የስድስተኛ ፓትርያሪክ ምርጫ ሂደት

  • ‹‹ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልምና/2ቆሮ. 13÷7/›› (የአስመራጭ ኮሚቴው መሪ ቃል)
  • በአስመራጭ ኮሚቴው የተዘጋጀው የዕጩ ፓትርያሪኮች አጭር የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ታትሞ ተሰራጭቷል
  • የብፁዕ አቡነ ማትያስ ፎቶ በምርጫው ስፍራ ተሰራጭቶ መገኘቱ አነጋጋሪ ኾኗል
  • ‹‹ለአፍሪካና ለኢትዮጵያ መልካም እረኛ እንዲሰጥ ለመጸለይ ነው የመጣነው›› /የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች/

የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በመከናወን ላይ ነው፡፡

የምርጫው ሂደት ዛሬ፣ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት ሲጀመር የውዳሴ ማርያም ጸሎት፣ በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ካህናት ጸሎተ ኪዳን ተደርሷል፤ ከወንጌሉ ክፍል አንቀጸ ብፁዓን በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክና የአርሲ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ተነቧል፡፡

ስለምርጫው አጠቃላይ ሂደት እና ስለ ድምፅ አሰጣጡ በአስመራጭ ኮሚቴው የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ባያብል ሙላቴ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡

የድምፅ መስጫ ወረቀት የሚሰጥበት ሣጥን ከበላዩ በጣውላ የተዘጋና ዙሪያው ውስጡን በሚያሳይ መስተዋት የተሰራ ሲኾን ከመንግሥትና ከታዋቂ የሀገር ሽማግሌ ምእመናን በተወከሉ ታዛቢዎች ተፈትሾ እንዲታሸግ ተደርጓል፡፡

መራጮች በተለዩበት ምድብ በየአህጉረ ስብከታቸው እየተጠሩ ድምፃቸውን እየሰጡ ነው፡፡

Coptic Orthodox Church Representatives in the election hall

የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ ቡነ ቢሾይ እና አቡነ ሄድራ
(ፎቶ ተስፋ ዓለም ወልደየስ 

ከመንግሥት የተወከሉት የምርጫው ታዛቢዎች ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የመጡ ሲኾኑ እነርሱም፡- ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ፣ አቶ ልዑል የኋላ እና አቶ ትእዛዙ ደሳለኝ   ናቸው፡፡ ከታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎች በቅዱስ ሲኖዶስ የተወከሉት÷ ደጃዝማች ወልደ ሰማዕት ገብረ ወልድ፣ ኢንጅነር ጌታቸው ማኅተመ ሥላሴ እና አቶ ደርቤ ሥነ ጊዮርጊስ ናቸው፡፡

በታዛቢነት ከተጋበዙት አኀት አብያተ ክርስቲያን መካከል በምርጫ ቦታው የተገኙት የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካይ ብቻ ናቸው፡፡ በመራጭነትና በታዛቢነት የተገኙት የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች በስም ዝርዝራቸው፡- ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል (የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ)፣ ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ(ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ዕረፍት በኋላ ዐቃቤ መንበር የነበሩ)፣ ብፁዕ አቡነ ቢሾይ፣ ብፁዕ አቡነ ቤመን (የላዕላይ ግብፅ ሊቀ ጳጳስ)፣ ብፁዕ አቡነ ሄድራ(አስዋን) ናቸው፡፡ ‹‹ለአፍሪካና ለኢትዮጵያ መልካም እረኛ እንዲሰጥ ለመጸለይ ነው የመጣነው›› ብለዋል ግብጻውያኑ ልኡካን፡፡

መራጮች ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ በአዳራሹ ተቀምጠው ለመከታተል የተፈቀደላቸው ሲኾን የምርጫውም ሂደት በተደራጀና ቀልጣፋ ኹኔታ እየተከናወነ መኾኑን ለሐራዊ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ቀደም ሲል በሰባት ገጽ ታትሞ ከተሠራጨ በኋላ ታግዶ የነበረው የዕጩ ፓትርያሪኮችን አጭር የሕይወት ታሪክ የያዘው መጽሔት ዛሬ ጠዋት በኻያ ገጽ ታትሞ ለመራጮችና ለምርጫው ተከታታዮች ተሰራጭቷል፡፡

ከአምስቱ ዕጩ ፓትርያሪኮች አራቱ በምርጫ ጣቢያው (የስብከተ ወንጌል አዳራሹ) ተገኝተው ድምፃቸውን የሰጡ ሲኾን ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ጨርሶ አልታዩም፡፡ ቀኑ የካቲት 21 ቀን የእመቤታችን ወርኀዊ በዓል እንደመኾኑ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በመንበረ ፓትርያሪክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተገኝተው፣ ቀድሰው ነው ወደ ምርጫው የገቡት፡፡

የምርጫው ሂደታዊ ዘገባ ይቀጥላል፡፡CoverElection Mag 001Election Mag 002Election Mag 003Election Mag 004Election Mag 005Election Mag 006Election Mag 007Election Mag 008Election Mag 009Election Mag 010Election Mag 011

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: