ፓትርያሪኩ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶስ በራሱ መተማመን አለበት›› አሉ

 • ቋሚ ሲኖዶሱን ለማገዝ የተቋቋመው ‹‹ሥራ አስፈጻሚ›› የሥራ ጊዜ አበቃ
 • አዲስ የቋሚ ሲኖዶ አባላት ተመርጠዋል
 • ፓትርያሪኩ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ጋራ ትውውቅ አደረጉ
 • ‹‹ቅድስና፣ ንጽሕና፣ ታማኝነት በተለይም ደግሞ ሃይማኖትን ይዞ መገኘት ያስፈልጋል›› /ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ለሠራተኞች ከሰጡት ማሳሰቢያ/

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከማንኛውም የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ አካልና የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት በመኾን ሕጎችን፣ ልዩ ልዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን የሚያወጣው ቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹በራሱ መተማመን አለበት›› ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አሳሰቡ፡፡ ቅዱስነታቸው ማሳሰቢያውን የሰጡት ስድስተኛ ፓትርያሪክ በመኾን ሥርዐተ ሢመታቸው በተፈጸመበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

ፓትርያሪክ (ርእሰ አበው) ኾነው የተመረጡበትን ሓላፊነት የቅ/ሲኖዶሱን አባላት በመያዝ በጋራ እንደሚወጡት ያላቸውን ተስፋ የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ እንደ አንድ ልብ አሳቢ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾኖ በሥምረት ከሠራ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንደገለጹት፣  በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውና የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ የኾነው ቅ/ሲኖዶስ በራሱ መተማመንና ቤተ ክርስቲያኒቱን የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡

Image

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

በቅዱስነታቸው ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ምዕዳን እንደተመለከተው÷ ይህ ግዴታ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዓላማ እንደተዘረዘረው ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዳይፋለስ መጠበቅና ማስጠበቅ ነው፤ ይህ ግዴታ ምእመናን ከአበው የተቀበሉትን ሃይማኖትና ሥርዐት ጠብቀው በትምህርተ ሃይማኖትና በመልካም ሥነ ምግባር ታንጸውና ጸንተው እንዲኖሩ፣ አእምሯቸውም እንዲሰፋ ጠንክሮ ማስተማር ነው፤ ይህ ግዴታ ቤተ ክርስቲያን ፍትሕ ርትዕ እኩልነት የሞላባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ በሕግና በሥነ ሥርዐት የምትመራ የእምነትና ሐቅ መገኛ እንድትኾን መጠነ ሰፊ ሥራ መሥራት ነው፡፡

‹‹እምነትና ሐቅ ከቤተ ክርስቲያን ካልተገኙ ከየት ይገኛሉ?›› ሲሉ የጠየቁት ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሐቅ በስፋት የሚገኝባት የእምነትና ሐቅ አስተማሪ መኾን እንደሚገባት በቃለ ምዕዳናቸው መክረዋል፡፡ በመልካም ሥነ ምግባር የታነጹ ታማኞች፣ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እንደ ምሶሶ አቅፈው ደግፈው የያዙ፣ ገንዘባቸውን፣ ጉልበታቸውንና ሞያቸውን በልግስና የሚሰጡ ምእመናን ያሉባት ቤተ ክርስቲያን መኾኗን ፓትርያሪኩ አስታውሰው፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ ሕግንና ሥነ ሥርዐትን ተከትሎ መሥመሩን ሳይለቅ እንዲጓዝ ካህናትና ምእመናን የድርሻቸውን ለመወጣት ብርቱ ጥረት ማድረግ አለባቸው፤››ብለዋል፡፡                                                                                                                                                             ለሀገር ዕድገትና ልማት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ያላትና ሊኖራት የሚገባው ተሳትፎ በቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳን ውስጥ ተዳስሷል፡፡ በስብከተ ወንጌልና በትምህርተ ሃይማኖት ምእመናንን ከማብዛትና ማጠናከር ጎን ለጎን ቤተ ክርስቲያን ዕድገቷንና ልማቷን ለማፋጠን ከምንጊዜውም የበለጠ መነሣት አለባት፡፡ ቅዱስነታቸው ‹‹የልማት ግሥጋሴ›› ካሉት የአገሪቱ ኹኔታ አንጻር ቤተ ክርስቲያን ወደ ኋላ መቅረት የለባትም፡፡ ለዚህም የሰው ኀይሏን አሠልጥና ራሷ የምትፈልጋቸውን÷ ለአብነት ያህል ከውጭ የምታስመጣቸውን ንዋያተ ቅድሳት÷ ራሷ ለማምረት መዘጋጀት አለባት፡፡ የሠለጠነ የሰው ኀይል ለመፍጠር ግን መጠነ ሰፊ ጥረት ይጠይቃል፡፡ ከዚህም ባሻገር የሀገር ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን፣ የሕዝብ ፍቅርና አንድነት እንዲጸና ቤተ ክርስቲያን ከኅብረተሰቡና ከመንግሥት ጋራ ተሰልፋ ቀድማ በመገኘት ምሳሌ መኾን አለባት፡፡

መንፈሳዊ አገልግሎት የሚከናወነው በእግዚአብሔር ስም በመኾኑ በመንፈሳዊነት የተደገፈ ታማኝነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተጠያቂነት የመላበት መልካም ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅብን ቅዱስነታቸው በበዓለ ሢመታቸው ቀን በሰጡት ትምህርተ ወንጌልና ቃለ ምዕዳን ደጋግመው ጠቅሰዋል፡፡ ከስሕተት ባንጸዳም የምንችለውን ጥንቃቄ ካደረግን በእግዚአብሔር ረዳትነት ሁሉም ይቻላል፡፡ ቅድስና፣ በመንፈሳዊነት የተደገፈ ታማኝነት፣ ፍትሐዊነት፣ ተጠያቂነት በተለይም ደግሞ ሃይማኖትንና እምነትን ይዞ መገኘት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ በዛሬው ዕለት÷ ከመንበረ ፓትርያሪኩ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ጋራ ባካሄዱት የትውውቅ መርሐ ግብር ላይም አጽንዖት የሰጡበት ጉዳይ ነበር፡፡

ከሁሉም በፊት ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ፣ አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን የማድረግ ዓላማ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ÷ በሥምረት እየሠራ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ግዴታውን ለመወጣት ‹‹በራሱ መተማመን›› አለበት፡፡ በቅዱስነታቸው ርእሰ መንበርነት የሚመራው ቅ/ሲኖዶስ በሥምረት መሥራቱ የጠበቀ እንዲኾን በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አነሣሽነትና ጉዳዩ በሚመለከታቸው አባቶች መልካም ፈቃድ የምርጫው ሂደት ፈጥሮት ባለፈው ክፍተትና የግንኙነት መሻከር ላይ በግልጽ ተነጋግሮ በቀጣይ ለሚጠበቁት ታላላቅ ተግባራት መግባባት ለመፍጠር ችሏል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዕጩ ፓትርያሪኮች ላይ ተነጋግሮ እንዲወስን ተካሂዶ በነበረው ስብሰባ ላይ ከፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ አንጻር የዕጩዎች አቀራረብንና የአስመራጭ ኮሚቴውን አሠራር የተቹት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልና ብፁዕ አቡነ አብርሃም አቋማቸውን አብራርተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል÷ ‹‹የወጣው የምርጫ ሕግ አልተከበረም፤ አስመራጭ ኮሚቴውም ግዴታውን አልተወጣም›› ከሚል አቋም መውሰዳቸውን፣ ይህም ለቤተ ክርስቲያን ህልውና ከማሰብ አንጻር እንጂ የፓትርያሪኩን (በወቅቱ ብፁዕ አቡነ ማትያስ) አባትነት አልያም በብዙኀኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት የተደገፈውን አቋም ላለመቀበል አለመኾኑን ገልጠው ተናግረዋል፤ ‹‹ብፁዕ አባታችን ያስችልዎት ነው የምንለው›› በማለት በፓትርያሪኩ በዓለ ሢመት ዋዜማ በተፈጠረ መድረክ አለመግባባቱን ለማስወገድ ተችሏል፡፡

የይቅርታ ጥያቄው ለእርሳቸው (ለቅዱስነታቸው) ሳይኾን በአለመግባባቱ ተደፍሯል ላሉት ቅዱስ ሲኖዶስ መቅረብ እንደሚገባው ያመለከቱት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ÷ ሁለቱ ሊቃነ ጳጳሳት በበዓለ ሢመቱ ላይ እንዲገኙ ጠይቀዋቸዋል፤ እነርሱም ተገኝተዋል፡፡ ሐቁ ይህ ኾኖ ሳለ የአቋም ልዩነቱን የጠብ መሣሪያ ለማድረግ የቋመጠ አንድ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ አባቶችን ያሳንስኹ መስሎት የሚደራርተው አሉባልታ÷ ሥር የሰደደ ጥላቻውንና ስጋቱን ከሚያጋልጥበት በቀር ርባና ሊኖረው አይችልም፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ በትላንትናው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰበሰቡት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ÷ ላለፉት ስድስት ወራት ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱንና ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩን ለማገዝ የተመረጡት ስምንት ብፁዓን አባቶች የሥራ ጊዜ ማብቃቱ ታውቋል፡፡ ስምንቱ ብፁዓን አባቶችን በቋሚ ሲኖዶሱ ውስጥ ተካተው እንዲሠሩ የተደረገው የቀጣይ ፓትርያሪክ ምርጫ እስኪከናወን ድረስ በመንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱንና ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩን ለመርዳት እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ስምንቱ አባቶች÷ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እንደነበሩ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በኋላ ቢያንስ ቀጣዮቹ ሁለት ሦስት ወራት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ የመንበረ ፓትርያሪኩን ጠቅላላ ኹኔታ በመገንዘብ ካለፉት የሚማሩበት፣ ከምርጫው በኋላ በፓትርያሪኩ ፊት ሞጎስ (ተወዳጅነት?) በማግኘት ግላዊና ቡድናዊ ጥቅሙን ለማራመድ የእርስ በርስ ሽኩቻ እንደጀመረ የሚነገርለትን የፅልመት ቡድን የሚጠራርጉበት፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ሳቢያ በውዝፍ የተተዉ የመዋቅርና የአሠራር ለውጦችን ለማካሄድ ዝግጅት የሚያደርጉበት፣ በአንዳንዶቹም ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገቡበት እንደሚኾን ተስፋ ተደርጓል፡፡ ‹‹ትብብራችኹ አይለይ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን ይዤ በጋራ እወጣዋለኹ›› ብለዋልና ከነባር የሥራ ሓላፊዎችና ዕውቀቱ ክህሎቱ ካላቸው ባለሞያዎች የሐሳብና የተግባርም ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በትላንቱ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ በአዲስ/ተለዋጭ አራት ብፁዓን አባቶች ተዋቅሯል፡፡ ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ፣ ከብፁዕ ዋና ጸሐፊውና ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ በመኾን እየሠሩ የሚቆዩት አራቱ አባቶች÷ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል እና ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ናቸው፡፡

መጋቢት ሁለት ቀን ዐቢይ ጾም (ጾመ ሁዳዴ) የሚጀመርበት ነው፡፡ በትላንቱ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ወደ የአህጉረ ስብከታቸው ተመልሰው ወርኀ ጾሙን በአገልግሎት እንዲያሳልፉ በማሳሰብና በመምከር መልካም የሱባኤ ወቅት በመመኘት ተሰነባብተዋል፡፡

Advertisements

17 thoughts on “ፓትርያሪኩ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶስ በራሱ መተማመን አለበት›› አሉ

 1. ሃይማኖት ርትእት March 6, 2013 at 5:00 am Reply

  እንግዲህ መለጠፉ ተጀመረም አይዶል……..ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰላም ለመሥራት የማንንም አገዛ አትሻም………ብቻዋን ምልእት ናት…….በሆነ ባልሆነው ሌላ ስም እያነሡ መጨቅጨቅ ቢበቃ ደግ ነው…….ከእግዚአብሔር ጋር ማለት ሲገባ ሌላ ጠገግ ፍለጋ ሰልችቶናል

 2. Dave March 6, 2013 at 5:44 am Reply

  I will never support a cadre in the name of the orthodox church. Lets God bring another way to save the church.

 3. Chiqunu March 6, 2013 at 6:12 am Reply

  Kezih behwala wore ayasfeligim…egzabher tenagrwal…yenaten worena filagotima aynew ke budinawinet yalweta neber….kezih behwala zim bitilu arif newe…orthodox kehonachihu abiyii tsomin be neger sayhon bestosme betselot asalifut

 4. Anonymous March 6, 2013 at 6:59 am Reply

  እኔ የሚገርመኝ አቡነ ማትያስ መሾማቸው አይደለም እንዲያውም ካሉት አባቶች በአቋም ሊሻሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አቡነ ጳውሎስን ሁሉም ፈርቶ አባ ገነን ሆነው ቤተክርስቲያኗን ሲመዘብሩና ሲያስመዘብሩ ዝም ጭጪ ሲሉ እርሳቸው በሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ በአምባ ገነንነታቸው፣ በገንዘብ ብክነት፣ በሃይማኖታቸው ወዘተ ይናገሩ ይጣሉ የነበሩት እርሳቸውና እርሳቸው ብቻ ነበሩ፡፡ ይህም የቅርብ ጊዜ ትውስታ ናቸው በእኔ አመለካከት ጀግና እላቸው ነበር፡፡ አሁን ካሉት ከዓላማቸው ፈሪ የሆኑ፣ ለምን ጳጳስ እንደሆኑ ዓላማቸውን ያልተረዱ፣ ግራና ቀኛቸውን ሳያውቁ የሚወዘወዙ፣ እንደ ቦይ ውሃ በነዷቸው የሚነዱ፣ ለደቂቃ ወጥ አቋም የሌላቸው፣ እንደ ሕጻን ልጅ በየደቂቃው የሚያኮርፉ፣ ሁሉ ጌዜ ብሶት የሚያወሩ ብቻ በተሰበሰቡበት ከእርሳቸው የተሻለ አለ ብየ አላምንም፡፡ ለዚህ ነው ዝም ብለው መርጠው ዝም ብለው የሾሙት፡፡
  እኔ የገረመኝ መሾማቸው ሳይሆን ለቤተክርስቲያን ጠበቃ ነኝ፣ ከእኔ በላይ ለአሳር፣ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ የሚለው፣ ዘመናዊ አሥተዳደርና ለውጥ በቤተክርስቲያን አመጣለሁ ብሎ ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና የሚለው ሥውር የመንግሥት አሥተዳደርን በመደገፍ የመንግሥትን፣ የእነ ንቡረ እድ ኤልያስና የእነ አባ ሠረቀ ባለሟልና ተዋናይ መሆኑ ነው፡፡ ‹‹በልጅነቱ የመነኮሰ ሰልሞ ይሞታል እንደሚባለው›› ማኅበሩ በትውልድ ተወቃሽ፣ በየዋሃንና በቅንነት ትክክለኛ ዓላማ ያለው መስሎአቸው ለሚከተሉት ኣባላቶቹ አስነዋሪ፣ በየዋኅነት ገንዘባቸውን ለሚሰጡ ምዕመናን አሳፋ ሥራ የፈጸመበት፣ እውነተኛ መሥሎ ሥውር ደባውን በቤተክርስቲያን ያሴረበት፣ የክፋትና የተንኮል እጁን የጫነበት ወቅት መሆኑ ትዝብትና ጥርጣሬ ውስጥ፣ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ርምጃ የሚሔድበት መሆኑን ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፡፡ ለመንግሥትም ታማኝ አገልጋይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
  የእውነት አምላክ፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤትና በረከት፣ በየገዳማቱ፣ በየአድባራቱ፣ በየጫካው፣ በየ ትምህርት ቤቱ ያሉ አባቶቻችን ጸሎት ቤተክርስቲያንን ምዕመናንን ይጠብቅልን አሜን፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ይፋረድልን፡፡
  ዛሬም ሆነ ወደፊት ቀጥተኛ የሃይማት አባት እግዚአብሔር እንዲሰጠን ገዳማት ውስጥ በዓት አጽንተው ለተቀመጡ አባቶች ማሳሰብ ነው፡፡

  • Anonymous March 7, 2013 at 11:16 am Reply

   yefelegikew kalihone mahibere kidusan lay wurjibign mawired new. Chigir yelem ketilibet ketekemeh. Mahiburina abalatu (endante yalew menajo sayihon) min endemiyadergu; min madireg endemichal gizena hunetan agenazbew egziabher eskefeked dires yagelegilalu. Lante gin tiru menfes yadilih!!

 5. hmmm March 6, 2013 at 3:52 pm Reply

  “ማኅበረ ቅዱሳንን ይፋረድልን፡፡ “”” ????? ምን አደረገ? ምነው ሰው በቁመናው ለቀቀ?

 6. mamo March 7, 2013 at 9:36 am Reply

  “ማኅበረ ቅዱሳንን ይፋረድልን፡፡ “”” ????? ምን አደረገ? ምነው ሰው በቁመናው ለቀቀ? tehadso nesh meselegne

 7. Assefa Melaku March 7, 2013 at 7:43 pm Reply

  እውነት ነው ነጋዴውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሁሉን ቻይ አምላክ ይፋረድልን ::

 8. ሃይማኖት ርትእት March 8, 2013 at 3:34 am Reply

  ከዚህም ባሻገር የሀገር ሰላምና ጸጥታ እንዲሰፍን፣ የሕዝብ ፍቅርና አንድነት እንዲጸና ቤተ ክርስቲያን ከኅብረተሰቡና ከመንግሥት ጋራ ተሰልፋ ቀድማ በመገኘት ምሳሌ መኾን አለባት፡፡……What does this mean? The line up is of God.

 9. hailu March 8, 2013 at 3:44 am Reply

  Who cares about this farciscal so called patriarch election. We know very well the process he came to this position with. Aba Paulos was illegal, and Aba Matias will be far worse illegal for he has not shown any concern about the division that shook our church for the past 20. A righteous father would have said NO to election if it causes the church to remain divided. A man of spiritual wisdom would have said YES to peace and reconcilliation first than hastely grabbing power with the help one’s ethnic party.

  And as to those who have started calling “His Holiness” while they have been telling us he came to the position in an unholy process, predetermined by the govenment, I say have you no shame? Would you oppose the devil before it controls you but then start calling him master ones it has a grip on you? That is what it sounds like. If the process was not holy, then the outcome is Unholy.

 10. ሃይማኖት ርትእት March 8, 2013 at 5:48 am Reply

  ቀረኝ
  ሐራ አዲሱ ተመራጭ እርቀ ሰላሙ ይቀጥላል አሉ ስትል ዘግባለች። ምንጊዜም እንደተቀለደ እና እንደተደባበቁ መራመድ የለም። ከምራቸው ከሆነ ሰሞኑን በስደት ያሉትን አባቶች የሚያብጠለጥለው ሐረካት ከየት መጣ? አንግዲያው ለሰላሙ የማሰናከያ ድንጋይ ነውና አድራጊዎቹ ተለይተው ተገቢው ትምህርት ሲሰጣቸው እንተማመናለን እንጂ ዝም ብሎ ለሚድያ መቅረቢያ ያኽል መወራቱ ሊቆም ይገባል።

 11. Anonymous March 8, 2013 at 9:18 pm Reply

  Poletica ena haymanot leytachu stawku asteyayet tsetalach degmo eko yamerica amgn enawkachhalen beltachu emtaskedsu letu beselam emdersu kekdase ylk betekrstiyan dej emtrmesemesu astemari siyastemr game emtchwetu eko nachu ykesarn lekesar stu new yetbalew !!

 12. Anonymous March 10, 2013 at 2:55 am Reply

  Yemanem shermuta eyetenesa ”his Holiness” yebalal? Wey Ethiopia !!

 13. Anonymous March 10, 2013 at 9:03 am Reply

  ሐቁ ይህ ኾኖ ሳለ የአቋም ልዩነቱን የጠብ መሣሪያ ለማድረግ የቋመጠ አንድ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ አባቶችን ያሳንስኹ መስሎት የሚደራርተው አሉባልታ÷ ሥር የሰደደ ጥላቻውንና ስጋቱን ከሚያጋልጥበት በቀር ርባና ሊኖረው አይችልም፡፡……

  ALGEBAGNIM…!! manin new demo..? yegebachu kalchu please!!!

 14. Anonymous March 10, 2013 at 9:06 am Reply

  ሐቁ ይህ ኾኖ ሳለ የአቋም ልዩነቱን የጠብ መሣሪያ ለማድረግ የቋመጠ አንድ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ አባቶችን ያሳንስኹ መስሎት የሚደራርተው አሉባልታ÷ ሥር የሰደደ ጥላቻውንና ስጋቱን ከሚያጋልጥበት በቀር ርባና ሊኖረው አይችልም፡፡

  MANIN NEW DEGMO…? ALGEBAGNIM….! YEGEBAW KALE , PLEASE!!!

 15. Desta March 10, 2013 at 9:09 am Reply

  …..ሐቁ ይህ ኾኖ ሳለ የአቋም ልዩነቱን የጠብ መሣሪያ ለማድረግ የቋመጠ አንድ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ አባቶችን ያሳንስኹ መስሎት የሚደራርተው አሉባልታ÷ ሥር የሰደደ ጥላቻውንና ስጋቱን ከሚያጋልጥበት በቀር ርባና ሊኖረው አይችልም፡፡

  Algebagnim…! yetignaw blog new? yegebaw kale please!!

 16. ሃይማኖት ርትእት March 11, 2013 at 7:51 am Reply

  I have heard the blessing of the “Patriarch” for the lent. Speaking less about the Heavenly Kingdom, he spokes loud about the earthly and the defied kingdom. Why??? is God allowing these people to sin on His Altar?

  Are they enforcing people to evacuate from the church? NEVER WE WON’T DO IT. We shall remain there forever. The Orthodoxy laities, STAY WHERE YOU ARE UNTIL THE MIRACLES OF THE ALMIGHTY CHANGES EVERYTHING. A bishop is ordained to speak only for the Kingdom of God, nothing less nothing more.

  Why is the guy barking about the gov’ts development agenda? Are we ready to leave another monastery like waldiba for the witches?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: