ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!

 • ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
 • ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
 • የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
 • ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/

የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-

1)  ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ

2)  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

3)  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

4)  ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ

5)  ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

የአስመራጭ ኮሚቴው አጣርቶ ሊያቀርባቸው ከሚችላቸውና የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አባቶች አራቱ በኮሚቴው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ኮሚቴው በሚያቀርባቸው ዕጩዎች ውስጥ ያልተጠበቁ አባቶች ሊታዩ እንደሚችሉም አስቀድሞ የተገመተ ነበር፡፡

ነገር ግን በብዙ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ድምፅ የተጠቆሙትና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አንቀጽ 5 የተዘረዘረውን የዕጩ ፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱን ያሟላሉ ተብለው የታሰቡት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤእና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከዕጩዎቹ ሳይካተቱ መቅረታቸው ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አካላትን መስገረሙ አልቀረም፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ቀድሞም ከዕጩዎች ዝርዝር እንዳይጨመሩ በአንዳንድ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና በተለይም ‹‹መንግሥት የሚፈልጋቸውን ብፁዕ አቡነ ማትያስን እናስመርጣለን›› በማለት በመራጮች ላይ ሽብርና ስጋት ሲፈጥሩ በሰነበቱት÷ የእነ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፣ መጋቤ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ፣ መ/ር አባ ገብረ መድኅን ኀይለ ጊዮርጊስ እና መ/ር ዕንቊ ባሕርይ ተከሥተ ቡድን ከፍተኛ ጫና ሲፈጠር መሰንበቱ ተዘግቧል፡፡

ኮሚቴው ዕጩዎቹን የለየበትን ሂደት ወደፊት በዝርዝር ለማወቅ የሚጠበቅ ቢኾንም ስለ ተግባርና ሓላፊነቱን አስመልክቶ÷ በአንቀጽ 6/ሐ – ጥቆማ ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከካህናትና ምእመናን እየተቀበለ እንደሚሠራ፤ በአንቀጽ 6/ሰ – የዕጩዎችን ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ ለ15 ቀናት ይፋ በማድረግ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንደሚቀበል፤ በአንቀጽ 6/ሸ – በተቀበላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች መሠረት ዕጩዎቹን ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ መርምሮና አጣርቶ የሚቀበለውን ከተቀበለ፣ የማይቀበለውንም ከጣለ በኋላ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ዕጩዎች ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ እንደሚያሳውቅ በግልጽ የተደነገገ በመኾኑ ቀጣይ አካሄዱ ከእኒህ በተጨባጭ መሸራረፍ ከጀመሩ አናቅጽ አኳያ የሚመዘን ይኾናል፡፡

ሐራዊ ምንጮች ከወዲሁ ስለኹኔታው ለመረዳት ባደረጉት ጥረት ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው ጥርጣሬ ያላቸው ሲኾን ከዚህም በመነሣት ውሳኔውን በፊርማቸው ስለማረጋገጣቸውም አበክረው ይጠይቃሉ፡፡

‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ›› የሚለው ሰሞንኛ አባባል ቋጠሮው ሊፈታ እነኾ ቀኑ ቀርቧል፡፡

Advertisements

18 thoughts on “ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!

 1. Tilahun ayalew February 21, 2013 at 9:49 pm Reply

  ሰበር ዜናን በጣም እወደዋለሁ።ምክንያቱም
  ስለ ኢትዮጵያ ግዜያዊ ሁኔታ ኢንፎርሜሽን ስለማገኝበት።

 2. Anonymous February 21, 2013 at 11:33 pm Reply

  abune samuel alemekatetachew egeziabeharen enamesegenalen

 3. Haymanot Rtet February 22, 2013 at 6:15 am Reply

  ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ

  • በቀለ February 22, 2013 at 3:26 pm Reply

   አሁን አታልቅሺ
   የማህበረ ቅዱሳን ግብዓተ መሬት ሲፈጸም በደንብ ታለቅሻለሽ፡፡

 4. ሃይማኖት ርትእት February 22, 2013 at 6:24 am Reply

  ከማጀብ መታጀብ

 5. Chiqunu February 22, 2013 at 7:41 am Reply

  WoW it is nice decision NOT to include both Abune Gabriel and Samuel. both don’t deserve to be patriarch.

  • Mahlet February 22, 2013 at 11:43 am Reply

   Ha ha ha Gash Chiqunu…ende techekonk yaskereh ena …..Abune Gebriel and Samule minabak adereguh ena new “they don’t deserve to ” patriaric yalkew. What is your justification? Tehadiso nesh meselegn….that is why! Moron

 6. ገ/ሚካኤል February 22, 2013 at 8:35 am Reply

  May I say Congra For YeChelamaw Buden????????
  But I hope God will destroy your Building like Senaor Ginb.
  እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር፡፡
  ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ›› —› ልክ ነው???
  እግዚአብሔር እናንተ በምትመርጡዋቸው አባት አድርጎ የፍቅር፣ የቅንነት፣ ለቤተክርስቲያን እድገት የሚያስብ እና የአስተዋይነት ልቦናን እንዲሰጣችሁ ጸሎቴ ነው፡፡
  ኦ ንጉሠ ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላመከ ኃበነ ከመ ኢንትመአእ በፀር አላ ንትፋቀር በበይናቲነ፡፡
  ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!
  ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!
  ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!

 7. Anonymous February 22, 2013 at 10:26 am Reply

  elelelelelelelelelelelele abba samuel be Simonawi menged yihn talaq maereg kihinet lemagignet kenbuchlochachew yadergut tiret beamlak feqad tequwartuwal. Amen kezih behuwala keteteqomut mehakel Amlak lebetu yalachew Abat yihunu. Amlak hoyi ante lebeth asb

 8. Anonymous February 22, 2013 at 11:15 am Reply

  ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ባለመካተታቸዉ ሀዘን ልቤን ሰብሮታል፡፡ የእግዚአብሔርን መንገድ ማን ያዉቃል? ብቻ …

 9. Solomon from harar February 22, 2013 at 1:22 pm Reply

  Aba samuel bemrchaw mekatet becha syhon memrtem alebachew

 10. Solomon from harar February 22, 2013 at 1:35 pm Reply

  What the reson abune samuel from 9000 vote gets 7200 so what is the probelm that he out from 5 pope

 11. Ke harar michael February 22, 2013 at 5:33 pm Reply

  Pa pa pa betam tekeklegna mecha new end solomon menm layagegn lemayawkachew aba samuel yachebchbal

 12. Solomon February 22, 2013 at 5:41 pm Reply

  Zarem negem aba samuel telk abat nachew negr gen kemrchaw yaltekatetubt mekniyat menden new?

 13. Anonymous February 23, 2013 at 3:54 pm Reply

  ሩጫ እንጂ ምርጫ አልሆልን አለ አይደል፤አቡነ ገብርኤልና እና አቡነ ሳሙኤል ለምን አልተካተቱም;በጣም አስገራሚ ነገር ነዉ፡፡

  • Anonymous February 24, 2013 at 5:16 pm Reply

   abune samuele balemekatetachew betam azignalehu!!

 14. Philipos ZeRaguel February 24, 2013 at 1:26 pm Reply

  BEST ELECTION!!!! SPECIALLY ABA MATIYAS

 15. Gebremikael February 25, 2013 at 9:35 pm Reply

  You might call me tehadisso or woyane because of my comment I repeat again again abune matyas .abunematyas yetewahedo cchurch leader god wiil help him he is strong father honest father please give your vote for him.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: