ምን ማለት ነው? አዬ ሐራ! እናንተም ቀልድ ዘመም መኾናችኍ ነው ወይስ “ከጊዜው የቀደመ” የሚለው ዳኅፀ ታይፕ ነው (“የዘገየ” ለማለት ዐስባችኍ በታይፕ ስሕተት “የቀደመ” ብላችኹት ነውን)? ርሳቸውን መልምሎ የሾማቸው ማን ኾነና! ደግሞስ የጨለማው ቡድን ርስ በርሱ ቢፈረካከስ አንዱ ፍርካሽ ብርሃን የሚኾን መሰላችኍ? ከእሾኽ ወይን እንደማይለቀም ኹሉ ከኵርንችትም በለስ እንዳይገኝ እያወቅነው፦ ከንቱ ድካም። እሊህን እሾኾች እና ኵርንችቶች መንቀል ቢያቅት ባይኾን ውሃ ማጠጣት አይገባም። ይድረቁ።

 6. Ayalew Kerie April 19, 2013 at 1:54 pm Reply

  ቤተክርስቲያናችን ለማጥፋትና ስጋዊ ጥቅማቸዉን ለማጋበስ የሚተጉትን የበግለምድ ለባሽ ተኩላዎች ለማጋለጥ የምታደርጉትን ጥረት ቀጥሉበት! ለዚህም እግዚአብሄር ይርዳችሁ!

 7. muse April 19, 2013 at 2:10 pm Reply

  ይህ ዘገባ በኣንድ ብሔር (የትግራይ)ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ነው! ፈጽሞ የመንፈሳዊነት ሽታ የማይታይበት የፖሎቲካ ነክ ዘገባ ነው! ለዛውም የጨለምተኛ ዲያስፖራዎች ኣንደበት መሆኑ ቁልጭ ብሎ ይታያል!

  • mark April 21, 2013 at 10:06 am Reply

   ወንድም ሙሴ ዋናው ቊም ነገር የተጻፈው እውነት ነው ወይ ነው፣ የተጠቀሱት ሰዎች በዘራቸው ተሳስበው የቤተክህነትን ሀላፈነት ይዘዋል ወይ ነው፤ መንግስት ቤተ ክህነትን ያለ አግባብ በአንድ አካባቢ ሰዎች እንዲቆጣጠሩት ጫና ያረጋል ወይ ነው፤ ይህ ደግሞ ጸሀይ የሞቀው ሀቅ ነው የርሶም ልብ ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ አትናገሩ ከማለት እነ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን እና አቶ ኣባይን በስማችን አትነግዱ ማለት የክርስትያን ተግባር ይሆን ነበር

 8. dereje melaku April 20, 2013 at 12:29 pm Reply

  in order to abolished such kind of fascistic and evil action of the wouyane junta regime we have to united today not tomorrow god bless Ethiopia

 9. hara April 20, 2013 at 6:42 pm Reply

  How do you find when pop come for the second time from Tigrai?

 10. Anonymous April 22, 2013 at 8:39 am Reply

  ( Col. 2:13-15 ) Our problem is not with Satan, he has been defeated. The issue is our relationship with God, knowing who and what we are in Christ Jesus. Therefore, we are to keep the enemy from having any footholds through our prayers and directed actions as per the responses for our prayers!!!…in the Name of Jesus Christ and His Blessed St. Mary The Virgin and All His Saints, Let us UNITE we followers of Orthodox Tewahido and pray!…Let’s then FIGHT and DESTROY this “evil dark group” openly in the Name of The Almighty God for He is with Always us!…NOTHING CAN EVER LIMIT or DEFEAT US IN OUR LORD JESUS CHRIST!…WE SONS & DAUGHTERS OF ORTHODOX TEWAHIDO MUST PROCEED UNTIL VICTORY PREVAILS i.e. Until the works of the protestants and corruptors will cast down!!!….Hey, we Christians don’t believe in ETHINIC descrepancies NOR ANY DIFFERENCES..THAT IS THE BEST GIFT WE GOT FROM OUR LORD & BE PRIDE OF!!!…. In Christianity, THE IS NO PLACE FOR DISCREPANCY AMONG BELIEVERS, THERE ONLY EXISTS THE KINGDOM OF PEACE & JOY WITH “UNITY & HARMONY”!!…THIS IS JUST THE WORK OF SATAN!…NO CHRISTIAN SHALL FEEL PREJUDICES!!!….I TELL YOU, THIS IS THE WORK OF THE PROTESTANTS AND THE GOVERNMENT IN ORDER FOR US NOT TO UNITE AND LIVE A STRONG CHRISTIAN LIFE!…LET’S PRAY FOR OUR CHURCH, FOR OUR COUNTRY AND FOR OUR ‘PAPAS’!…AND LET’S SUPPORT AND UNITE EACH OF US DESPITE OUR ETHINIC DIFFERENCES…THIS A WORLDLY SLOGAN, NOT A GODLY COMMANDMENT!!! If such things are actually going on there, let’s unite and caste down these responsible personnels for they are not Christians!……One more thing, The government should put off his dictatory activities from us!!!..Let’s us live peacefully with our God, don’t come and disturb our emotional intimacy and safety!….you government officials MUST know your safe borders and shell…Please, be aware of your borders b/c you can’t rule the HEAVENLY KINGDOM!..i don’t have any political problem, but you see you are in the wrong place..you can live with your hethen philosophy just out side our church not inside unless you want to be TRUE followers of Orthodox Tewahido not missionaries of the protestants and your personal interests!!!… .MAY GOD BLESS ETHIOPIA & HIS FOLLOWERS, Amen!!!

 11. Anonymous April 22, 2013 at 1:57 pm Reply

  It is just a politics between you who badly want government and church power and others! ታገሉና አሸንፉ ስልጣን ታገኙ ይሆናል። የሚይሳዝነው ግን ቤተክርስቲያን የእንደናንተ ኣይነት የስልጣን ጥማተኛ ፖለቲከኞች መድረክ መሆኗና ያለባትን መንፈሳዊ የቤት ስራ መስራት አለመቻሏ ነው። ሌላው ቤተእምነት ግን—

 12. Ewunetu Yigeletal Gena gena April 22, 2013 at 3:39 pm Reply

  Guys, Please note that we have a very serious documentation. This article is not directly prepared by Mahibere Kidusan Council members. By the way “Hara Tewahedo” is sponsored by Abune Abrham and Abune Samuel. And, the writers are Alula and daniel Kibret, the former MK members and Maneyazizewal of Shewa. They intentionally run against the Tigray People. Moreover, this article is prepared by:
  1. Eskindir Gebrekirstos from betekihinet and his trash father (Like Tiguhan Gebrekirstos – he was a monk of EOTC and he is currently the father of 7 children including the evil Eskindir).
  2. Manayazizewal and Daniel Kibret was also involved. We will have enough explanation the reason behind this trash and false artilcle)

  We will write about Eskindir and his families who are currently working in EOTC (His father is working in Holy synod office, his mother is in Meskaye Hizunan, His brother is in Kiray Betoch, His Sister is in Yared church, His wife in in St. Michael church and other 12 cousines are also working in different parish churches of Addis Ababa Diocese). Wait the truth with documentation by Abab selama……..

 13. Anonymous April 23, 2013 at 7:47 am Reply

  Really how Ethiopia is becoming in trouble. Hearing those things is an agonizing for me…..

 14. Anonymous April 25, 2013 at 7:30 am Reply

  ፓትርያርክሽ እና መሪሽ ማን ነው?
  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሆይ የነጻነት ፤ የሰላም፤ የልማት፤ የጥበብ፤
  የፍልሰፍና የዕድገት፤ የሥነ ልቡና የኢኮኖሚና የአዲስ ነገር ሁሉ መገኛ የአፍሪካ እመቤት
  ነሽ፡፡ ይህንንም እነ ማንዴላ፤ ቸነዋ አቸቤ፤ ሄሮዶተስ እና አብርሃም ሊንከን
  ያውቁልሻል፡፡የሥልጣኔና የሥነ ጥበብ ፋና ወጊ መሆንሽን አፍሪካውያን እና የዓለም ሕዝቦች
  ሁሉ ያውቁታል፡፡
  ከአፍሪካ አገሮች ደግም በሁለንተናዊ እንቅስቃሴዋ በዕውቀት፤ በምርምር ፤ ፊደሎችን በራስ
  ልሳን አዘጋጅቶና ቀርጾ በማስተማር ቀዳሚውን ቦታ የምትይዘው ኢትዮጵያ ስትሆን
  የእንቅስቃሴዋ ምንጭ ደግሞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሆንዋ ነው፡፡
  ይህንን ተጨባጭ ታሪክ ዓለም እና አፍሪካ የሚያውቁት ጉዳይ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሆይ
  ለኢትዮጵያ ምድር እና ለሕዝቦቿ ሁሉ ታላቅ ባለውለታ ነሽ፡፡ የዕድሜ ባለ ጸጋዋ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ
  ሆይ መኩሪያ እና አለኝታችን፤ ማንነታችን የነጻነት አዋጅ አብሳሪዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ሁሉ እናት
  እና ከዓለም ሳይንቲስት እንድንቀላቀል ያደረግሽን አንቺኮ ነሽ፤ የዘር የቀለም ልዩነት ሳይኖር ሀ
  ፤ ሁ… ብለሽ የፊደል ገበታ ዘርግተሸ ያስተማርሽን የሰማንያ ሚሊዮን ልጆች እናት እና
  የአፍሪካውያን ሁሉ መመኪያ አንቺኮ ነሽ፤ ታዲያ እማማ ይህ ሁሉ ውለታሽ በምን ይሆን
  የሚመለሰው ? እረውለታውስ በቀረብሽ ለክብርሽ በቆምንልሽ ልጆች ወልደሽ እንዳልወለድሽ
  ሣር ና አራሙቻ፤ ሰርዶ እና ሰርሜዶ በቀለብሽ፡፡ጌታ ካላረመልሽ የለም እኮ የሚነቅልልሽ ቂጣ
  ጋግረሽ የጡትሽን ወተት ግተሽ ፤ ደክመሽ አሳድገሽ መልሱ ይህ ሆነልሽ ተይው እማማ ሆድ
  አይባስሽ የሰማንያ ሚሊየን ሕዝቦች እናት ነሽ፡፡ እረ ማን ነው ፓትርያርክሽ?
  ስላንች የሚያስብልሽ ወይስ የሚሸጥሽ? በሩቅ ቆሞ የሚያፌዝብሽ ቀርቦ ችግርሽን የሚፈታልሽ
  እረ ማን ነው ፓትርያርክሽ?
  ደፋ ቀና ብሎ ሚታዘዝሽ እስኪ በግልጽ ልጠይቅሽ ማን ነው ፓትርያርክሽ አባይ ፀሐየ ወይስ
  አባ ማትያስ? አንቺማ ምን ታውቂና ግንኮ ፓትርያርክሽ ማትያስ አይደለም፤የበረሃው ጊንጥ፤
  እፉኝት የሰይጣን ሸክላ ድብኝት አባይ ፀሐየ ነው ፓትርያርክሽ፡፡ በዝሙት መንፈስ
  ማሰልጠኛው የሰይጣንን ባንድ ያዋቀረው፤ የጨለማው ቡድን መሪ እሱ ነው ፓትርያርክሽ በይ
  በደንብ ተዋወቂው፡፡ እሱ ከሆነ የሚመራሽ እማማ ተጠንቀቂ ጡትሽን እንዳይነክስሽ ሰው
  ስለሆንኩ ይህንን አልኩሽ፤ ሁለን የሚያውቅ የፈጠረሽ፤ የገነባሽ አንድ ኃይል አለሽ፡ውሻው
  ጡትሽን ላይነክስሽ ኃይልሽ ኃይለኛ ነው፡፡
  መለጎሚያ እና መለበቢያ መቆለፊያም ቁልፍ አለው፡፡ ጭንቅላቱን የሚያደማው፤ ካንሰር ነው
  መጨረሻው የበሩ መዝጊያ መሎጊያው፡፡

  በአቶ አባይ ፀሐየ እየተመራች ያለችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወዴት እያመራች ነው? ታላቁን የቤ/ክ/
  አስተዳደር የተሸከማችሁ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሆይ ምን እየሰራችሁ ነው? ቤተ
  ክርስቲያኒቷ የነጻነት አዋጅ የታወጀባት እና የአፍሪካ ሥልጣኔ መሪ መሆንዋ እየታወቀ
  በሰይጣን ባንዳዎች እና በመሪያቸው አቶ አባይ ማንነቷን እና ክብሯን አጥታለች፡፡
  ታዲያ የእናንተ ዝምታ እና አድርባይነት እስከ መቼ ነው? አምላካዊ ሥልጣናችሁን ስትቀበሉ
  ዓለሙን ከድታችሁ፤ ራሳችሁን ገድላችሁ፤ ጥቅም እና ሥልጣን ሳይገዛችሁ ለአገር እና ለሕዝብ
  ለእውነት እና ለፍትሕ የቆማችሁ እንድትሆኑ ነበር፡፡ ግን ሕዝብ እና አገር ሰላም ሲያጣ ፍትሕ
  እና እውነት ሲጠፋ በናንተ በኩል ምላሽ አልተሰጠም፡፡
  ዝምታው ምንይሆ? ወይስ እንደተለ መደው የአባይ ፀሐየነ አፍራሽ መመሪያ እየጠበቃችሁ ነው?
  ብሎ ብሎ የፈነዳ እንደሆነ የምትመሩት ሕዝብ እሳት ሆኖ ያቃጥላችኋልና አድርባይነቱን
  ትታችሁ ለሐቅ እና ለቆማችሁበት ዓላማ ሥሩ፡፡ በናንተ ተባባሪነትም የበረሐው ዛር አባይ ፀሐየ
  ቤተ ክርስቲያኒቷን የቡና ማጠቢያ እና የጫት መጋዘን እንዳየደርጋት ተጠንቀቁ፡፡
  ደም የለመደው የበረሃው ዛር እና የደም ዝውውሩ በገሞራዊ ዝሙት ጠንቅ የተመረዘው፤
  ከማያቋርጥ በደሉ የተነሳ ከሟርተኛ ዓይኑ ደም የሚታለበው፤ መርዝ እንደበላ አይጥ
  በቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር የሚያቋንጠው አቶ አባይ ፀሐየ እንደ 2001 ዓ.ም በተለመደው
  ጨለማዊ ግብሩ ደማችሁን እንዳይጠጣው፡፡ አስተዳደራዊ በራችሁን በሕግና ሥርዓት
  ብትዘጉት መልካም ነው እንላለን፡፡የበረሐው ዛር እና ደም ቀለቡ የሆነው አባይ ፀሐየ በማንም
  የሃይማኖት ተቋም አይገባም፤ ተቋሞችም ደም አላቋደሱትም፤ በራቸውም በሕግ ቁልፍ የተቆለፈ
  ነው፡፡

  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕግ አላት ወይስ የላትም?
  የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሆይ ሕግ የሌለው አስተዳደር በር የሌለው ቤት ነውና ቤታችሁን በሕግ
  ዝጉት፡፡ በተከፈተ ቤት የሚገባ እና የሚወጣ አካል በሩ እስከተከፈተ ድረስ ሕገ ወጥ ሊባል
  አይችልም፡፡ በመሆኑም እንደነ አባይ ፀሐየ ያሉት ተልከስካሽ ዛሮች እና ደም የሚልሱ የእርድ
  ቦታ ውሻዎች በተለመደው ልክፍታቸው እንዳያሳብዷችሁ ከወዲሁ በራችሁን ዝጉ፡፡ ብፁዓን
  ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ በሥልጣናችሁ ብሔራዊና ዓለም አቀፋ ኅብረተስብ የሚያከብራችሁ፤
  የሚፈራችሁና ቦታ የሚሰጣችሁ ግዙፋን አካላት ናችሁ፡፡ ነገር ግን እንደነ አባይ ፀሐየ ያሉት
  ዓለም አቀፍ እና ብሄራዊ ሕገ መንግስት የማይገዛቸው ስውር ባንዳዎች በስማችሁ፤
  በሥልጣናችሁ እንደ ልጆች ጢባጢቤ ተጫወቱባችሁ፡፡እንደ ሕጻን ልጅም አታለሏችሁ፡፡ ታላቁ
  ክብራቸሁ በባንዳዎች እና ግብረ አበሮቻቸው የፖለቲካ ልብስ ተሸፍኖ በቆሻሻ መጣያ ገንዳ
  ተጣለ፤ ምዕመናን ልጆቻቸሁም አፈርንባችሁ፡፡ አባቶቻችን ሆይ በዓለም ላይ ከናንተ የበለጠ
  ተሰሚነት ያለው ዓለም አቀፍ ባለ ሥልጣን የለም፡፡ከሃምሳ በላይ ዓለም አቀፍ ጳጳሳት ይቅሩና

  አንድ ጠንካራ አባት ብቻ አንድን ሕገ ወጥ አካል በእንብርክኩ ሊያስኬደው ይችላል፤ ግን
  ፍርሃታችሁ፤ አድርባይነታችሁ የቤ/ክ መሪዎች ስትሆኑ አድራሻቸው በጉልህ ከማይታወቁ
  የፖለቲካ መሪዎች ጋር ተጣብቃችሁ መታየታችሁ አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ አዲሱና ባለታሪኩ
  ትውልድ ጊዜ ሲያልፍ ሊጠይቃችሁ እንደሚችል አውቃችሁ በማንም አሽሻም እና ሱሰኛ አካል
  ሳትመሩ ሕጋችሁን እና ማንነታችሁን ከምትመሩት ሕዝብ ጋር አስከብራችሁ ብትኖሩ መልካም
  ነው እንላለን፡፡
  እረ ለመሆኑ በ 2001 ዓ.ም በእናንተና በአባላቶቻችሁ ይደርስ የነበረውን ዛቻ፤ ድብደባና የቤተ
  ክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ ችግር እንዴት ረሳችሁት? ያን ችግር የፈጠረውስ አቶ አባይ ፀሐየ
  እንደነበረ አታስታውሱምን? አሁንም ቢሁን ይህ ግለሰብ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጀርባ መች ወረደ
  ያወጣችሁትን የፓትርያርክ ምርጫ ሕግስ የልጆች ዕቃ ዕቃ ጨዋታ አላደረገውምን?
  ክብራችሁ ወርዷል፤ ቀላችኋል፤ እባካችሁ ቢቻል ከፍ በሉልን ባይቻል ደገሞ ወደነበራችሁበት
  ቦታችሁ ተመለሱልን፡፡

  አቶ አባይ ፀሐየ ባህርይዎ ምንድን ነው?
  አንዳንዴ ቀጭን ጋቢ አገልድመው ሽማግሌ ይመስላሉ፤ አንዳንዴ እንደ መንግሥት ባለሥልጣን
  ይሆናሉ አንዳንዴ ደግሞ እንደ ሕጻን ስኳር ይልሳሉ አንቱ ወይስ አንተ ማን እንበልዎ ? መጥሪያ
  ስም አጣንልዎ፤ የድሮ አለቃዎ የእርሶን የልጅነት አይሉት የአዋቂነት ፀባይዎን ተረድተው
  የልጅነት ፀባይዎ በመረጋገጡ የስኳር ኃላፊ ሆነው ስኳር እንዲልሱ አድርገዎታል፡፡ ግና ጸሎት
  እና ሥጋ ወደሙ እንጂ የሚላስ ስኳር በሌላት ቤተ ክርስቲያን እየተሸከረከሩ መሞዳሞድዎ
  ለምን ይሆን? ይስሙኝ ልንገርዎት የቤተ ክርሰቲያን ገንዘብ እና ጥይት አንድ ናቸው፤ ወደ ውስጥ
  ሲገቡ አይታወቁም ሲወጡ ግን አካል ገላን ቦድሰው ይወጣሉና ለእርሶና ለቤተሰብዎ መርዝ
  አብልተው ባይገሏቸው ምናለ! ቤተሰብዎ ክርስቲያን ነው ይባላል እርሶ ግን የክርስትና ምንጭ
  የሆነችውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ገልብጠው ሊጥሏት እና ያን በበረሃው የመከሩትን ዕቅድ
  ለመተግበር ይሯሯጣሉ፤ ግን ዕድሜዎን ያሳጥራሉ እንጂ ምንም ሊያደርጉ አይችሉም፡፡
  አቶ አባይ በእግዚአብሔር ሀብት ላይ መቀለድ በሾለ ብረት ላይ በባዶ እግር መቆም ማለት
  ነውና ጠንቅቀ ቢሉ መልካም ነው፤ ግን በእርሶ ምን ይፈረዳል እርሶና ድርጅቶ እንጂ
  እግዚአብሔር መሣርያ፤ ጥይትና ሚሳየል የለው ቢኖረውስ እርሶን አያገኝዎት¡ በሠራዊት
  ታጅበው ሞት መች ደፍሮት¡ እርሶ እንደሆን ከእግዚአብሔር በላይ ነኝ ብለው ያስባሉ ግን
  እኮ ሞኝ ነዎት መቀበሪያዎን አፈረሷት፡፡ የእናትዎን አጽም ቆፍረው አውጥተው መድፍን
  ሊያደርጉት ታጠኑት አባዜዎ ምን ይበዛ! የበደል ጭልፋዎ መስፋቱ፡፡

  ኢህአዴግ እና ሕገ መንግሥቱ
  ለነጻነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለመብት ታገልኩ የሚለው የእነ አቶ አባይ ፀሐየ ሕገ መንግሥታዊ
  ቅዠት መጨረሻው ምን ይሆን? በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ የተደራጀው የጨለማው ቡድንስ የት
  ይሆን የሚገባው? ለመሆኑ ሕገ መንግሥቱ ለኢህአዴግ ኣባላት መብት ማስከበር የቆመ ወይስ
  ለመላው የአገሪቱ ሕዝብ? ሕጉ ዜጎቹን ሁሉ ሲገዛ አባይ ፀሐየ እና የጨለማው ቡድን ከሕገ
  መንግሥቱ በላይ የመሆናቸው ምስጢር ምን ይሖን? መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ
  እንደማይገባ በሕገ መንግሥቱ ተደንግጓል በአባይ ፀሐየ እና በጨለማው ቡድናቸው ግን
  ተሽሯል፡፡አባይ ፀሐየ በሃይማኖት ጣልቃ ይገባል፤ መንግሥትና ሲኖዶስ ሳያውቀው አዲስ
  ፓትርያርክ እንዲሾም አድርጓል፤፡ይህም በቤተ ክርስቲያኒቷ የጨለማው ቡድን በሚሰጠው
  መመሪያ መሠረት ነው፡፡

  ብሔር ብሔረሰቦች እና እንቆቅልሹ
  በብሔር ብሔረሰቦች መካከል እኩልነት አለ የሚለው የእነ አባይ ፀሐየ ቡድናዊ ወሬ ከጽሑፍ እና
  ከሚዲያ ያላለፈ አሉቧልታ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ይልቁንም ለፖለቲካ አንጃነት
  የሚፈልጓቸውን ለመመልመል የሚጠቀሙበተት ዘዴ እንጂ እኩልነት ፈጽሞ የሚታሰብ
  አይደለም፡፡ሌላው ይቅርና በትግራይ ክልል እንኳ የአንድ ወረዳ የበላይነት ብቻ የሚንፀባርቅበት
  ብልሹ ፖለቲካ ነው፡፡መብታችን ተጣሰ የሚል ጥያቄ ሲነሳ ለእኩይ ተግባሩ ማስፈፀሚያ
  እንዲሆኑ በመለመላቸው የእነ ኤልዛቤል ጽልመታዊ ቡድን እና የአባይ ፀሐየን ፍርፋሪ
  የሚለቃቅሙ የደኅንነት አባላት ነን በሚሉ ጥቋቁር ውሾች ከመነከስ ውጪ የሰዎች ጥያቄ
  ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ሲፈታ አይታይም፤፡፡ ለምሳሌ፡- ሰሞኑን በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ
  ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ድርጊት ይህንን የሚያሳይ ትልቅ መረጃ ነው፡፡
  የተማሪዎች የመብት ጥያቄው እና የኮሌጁ ብልሹ አሰራር ይፋ እንዳይወጣ እነ አቶ አባይ ፀሐየ
  እና ቡድናቸው የተማሪዎች ችግር ይፈታ ማለት ሲገባቸው በተቃራኒ ጀርባቸው ይጠና እያሉ
  ያስወሩ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ማንም ሰው ከወንጀል ሥራ ውጪ
  የፈለገውን መደገፍ እና ማድረግ ይችላል፡፡ ጭፍን ተልዕኮ ያላቸው አባይ ፀሐየ እና
  ሰይጣናዊው የጨለማው ቡድናቸው በተራራና በሸጥ የተከለለ ቡድናዊ ሥራ ሲሰሩ ሰንብተዋል፡፡
  ተማሪውንም በማስራብ ብሔራዊ ፍቅር እንዳይኖረው አድርገዋል፡፡
  የተወሰኑ ደህንነት ነን ባዮችም የአባ ጢሞቴዎስን ፍርፋሪ እየለቃቀሙ እና በገንዘብ እየተገዙ
  ተማሪዎቸን ያሸብሩ ነበር፡፡ እንዲሁም በወረዳ 09 ባለው ፖሊስ ጣቢያ የሚሰሩት ኮማንደር
  ኃይሉ እና የሚያዝዟቸው ፖሊሶች ርሀብ አንጀቱን ባቆራመደው ተማሪ ሞራል ላይ ሲረማመዱ
  ሰንብተዋል፡፡

  ኢህአዴግ እና የአባላቱ ጥቅም
  ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው የኢህአዴግ አባላት ቢዘርፉ፤ ቢሰርቁ ፤ ቢደበድቡ፤
  ቢያስሩ እና ሰው ቢገደሉ ማንም አይነካቸውም፡፡ በቅድስት ሥላሴ ኮሌጅም ለሁለት ግለሰቦች
  ብቻ ሲባል የቤተ ክርስቲያኒቷን እና የአገር ተረካቢውን ትውልድ በረሐብ መቅጣት የኢህአዴግ
  አባዜ ዋነኛ ምልክት ነው፡፡ በዋናው መሥሪያ ቤት በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በአባይ ፀሐየ
  ስውር የአባልነት ካርድ የተሰጣቸው እነ አቶ እስክንድር፤ እነ አቶ ተስፋየ እና አቶ አሰፋ
  አባልነታቸውን ተጠቅመው ቤተ ክርስቲያኒቷን እያመሷት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ቤተ ክርሰቲያኒቷ
  የማታውቃቸው አቶዎች ጥልቅ የፖለቲካ ታማኝነት ስላላቸው ብቻ ባልዋሉበት እና
  በማይመለከታቸው ቦታና የሥራ ዘርፍ ገብተው ቤተ ክርስቲያኒቷን ባልተወለደ አንጀታቸው
  እየዘረፏት ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩልም የኢህአዴግ የ2005 ዕጩ ተመራጭ ንቡረ እድ ኤልያስ
  አብርሃ የተባለው የጨለማው ቡድን የቀኝ ክንፍ የእነዚህ አንጃወች መልማይ እና የቤተ
  ክርስቲያኒቱ ሀብት እና ንብረት በእነዚህ አቶዎች እንዲዘረፍ መንገድ በማመቻቸት ከፍተኛ
  አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ አቶ አሰፋ የተባለው ግለሰብ ደግሞ በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ይሰራ
  የነበረ እና በአሁኑ ሰዓት ቤተ ክርስቲያኒቷን እየዘረፈ ያለ የሰይጣን ፖስታ አመላላሽ ነው፡፡

  የአባ ማትያስ ምርጫ
  በኢህአዴግ የተፈጸመ ቆሻሻና የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖናዊ ታሪክ ያበላሸ ምርጫ
  ነበር፡፡ ኢህአዴግ ቤተ ክርስቲያኒቷን የማዳከም እስትራቴጂውን ለማስፈጸም ዕቃ መምረጥ ስለ
  ነበረበት የኢየሩሳሌሙን የበርገር መጋገርያ ዕቃ በዕቃ መጫኛ አውሮፕላን ጭኖ ኢትዮጵያ
  ውስጥ አስገብቶታል፡፡ ይህም ኢህአዴግ ከደርግ መውደቅ ማግስት ያቀደውን
  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን የማውደም ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በአቶ አባይ ፀሐየ አቀንቃኝነት
  እና የ 7 ልጆች አባት በሆነው በአባ ጢሞቴዎስ አጨብጫቢነት የማውደሚያ ዕቃው ከኢየሩሳሌም
  ተጭኖ መጥቶ በሟቹ በአባ ጳውሎስ መኝታ ቤት ተዘርግፏል፡፡ ዕቃ ብለን የገለጽነው ይህ ሰው
  የሥራ ልምድና ብቃት የሌለው ግዑዝ አካል ነው፡፡ በቅርቡ የቅድስት ሥላሴ ተማሪዎችን ቀላል
  ጉዳይ ከመፍታት ይልቅ መሸሽንና መደበቅን እንደ ትልቅ አማራጭ ተጠቅሞታል፡፡ ይህ
  ሰው አዲስ አበባ ቀዳሽ በነበረበት ሰዓት ሰሞነኛ እንጂ ሌላ ያልሰራ እና ኢየሩሳሌምም ሄዶ
  ሥራውን በአግባቡ ባለመስራቱ የተነሳ ከመነኮሳቱ ጋር ተጣልቶ ወደ እንግሊዝ አገር መኮብለሉ
  የሰውየውን ብቁ አለመሆን የሚያወሳ ነው፡፡
  በአጠቃላይ በ 35 የጵጵስና ዓመታት የሚጨበጥ ሥራ የልሰራ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ በቤተ
  ክርስቲያኒቷ የጨለማ ቡድን እና በእነ አቶ አባይ መልማይነት በቤተ ክርስቲያኒቷ ጫንቃ ላይ
  ከባድና የማይወርድ ቀንበር ተጥሎባታል፡፡ይህን ሰው በቀላሉ ስንመለከተው የተማሪዎችን ቀላል
  ችግር አለመፍታቱ ማንነቱንና አቅሙን ግልጽ ያደርገዋል፡፡

  የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በቤተ ክርስቲያናችን ሲፈተሽ
  በዚህ ሚኒስቴር በኩል እየወጣ ያለው ሕግ ጥንታዊቷን እና ታሪካዊቷን ቤተ ክርስቲያንን
  የሚያዳክም የፕሮቴስታንቲዝም አባዜ ያለበት ስውር ደባ ነው፡፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያኒቱን
  ለመበታተን ሆን ተብሎ የተሰራ ታሪክ አልባ አጀንዳ መሆኑን ሕዝቡ በደንብ ሊያውቀው
  ይገባል፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን ሃይማኖት መከተል ይችላል፤ ነገር ግን ጥንታዊቷን
  ቤተ ክርስቲያን ለመበታተን መሞከርና በበረሃ ሳላችሁ ያቀዳችሁትን ቤተ ክርስቲያኒቷን
  የማፍረስ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ መሞከር ዓለም አቀፍ ሕገ ወጥ ተግባር ከመሆኑም በላይ
  ሕዝቡን እና ምድሪቱን የደም ቀየ እንዳታደርጉት ተጠንቀቁ፡፡ አባ ማትያስን ያመጣችሁበት
  ምክንያትም ይህን ደንባራ ዕቅዳችሁ ለማስፈጸም እንደሆነ የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች በሙሉ
  እንገነዘበዋለን፡፡
  ግራ የሚያጋባው የኢህአዴግ አመራር
  የፖለቲካ ወይስ የሃይማኖት አመራር ? ሚኒስትሮች የ 5 ዓመት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
  ለማስፈጸም ወይስ ፕሮቴስታንቲዝምን የማስፋፋት ሥራ መሥራት? ስንት ሚኒስትሮች
  በፕሮቴስታንት ተሰበኩ፤ ስንት ዴኤታዎችስ ለፕሮቴስታንቲዝም ስብከት ተመለመሉ? በሃገሪቱ
  ከ 40 ፐርሰንት በላይ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ምርጫ
  የፖለቲካ ሽፋን ሲሆን መራጩ ደግሞ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አባል ይሁን እንጂ ተመራጩና
  ሥልጣን የሚይዘው ግን የሌላ እምነት ተከታይ መሆኑ ለምን ይሆን?
  ነገሩ እንዲህ ነው የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ ያ አሜሪካዊ ሚሽነሪ በታሪክና በሃይማኖት የዘመተው
  ያ ጠማማ ሰው የሰጣችሁን የጥናታዊ ጽሁፍ ስትራቴጂን እያስፈጸማችሁ መሆኑን እናውቃለን፡፡
  ለዚህም የቤተ ክርስቲያኒቷን ሃይማኖታዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ሰላማዊ ሥራዋን ለማሽመድመድ
  ግዑዝ አካል የሆነውን አባ ማትያስን በፓትርያርክነት አስቀመጣቸው፡፡
  የበረሃው ዛር አባይ ፀሐየም የኮሚኒስት አራማጅ እንደነበርህ ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም
  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን ለማውደም ወደ ኋላ የማትል መርዘኛ እና ጠንቀኛ ሰው መሆንህን የቤተ
  ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ሁሉ በደንብ አውቀውሃል እና ለዘርህ ርስት፤ ለነፍስህ ዕረፍት
  እንዳታጣ፡፡ የምታምነው የለህም እንጂ ካለህ በምታምነው ብለህ ከቤተ ክርስቲያን
  ጫንቃ ላይ ውረድ፡፡ ግን አንተ ምን ገዶህ ስትኖር በጠመንጃ ስትሞትም በጠመንጃ ፡፡ የቤተ
  ክርስቲያን የአባልነት ግዴታህን ሳትወጣ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ በማታውቃት ቤተ ክርስቲያን
  ክርስቲያን ነኝ ብለህ ሳይሆን የክርስቲያን ዘር ነኝ ብለህ ባቃጠልካት ቤተ ክርስተያን ሥጋህ
  ይቀበርባት ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጪ እንዳልሆንህም ጠንቅቀህ ታውቃለህ ፡፡ አቶ አባይ
  ፀሐየ በከባድ በሽታ በሚሰቃየው አካልህ እና ነገ እና ከነገ በስቲያ አፈር በሚሆነው ገላህ የማይሞት
  እና ዘላለም ሊኖር የሚችል በደል እንደፈጸምህ እንዳትሄድ አመፀኛው እጅህን እና እግርህን
  ከቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ አውርድ፡፡ ይህ ካለሆነ ግን እፍ የማይባል እሳት ይበላሃል፡፡(ኢዮ 20)

  አቶ አባይ ፀሐየ በድርጅታችሁ ራዕይ መጽሔት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያንን መግደል እና መተቸት
  ዋናው ተግባራችሁ መሆኑን እናውቃለን፡፡ በሌላ በኩል ለእስላም የሸሪያ ፍርድ ቤቶች በየዓመቱ
  አንድ መቶ ሚሊዮን እና ከዚያ በላይ ገንዘብ ስትመድቡ ፊደል ቀርጻ አፋችሁን እንድትፈቱ
  ያደረገቻችሁን ቤተ ክርስቲያን ለማፍረስ መመካከራችሁ እጅግ በጣም ያሳዝናል፡፡ ሆኖም
  እናንተ ትፈርሳላችሁ እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ አትፈርስም፡፡ በጦር አውድማ ሳላችሁ በእናንተ
  ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቷ ተቃጥላለች፤ ቦንብ እና ሚሳኤል ፈንድቶባታል፡፡ እናታችሁ እና
  ባለ ውለታችሁ ነበረች፡፡ ግና ጡቷን እየጠባችሁ እድጋችሁ አናውቅሽም አላችኋት፡፡
  አባ እስጢፋኖስ እና ሙሰኛው ተስፋየ
  የጅማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ ከየካቲት 18/05 ዓ.ም እስከ የካቲት 24/05 ዓ.ም በኢትዮጵያ
  ሕዝብ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ የሰሩት ግፍ እና በደልዎ ሳያንስዎ አሁን ደግሞ ከእነ አቶ ተስፋየ
  እና መሰሎቹ ጋር ምን እያደረጉ እንደሆነ ተገንዝበዋል? አዎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ገመና ለባዕድ
  አሳልፎ ላለመስጠት እያልን እንጂ ስለ እርሶ የማናውቅው አንድም ምስጢር የለም፤ ጉድዎ ከባህር
  አሸዋ የበዛ ነው፡፡ በሲ ኤም ሲ (cmc) አካባቢ ያለውን የክተት ጦር ማሰልጠኛዎን እናውቀዋለን፤
  ድብቅ ጦረኛ እና አባት መሳይ ዘላን ሰው ነዎት፡፡ ይልቁንም እንምከርዎ ለአደጋ እንዳይጋለጡ
  ይጠንቀቁ፡፡ አሁን የሚያደርጉት ስውር አጀንዳዎን ከሚያዝያ 01/05 ዓ.ም ጀምሮ ካላቆሙ ሙሉ
  በሙሉ የጦረኛነት መረጃዎን እውነተኛ አባት መስለውት ከእግርዎ ሥር ወድቆ ጉልበትዎን
  ለሚስመው የጅማ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንለቃለን፡፡
  አቶ አባይ ፀሐየ እና ቡድንዎ፤ አቶ ተስፋየ እና ጨለምተኛው ጓዝዎ እንዲሁም አቡነ
  እስጢፋኖስ ከነ ጀሌዎ ሁላችሁንም እግዚአብሔር በፍርድ ወንበሩ ፊት እስከሚያቆማችሁ እና
  ጽዋችሁ እስኪሞላ በአመጻችሁ ቀጥሉበት¡ ከሆነላችሁ ቅበሯት አጽሟ እሾህ ሆኖ ካልወጋችሁ
  ይሉኝታማ የላችሁም፡፡ በጨው ዓይናችሁን አጥባችሁ በየዋሁ ሕዝብ ስትቀልዱ እስከ የት
  ይሆን ጉዟችሁ? አንድ ቀን ግን ታርፋላችሁ፤ዶግ አመድ ተሆናላችሁ፡፡

 15. Anonymous September 6, 2013 at 10:36 pm Reply

  eneas min serawu. weyewu lenea. yih hulu yemihonewu benea yetenesa yihon. amilakea

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: