የኮሌጁ የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን እንዲለቁ ታዘዙ

 • መንሥኤው ‹‹ትምህርት በአግባቡ አልጀመራችኹም›› የሚል ነው
 • ‹‹ማስታወቂያው ለብቀላና እስር ሰበብ መፈለጊያ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ከዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ የኮሌጁን ንብረት እያስረከቡ ኮሌጁን እንዲለቁ አሳሰበ፡፡ ኮሌጁ ማሳሰቢያውን በዛሬው ዕለት በቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርቱ ላይ ያወጣው ‹‹ያቋረጣችኹትን ትምህርት አግባብነት ባለው መንገድ አልጀመራችኹም›› በሚል ነው፡፡

Holy Trinity College Academic Programs

የኮሌጁ የትምህርት መርሐ ግብር

ከድኅረ ምረቃና ከማታው ተከታታይ መርሐ ግብሮች በቀር የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር ‹‹ትምህርት በአግባቡ አልጀመራችኹም›› በሚል ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን መጋቢት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ያወጣውን ማስታወቂያ የጠቀሰው የዛሬው የኮሌጁ ማሳሰቢያ÷ ኮሌጁ ‹‹ለሰላም ባለው ጽኑ ፍላጎት ያቋረጣችኹትን ትምህርት ትቀጥላላችኹ›› በሚል እሳቤ እስከ ዛሬ ድረስ ‹ በትዕግሥት ቢጠብቅም ተግባራዊ ባለመደረጉ››  የቀኑ መርሐ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ የተዘጋ መኾኑንና ደቀ መዛሙርቱ የኮሌጁን ንብረት እያስረከቡ ኮሌጁን እንዲለቁ አስታውቋል፡፡

ጥያቄ ያቀረቡባቸው ሁለት የኮሌጁ ሓላፊዎች ከያዟቸው ተደራራቢ ኮርሶች በቀር ትምህርታቸውን በዛሬው ዕለት ጭምር መቀጠላቸውን የተናገሩ ደቀ መዛሙርት በበኩላቸው÷ ውዝግቡን የሚያጣራ የጋራ ኮሚቴ በተቋቋመበት ኹኔታ የወጣው የዛሬው የኮሌጁ የልቀቁ ማስታወቂያ ተማሪውን ለመበቀልና ለማሳሰር ምክንያት የሚፈለግበት የጥቂት ሓላፊዎች ፍላጎት መኾኑን ተናግረዋል፡፡

አንድ የውጭ መምህር እንዳያስተምር በዛሬው ዕለት መታገዱን የተናገሩ ሌላው የኮሌጁ መምህር፣ መርሐ ግብሩ ያለቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ማንም እንደፈለገ ሊዘጋው እንደማይችልና ርምጃውን እንደሚቃወሙ ገልጸዋል፡፡

ኮሌጁ በመደበኛው የቀን መርሐ ግብር 181 መደበኛና ስምንት ተመላላሽ ደቀ መዛሙርት አሉት፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የኮሌጁ የቀን መደበኛ ደቀ መዛሙርት ኮሌጁን እንዲለቁ ታዘዙ

 1. Anonymous April 9, 2013 at 8:06 am Reply

  የአቡነ ጢሞቴዎስና እና የዘላለም ረድኤት ቁርኝት ምስጢር ምን ይሆን?

  በጣም የሚያሳዝነው ነገር ይህን ኮሌጅ አቡነ ጢሞቴዎስ ከገደሉት ቆይተዋል አሁን በይፋ በማን አለብኝነት አወጡት እንጂ፡፡ አሁንም ከታማኝ ምንጭ ነው የምላችሁ ከፕሮቴስታንት ተሐድሶ ድርጅት በሚፈሰው ገንዘብ በዘላለም ረድኤት እና በመሰሎቹ አቡነ ጢሞቴዎስን ይዘው ኮሌጁን እያሽከረከሩት ይገኛሉ፡፡ አሁን እርሱን አትንኩብኝ ነው የሚሉት ምስጢሩን እግዚአብሔር ይፍታው፡፡ ይህን የምጽፈው የቤትህ ቅናት በላኝ እንዳለ ቅዱስ ዳዊት ተማሪዎች ሲበደሉ ኮሌጁ የበላይ እንደሌለው ማለትም ሲኖዶስ እንደማይመለከተው ስለመሰለ ነው፡፡ አቡነ ጢሞቴዎስ ገንዘብ ከሰጧቸው ቤተ ክርስቲያንን ከመሸጥ ወደ ኋላ የማይሉ ናቸው፤ ስለማውቅ ነው የምነግራችሁ፡፡ ከሁን በፊት የሆነውን ሁሉ እናገር ነበር ነገር ግን ለቤተ ክርስቲያን ስለማይጠቅም ለጊዜው እተወዋለሁ፡፡

  አሁንም በጣም የሚያሳዝነው ነገር መምህራን እናስተምራለን እያሉ ተማሪዎቹም በሰላም እየተማሩ እያለ ህልሙ እውን አልሆን ያለው መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በመጀመሪያ ባለፈው ሳምንት ያለ አቡነ ጢሞቴዎስ ፊርማና ቲተር ኮሌጁ ተዘግቷል ብሎ ለጥፎ ነበር፡፡ አሁን ግን እርሳቸውን አስፈርሞ ለጥፏል፡፡ከንቱ ድካም ተማሪዎች ዝም ብላችሁ ተማሩ አስተማማዎችም ዝም ብላችሁ አስተምሩ እነዚህ የፕሮቴስታንት ገንዘብ ያሰከራቸው የሚሠሩትን አያውቁትም፡፡

  የማስተርሱ እና የማታውን ትምህርት ያልዘጉት ብር ስለሚያገኙበት ነው፡፡ የብር ነገር አይሆንላቸውና፡፡

  ማስተርሱ

  የሚቀበሉት ብር ከአንድ ተማሪ የሚቀበሉት ብር 45ዐዐ ብር ነው ነገር ግን የሚያስተምሩት አስተማሪዎች ሆድ ይፍጀው፡፡ አንዱም ዘላለም ረድኤት ነው እርሱ የዲግሪ ተማሪዎች አይመጥነንም አስተማሪ ይለወጥልን እየሞትን ነው እንጂ እውቀት እያገኘን አይደለም ቤተ ክርስቲያን ኪሣራ ላይ እየወደቀች ነው ተምረን በገንዘቡ እያስተማረን የሚጠብቀንን ሕዝባችንን ካላገለገልን ከየሀገረ ስብከታችን በስማችን የሚላከው ብር እየባከነ ነው ብለው ይቀየርልን ብለው ጥያቄ ያቀረቡበትን ዘላለም ረድኤትን በሚገርም ሁኔታ የማስተርስ አስተማሪ አድርገውታል፡፡

  የሚገርመው በዚህ መርሃ ግብር አብዛኛው የኮሌጁ አስተማሪዎች ናቸው የተወሰኑት እርሱን ያስተማሩት መምህራን ናቸው፡፡ ሞራላቸው እንኳን አልተጠበቀላቸውም፡፡

  አዲሱ ፖትርያርክም ከአቡነ ጢሞቴዎስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከቤተ ክርስቲያን አኳያ እየመረመሩ እስከ አሁን እንደሚያደርጉት አካሄድ በራሳቸው አካሄድ መሄድ አለባቸው፡፡ ይኸውም መፍትሔው አቡነ ጢሞቴዎስ ይነሱ ሁለቱ መምህራን ይነሱ፡፡

 2. Gebrekidan April 9, 2013 at 8:09 am Reply

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: