ለምርጫው ፍጻሜ ካህናትና ምእመናን ለሦስት ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና በጸሎት እንዲጠይቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ፣ የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም፣ በ9፡00 ሦስተኛ ዙር መግለጫ ሰጠ፡፡

የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

 • የድምፅ አሰጣጥ የሚካሄደው በጠቅ/ቤ/ክ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ነው
 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከዛሬ ጀምሮ በአዳራሹ እየተገኙ ለሦስት ቀን ጸሎት ያደርሳሉ
 • ለኮሚቴው የደረሱት የካህናትና ምእመናን ጥቆማዎች ጠቅላላ ብዛት 2791 ነው
 • 15 ጥቆማዎች ዋጋ አልባ ኾነዋል
 • ለፓትርያሪክነት የተጠቆሙ ብፁዓን አባቶች ጠቅላላ ቁጥር 36 ነው
 • በመጀመሪያው ማጣሪያ ያለፉ ብፁዓን አባቶች ቁጥር 19 ነው
 • በመጨረሻው ማጣሪያ የተያዙ አባቶች ቁጥር 8 ነው፤ ከእኒህ አምስት ተመርጠዋል
 • ‹‹ዕድሜና ያለውን ነባራዊ ኹኔታ›› ዋነኛ መመዘኛ እንደኾነ ተገልጧል
 • ዕድሜ ዋነኛ መመዘኛ የኾነው አወዛጋቢ ስለኾነ ነው
 • የብፁዕ አቡነ ማትያስ ዕድሜ 71 ነው፤ [የተወለዱት በ1934 ዓ.ም ነው፡፡]
 • የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት፣ የእርስ በርስ ግንኙነትና የመረጃ አያያዝ በጋዜጠኞች ጥያቄዎች ተተችቷል
 • ጋዜጣዊ ጉባኤውን የመሩት የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው የጡመራ መድረኰችን መረጃ በማዛባት ነቅፈዋል

በጋዜጣዊ መግለጫው ከተነሡት ጥያቄዎች መካከል የኢ.ቴቪው ዘጋቢ÷ ዛሬ በመግለጫው የተካተቱት መረጃዎች ከፊሉ (በዘጋቢው ልኬት ሰባ አምስት በመቶ ያህሉ) በብሎጎች ቀድሞ የወጣ መኾኑን በመጥቀስ፣ የአስመራጭ ኮሚቴውን አባላት ‹ምስጢራዊነት›/ምስጢር ጠባቂነት/ ጠይቋል፡፡ ከዛሚ ኤፍ. ኤም. የቀረበው ጥያቄ÷ መረጃዎች በዚህ መልኩ እየወጡ መነበባቸው ለቤተ ክርስቲያን ክብር ጥሩ ነው ወይ የሚል መንፈስ ያለው ነው፡፡ የሁለቱም ጋዜጠኞች ጥያቄዎች መነሻ÷ የኮሚቴው ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ በጡመራ መድረኰች የሚወጡ ዘገባዎችን ሙሉ በሙሉ በከፋፋይነትና በመሠረተ ቢስነት በመፈረጅ ቀደም ሲል ያሰሙት ሚዲያዊ አሠራርን ያልተገነዘበ ጭፍን ወቀሳ ነው፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የኮሚቴው ዋና ጸሐፊ ሊቀ ማእምራን ፈንታሁን ሙጩ÷ ኮሚቴው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩትና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደመኾናቸው ምስጢር እንደሚጠብቁና ምስጢር ለመጠበቅም ተማምለው እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ ብሎጎች ከብዙ ሐተታዎች /ለምሳሌ÷ በዕጩነት ሊገቡ ከሚችሉ አባቶች ዝርዝር/ የተወሰነው እውነት ሊኾንላቸው እንደሚችል ዋና ጸሐፊው ጠቁመው÷ በመጨረሻው ማጣሪያ የተያዙትን ዕጩ ፓትርያሪኮች ማንነትና ዝርዝር በተመለከተ ለቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከመቅረቡ በፊት መጀመሪያ በብሎግ በመቀጠልም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ሲወጣ ግን በኮሚቴው አባላት መካከል ከፍተኛ ድንጋጤ መፈጠሩን ተናግረዋል፤ ከዚህም የተነሣ ያለቀሱ መኖራቸውን አልሸሸጉም፡

ማስታወሻ፡ በሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ የጠቋሚዎችን ቁጥር አስመልክቶ በተላለፉት ዘገባዎች፣ ጠቅላላ ብዛቱ ዘጠኝ ሺሕ ያህል እንደሚኾንና ከዚህም 7200 ለብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እንደኾነ መገለጡ ይታወሳል፡፡ የጠቋሚው ጠቅላላ ብዛት በኮሚቴው መግለጫ በተመለከተው አኀዝ እንዲታረም ከይቅርታ ጋራ እንጠይቃለን፡፡ ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በአግባቡ የተገለጹ መኾኑን እናረጋግጣለን፡፡ በአዎንታዊ የመረጃ ተግባቦት ለኦርቶዶክሳውያን የመንፈስና የተግባር መነሣሣት መጦመራችንን እንቀጥላለን፡፡ ሐራ ዘተዋሕዶ የግለሰቦች ሳይኾን እንደ ስሟ የተዋሕዶ ጭፍራ፣ የተዋሕዶ ዘብ፣ የተዋሕዶ ዋርድያ ኾና ሚዲያዊ ግዴታዋን ትወጣለች፡፡Asmerach Com Third Round Meglecha

Advertisements

5 thoughts on “ለምርጫው ፍጻሜ ካህናትና ምእመናን ለሦስት ቀናት ፈጣሪያቸውን በጾምና በጸሎት እንዲጠይቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ

 1. ዘይገርም February 25, 2013 at 4:51 pm Reply

  ይህ መግለጫ ሲኖዶስን ወክሎ ለምርጫው ያለፉትን አስመራጩ ያጸደቀው ነው ወይስ አስመራጩ ኮሚቴ ሰርቶ ያቀረበውን ቅዱስ ሲኖዶሱ ማጽደቁን ያስታወቀበት ነው? ግራ የሚያጋባ ነው። እንደመግለጫው አተያይ አስመራጭና ሲኖዶስ የተቀላቀሉ ይመስላል። ሲኖዶሱ የሚቀርብለትን ስለማጽደቅ የተነገረው ቀርቶ ሁሉም ነገር በአስመራጩ ብቻ እያለቀ ያለ ነገር ይመስላል።

 2. Gebremikael February 25, 2013 at 9:25 pm Reply

  Taydya min yitebes?

  • ሃይማኖት ርትእት February 26, 2013 at 5:19 am Reply

   Gebrie, tibsu altesmamashim endie?

 3. Solomon February 26, 2013 at 4:52 am Reply

  Egeziabher esu hulunem yastkakel

 4. ዘይገርም February 26, 2013 at 5:01 am Reply

  ገብረ ሚካኤል በእውቀት ምድጃ ላይ ይጠበስ!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: