የኮሌጁ አስተዳደር የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን አስታወቀ

 • ማስታወቂያው የተለጠፈው በመርሐ ግብሩ አስተባባሪ ዘላለም ረድኤት ነው
 • ደቀ መዛሙርቱ በተቃውሟቸው ለመቀጠል በመስማማት ትምህርት ጀምረዋል
 • ‹‹ሲያስወጡን እንተናነቃለን፤ ኮሌጁን ቅ/ሲኖዶስ እንጂ ዘላለም አይዘጋውም›› /ደቀ መዛሙርቱ
 • የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ‹‹[ለደቀ መዛሙርቱ] እንኳን ምሳ ራት አልሰጥም›› እያሉ ነው

ሙስናንና የአሠራር ብልሹነትን በመቃወም ከሁለት ሳምንት በላይ በተቃውሞ የሰነበቱት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት በትላንትናው ዕለት ረፋድና ከሰዓት በኋላ በክፍል በመገኘት ትምህርት ጀምረዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ትምህርት በማቋረጥና በካፊቴሪያው ከመመገብ በመከልከል በኮሌጁ እየከፋ የመጣው ሙስናና የአሠራር ብልሹነት እንዲስተካከል፣ ለዚህም ተጠያቂ ናቸው ያሏቸው ሁለት ሓላፊዎች ከቦታቸው እንዲነሡ ያቀረቡትን ጥያቄ እየተማሩም ለመቀጠል በመወሰን ነው ትምህርታቸውን ለመጀመር የተስማሙት፡፡

በቀጣይ በሚቋቋመው ኮሚቴ መሠረት በሁለቱ ሓላፊዎች ላይ የቀረቡት ጥያቄዎች በሚገባ ተጠንተው ውሳኔ እንዲሰጥባቸው በፓትርያሪኩ የተሰጠውን መመሪያ መቀበላቸውን የተናገሩት ደቀ መዛሙርቱ÷ ሁለቱ ሓላፊዎች ማለትም የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪ መ/ር ዘላለም ረድኤት እና አካዳሚክ ምክትል ዲኑ መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ በክፍል ተገኝተው ማስተማራቸውን እንደሚቃወሙና ይህም ተቃውሞ ሓላፊዎቹ ውሳኔ እስኪሰጥባቸው ድረስ እንደሚቀጥል በመስማማት ነው ትምህርታቸውን የጀመሩት፡፡

ደቀ መዛሙርቱ የደረሱበት ውሳኔና ወደ ትምህርት የተመለሱበት ኹኔታ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ ይበልጥ እንደሚያጠናክረው የሰጉት የቀን መርሐ ግብር አስተባባሪው መ/ር ዘላለም ረድኤት ግን ከመማር ማስተማሩ ጤናማነት ይልቅ በቀጣይ የደቀ መዛሙርቱ የተቃውሞ ስልት ግላዊ ጥቅማቸው አደጋ ውስጥ መግባቱን በማሰብ ውዝግቡን የሚያባብስ ርምጃ መውሰድን መምረጣቸው ተመልክቷል፡፡ በተካኑበት አሳባቂነትና ነገር ሠሪነት የኮሌጁን መምህራንና አስተዳደር እርስ በርስ በማተራመስ፣ ከሰሞኑ እንኳ ተቃውሞ ያነሡባቸውን ደቀ መዛሙርት ሳይቀር በጥቅም ለመከፋፈል እስከመሞከር የሚታወቁት አስተባባሪው÷ የኮሌጁን የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ በማሳሳት በትላንትናው ዕለት ባወጡት ማስታወቂያ፣ በተቃውሞ የሰነበቱት የቀኑ መደበኛ መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት በዕለቱ እስከ ቀኑ 8፡00 ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የኮሌጁን ፕሮቶኮል ሳያሟላ የወጣው ይኸው ማስታወቂያው÷ ደቀ መዛሙርቱ በትምህርት ገበታ ያልተገኙበትን ኹኔታ በመጥቀስ በዚህ ሳቢያ ኮሌጁ ለኪሳራ መዳረጉን፣ የቀኑ መርሐ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱንና ኮሌጁ የሚያተስናግደው የድኅረ ምረቃና የተከታታይ(የማታ) መርሐ ግብር ተማሪዎችን በመኾኑ ደቀ መዛሙርቱ እስከ ቀኑ ስምንት ሰዓት ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስብ ነው ተብሏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ትምህርት ገበታ በተመለሱበትና የመማር ማስተማሩ ሥርዐት በቀጠለበት ኹኔታ አስተባባሪው ያወጡት ይኸው ማሳሰቢያ መምህራኑን አስቆጥቷል፤ ደቀ መዛሙርቱን ግራ አጋብቷል፡፡

ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን ጋራ በመተባበር ደቀ መዛሙርቱ ትምህርታቸውን እየቀጠሉና እየተመገቡ ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ያግባቡት መምህራኑ፣ በአስተባባሪው እልክና በሊቀ ጳጳሱ ውሳኔ ብቻ መርሐ ግብሩ ሊስተጓጎል እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ እንደ መምህራኑ አስተያየት የግል ጥቅምን ለመከላከል ከማሰብ በቀር እንዲህ ዐይነቱን ውሳኔ ለመስጠት የሚገፋፋ በቂ ኹኔታ የለም፤ ካለም ውሳኔውን መስጠት የሚችለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው፡፡ ማሳሰቢያው የተመለከቱት ከከፍል ሲወጡ መኾኑን የተናገሩት ደቀ መዛሙርቱ በበኩላቸው÷ በሓላፊዎቹ ላይ ያነሷቸው ጥያቄዎች በቀጣይ በሚቋቋመው ኮሚቴ እንደሚታይ ተስፋ በማድረግ ትምህርት ከጀመሩ በኋላ በአስተባባሪው ወጥቷል በተባለው ማሳሰቢያ ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል፤ በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ መነጋገራቸውንም አስታውቀዋል፤ ‹‹ውጡ ብለው ሲያስወጡን እንተናነቃለን›› ብለዋል ደቀ መዛሙርቱ፡፡

በትላንትናው ዕለት የተቋረጠው ትምህርት መጀመሩን የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን፣ መምህራኑና የጸጥታ አባላት ተዘዋውረው መመልከታቸውንና ማረጋገጣቸውን የገለጹት ደቀ መዛሙርቱ÷ ካፊቴሪያው የምግብ አገልግሎት እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ምግብ አልተዘጋጀም ቢባልም እንጀራ እየተጫነ ሲወጣ መመልከታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ካፊቴሪያው ለደቀ መዛሙርቱ አገልግሎቱን እንዲቀጥል በመምህራኑና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን ሲለመኑ የዋሉት የኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስም ‹‹እነዚህ መውጣት ነው ያለባቸው፤ ለእነርሱ እንኳን ምሳ ራትም አልሰጥ›› ሲሉ መደመጣቸው ተዘግቧል፡፡

እንደ መ/ር ዘላለም ረድኤት ባሉት የበታች ሓላፊዎች የተንኰልና ጥቅመኝነት ምክር ብዙ ስሕተት ሲፈጽሙ ለቆዩት ሊቀ ጳጳስ ይህ ዐይነቱ አነጋገራቸው አዲስ ባይሆንም፣ ደቀ መዛሙርቱ ያነሷቸው የሙስናና የአሠራር ብልሹነት ጥያቄዎች በርግጥም በቂ ማስተካከያና ምላሽ እንደሚሰጥባቸው በማግባባትና የፓትርያሪኩን መመሪያ ዋስትና በማድረግ ትምህርት ባስጀመሯቸው መምህራን ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳይፈጥር ተሰግቷል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የኮሌጁ አስተዳደር የቀን መደበኛ መርሐ ግብር ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን አስታወቀ

 1. Anonymous March 28, 2013 at 8:04 pm Reply

  ደቀ መዛሙርቱ በኮሌጅ ቆይታቸው ጥራቱ የተጓደለ ምግብ ፣ ፍታሃዊ ያልሆነ የውጤት ምዘና ሥርዓት ፣ የአስተማሪዎች ንቀትና ስድብ ፣ በተሃድሶ መናፍቃን ቡድን ቅሰጣና በአስተማሪዎች የአቅም ማነስ ይማረራሉ፡፡ ከኮሌጅ ተመርቀው ሲወጡ የሚከፈላቸው ደመወዝ ለዕለት ኑሮ አለመብቃትና በጥቂት መናፍቃን ምክንያት በምእመናን ዘንድ ለደቀ መዛሙርቱ ያለው አመለካከት የተዛባ መሆኑ ቤተክርስቲያን ከምሩቃኑ ልታገኝ የሚገባትን አገልግሎት እንዳታገኝ እያደረጋት ነው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ያቀረቡት የመብትና የአስተዳደራዊ ለውጥ ጥያቄ ሁሉንም የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ባሳተፈ መልኩ እያቀረቡ ሲሆን ተቃውሞውን ከሚመሩት የደቀ መዛሙርት ተወካዮች (ካውንስል አመራር አባላት መካከል የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጆች መሆናቸው ማስረጃ የቀረበባቸው) አጋጣሚውን ተጠቅመው የኮሌጁን አስተዳደር ቁልፍ መዋቅር ኦርቶዶክሳውያንን በማስነሳት አዝማቾቻቸው በሆኑት ሁለት መምህራን ለመተካት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተመልክቶአል፡፡

  መናፍቁን አሰግድ ሣህሉን እስከ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ተከራክሮ ድግሪውን ያስነጠቀውን የኮሌጁን አካዳሚክ ምክትል ዲን መምህር ፍስሐጽዮንና የተሃድሶ ኑፋቄ ከሚያራምዱ አራት መምህራን አንዱ የሆነውን መምህር ዘለዓለም ረድኤትን ከቀን ተማሪዎች አስተባባሪነት ኃላፊነታቸው ካልተነሱ ትምህርት አንቀጥልም፤ ከአስተዳደሩ ጋርም አንደራደርም ወደ ሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀይሮአል፡፡

  ደቀመዛሙርቱ በመምህር ፍስሐጽዮን ላይ ያቀረቡት ክስ “የአስተዳደር ሥራ ስለሚበዛበት በአንድ ሴሚስተር የሚያሰተምራቸው አራት ኮርሶችን የሚያስተምረው ሳይዘጋጅ ነው” የሚል ነው፡፡

 2. Anonymous March 29, 2013 at 11:02 pm Reply

  Aseged is one of the heresy preacher in our church . I know him very well when I was in college, All of this doing not to protect our church but to distract our church strength, unity and holiness. so our believer / memenane / take an action to this kind of church heresy preacher

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: