ዋጋ ያላቸውን (የሚቆጠሩ) ድምፆች የመለየት ሥራ እየተሠራ ነው

የድምፅ አሰጣጡ ሂደት ተጠናቋል፡፡

የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና የምርጫው ታዛቢዎች በጋራ÷ በምርጫው ላይ የተገኙና ያልተገኙ መራጮች ቁጥር እኩል መኾኑን፣ እንዲሁም መራጮች የተቀበሉት የድምፅ መስጫ ወረቀትና በሣጥን ውስጥ የተገኘው የድምፅ መስጫ ወረቀት እኩል መኾኑን አረጋግጠዋል፤ በቃለ ጉባኤም ተመዝግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትና ታዛቢዎች በጋራ÷ እያንዳንዱ ድምፅ ሰጪ የሰጠው ድምፅ ዋጋ ያለው (የሚቆጠር) ን አለመኾኑን የመለየትና የመወሰን ሥራ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡

በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አንቀጽ 9 ንኡስ አንቀጽ 8 መሠረት÷ መራጮች በድምፅ መስጫው ወረቀት ላይ ከሌሎች መራጮች ስማቸው ተለይቶ እንዲታወቅ ሊያደርግ ወይም የራሳቸውን ማንነት ሊያመለክት የሚችል ፊርማም ኾነ ምንም ዐይነት ምልክት ማድረግ የለባቸውም፤ ተደርጎ ከተገኘም ወረቀቱ ዋጋ ቢስ ይኾናል፡፡

በማስከተል የድምፅ ቆጠራው የሚካሄድ ይኾናል፡፡

የምርጫው ሂደታዊ ዘገባ ይቀጥላል፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: