ሰበር ዜና – የኢትዮጵያው ቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ‹‹ዐራተኛው ፓትርያሪክና አብረዋቸው ያሉ አባቶች ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ስሕተቶች ከዛሬ ጀምሮ ‹‹በጽሑፍ፣ በሚዲያና በልዩ ልዩ ጉባኤያት ይፋ አደርጋለኹ፤›› አለ

 • ሕዝቡ በውጭ የሚገኙት አባቶች የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ የማያቋርጥ ተጽዕኖ እንዲያደርግባቸው፣ ለ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ ትብብሩንና ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልእኮ በዓለም ዙሪያ ጎልብቶ እንዲቀጥል የተለመደ ድጋፉንና ትብብሩን እንዲያጠናክር ጠይቋል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዛሬ፣ የካቲት 14 ቀን ረፋድ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫው÷ በሰሜን አሜሪካ በስደት ባሉት አራተኛው ፓትርያሪክና ሌሎች አባቶች የተቋቋመው ሲኖዶስ አውጥቶታል ለተባለው የሐሰት መግለጫ የተሰጠ አጸፋ መኾኑ በርእሱ ተመልክቷል፡፡

የመግለጫው ዋና ዋና ነጥቦች÷ አራተኛው ፓትርያሪክ በቅዱስ ወንጌልና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተደነገገውን በመጣስ የዚህን ዓለም ሹመት ከመንፈሳዊው ሹመት ጋራ አዳብሎ በመሥራት ይከሣቸዋል፤ የፓትርያሪክነቱም ሥልጣን የጨበጡት ‹‹የገዥዎችን ኀይል ተጠቅመው፣ ሲኖዶሱን ተጭነውና መንፈስ ቅዱስን ተጋፍተው ነው፤››  ይላል፡፡ ይህንኑ ሥልጣን በራሳቸው ጥያቄ ማስረከባቸውን የሚያስታውሰው መግለጫው÷ ሲኖዶሱ ጥያቄያቸውን አጥንቶ፣ ቀኖናው የሚለውን ጠብቆ ከሥልጣን ካነሣቸው በኋላ ዐራተኛው የቀድሞው ፓትርያሪክ ‹‹ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓትርያሪክ አይደሉም›› በማለት ውሳኔውን ያብራራል፡፡

ዐራተኛው የቀድሞው ፓትርያሪክ ባቀረቡት ጥያቄና በዚህ ቀኖና መሠረት እርሳቸውን አንሥቶ ሌላ ፓትርያሪክ ሾመ እንጂ በፓትርያሪክ ላይ ፓትርያሪክ አልሾመም፤ ሁለት ፓትርያሪክ እየተባለ የሚነገረው አነጋገርም ሕጋዊነት የሌለው ፍጹም የስሕተት አባባል መኾኑን ይተቻል፡፡ ሲኖዶሱ ይህን ውሳኔ ባስተላለፈበት ወቅት ዛሬ በአሜሪካ ያሉት አባቶችም ባሉበት፣ በተስማሙበትና በፈረሙበት ኹኔታ የተፈጸመ መኾኑን መግለጫው አስታውሶ፣ ዛሬ ያ የፈረሙበት ሰነድ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀምጦ እያለ እውነትነት የሌለውን ሌላ ታሪክ ለመተረክ ሲሞክሩ መሰማታቸው እጅግ ከፍተኛ ትዝብት ላይ የሚጥላቸው ነው ብሏል፡፡

መግለጫው ከዚህ በመቀጠል በውስጥም በውጭም ያሉ ምእመናን ከቅ/ሲኖዶሱ ጎን ሊቆሙ ይገባል ያለበትን ባለሰባት ነጥብ መልእክት አስተላልፏል፡፡

ጋዜጣዊ መግለጫውን በንባብ ያሰሙት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ሲኾኑ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ጨምሮ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተገኝተዋል፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ቀጥለው ይመልከቱ፡፡Sy Meg 001Sy Meg 002Syn Meg 003 Syn Meg 006Syn Meg 004Syn Meg 005

Advertisements

5 thoughts on “ሰበር ዜና – የኢትዮጵያው ቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ‹‹ዐራተኛው ፓትርያሪክና አብረዋቸው ያሉ አባቶች ፈጽመዋቸዋል ያላቸውን ስሕተቶች ከዛሬ ጀምሮ ‹‹በጽሑፍ፣ በሚዲያና በልዩ ልዩ ጉባኤያት ይፋ አደርጋለኹ፤›› አለ

 1. ግእዝ በመሥመር-ላይ February 21, 2013 at 7:51 pm Reply

  Strikingly, this was introduced to us by a certain Mel’akeBesrat: http://www.dejeselam.org/2013/02/blog-post_2183.html#links

  • Ben February 22, 2013 at 2:20 am Reply

   አንተ ታምን ከነበረው የነመልከ ፀዲቅ ውሸት ጋር ተማታብህ?

 2. ano February 22, 2013 at 6:51 am Reply

  Check the signature

 3. ገ/ሚካኤል February 22, 2013 at 9:00 am Reply

  For these
  እውነት እንደ እሬት ለሚመራችሁ ፖለቲካ-ሃይማኖት ቅይጦችና ፣ እውነትን ለምትፈልጉ ቅን የቤተክርስቲያን ልጆች
  I hope u will accept who ever the owner of the blog Truth is Truth and False is false for non-extremists(for these who look for Truth)

  Check the ff links for better stand.
  http://dejebirhan.blogspot.com/2013/02/blog-post_3703.html

  http://dejebirhan.blogspot.com/2013/02/blog-post_17.html

 4. Ayegud February 23, 2013 at 2:12 am Reply

  እውነቱ እንዲወጣ ከተባለ ለምእመኑ ማሳየት የነበረባች ሁ ዐራተኛው ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሪዎስ ባቀረቡት ጥያቄና በዚያን ጊዜ የተገኘው ቅዱስ ሴኖዶስ ያሳለፈውን ውሳኔ ፖስት ማድረግ ነው። ኣቡነ ናትናኤል ያሳለፉትን መግለጫ ዛሬ ብታሳዩን ፋይዳ የለውም። ድርጊቱን የፈጸመው የመንግስት አካል ሲናዘዝ ምነው የእናንተ መንፈስ አልተረበሸም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: