የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ዕጩ ፓትርያሪካቸውን አሳወቁ

 • ከዘረኝነትና ሙስና የጸዳ አመራር ይሰጣሉ ያሏቸውን አቡነ ሳሙኤልን በዕጩነት ጠቁመዋል
 • የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችም ሊቀ ጳጳሱ በዕጩነት እንዲቀርቡ ጠይቀዋል
 • በአስመራጭ ኮሚቴው ላይ የተአማኒነት ጥያቄ ተነሥቷል
 • የዕጩ ፓትርያሪክ ጥቆማው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል

የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ባወጣው የምርጫ መርሐ ግብር መሠረት፣ ከካህናትና ምእመናን የዕጩ ፓትርያሪክ ጥቆማ የሚቀበልበት ቀን ነገ የካቲት 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ ያበቃል፡፡ ኮሚቴው የጥቆማ ስጡ ጥያቄውን በይፋ ካቀረበ በኋላ በተለይ በአዲስ አበባ አራቱ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ዕጩ ፓትርያሪክ ጠቋሚዎቹ የድጋፍ ደብዳቤዎችን ይዘው በተናጠልና በቡድን እየቀረቡ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት ዕጩአቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፤ ጥቆማው ለዚሁ በተመደበው የፋክስ አድራሻ ጭምር እየተላከ መኾኑ ነው የተነገረው፡፡

ጠቋሚዎች የሚሞሏቸው ቅጾች በዕጩነት ስለሚጠቁሙት አባት ያላቸውን ዕውቂያ (በምንኲስና፣ በአገልግሎት፣ በትምህርት ደረጃ) የሚጠይቅ/የሚለካ ነው ተብሏል፡፡ ቅጹ በጠቋሚዎች ከተሞላ በኋላ የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ተፈራርመው በማኅተም በታሸገው ሣጥን ውስጥ የሚጨምሩት ሲኾን ይኸው ሣጥን ነገ ከቀኑ 10፡00 በኋላ ሁሉም የኮሚቴው አባላት ባሉበት ተከፍቶ የመለየት ሥራ እንደሚሠራ ተገልጧል፡፡ በፋክስ የሚላኩት የዕጩ ጥቆማዎች በምን ላይ ተመሥርተው እንደሚሰጡና የምሥጢራዊነት ጉዳይ ግን አጠያያቂ ኾኗል፡፡

ስለ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ በውጭና በሀገር ውስጥ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ካህናትና ምእመናን የዕጩ ፓትርያሪክ መመዘኛ መስፈርቱን ዐውቀውና ተገንዝበው በጥቆማው የሚሳተፉበት የብዙኀን መድረክ ሳይፈጠር፣ ባሉትም መድረኰች አንዳችም የቅስቀሳ ሥራ ሳይሠራ በነገው ዕለት የሚጠናቀቀው የዕጩ ጥቆማው ይኹን የምርጫው መርሐ ግብር አጠቃላይ ሂደት በኮሚቴውና በአባላቱ ላይ የግልጽነት፣ የተአማኒነትና የተቀባይነት ጥያቄዎችን እያሥነሳ ማወያየቱን ቀጥሏል፡፡ ጥያቄዎቹ ኮሚቴው ከሚሠራበት የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ ይዘት (መንፈሳዊነት)፣ ካወጣው የምርጫ አፈጻጸም መርሐ ግብር ግልጽነትና ጥድፊያ ጀምሮ እስከ ግሰለብ አባላቱ ማንነት ድረስ የሚዘልቅ ነው፡፡

ይህም ኾኖ ‹‹ምርጫው መካሄዱ ካልቀረ አጋጣሚውና ዕድሉ አይለፈን›› በሚል በተደራጀ አኳኋን ለዕጩ ጥቆማው የተንቀሳቀሱ አካላት መታየታቸው አልቀረም፡፡ በተረጋገጠ መነሻ÷ በጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ለመልካም አስተዳደር እንዲያመች በሚል ለአራት ከተከፈለው የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት መካከል የሦስቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች የቀድሞውን የሀ/ስብከቱን ረዳት ሊቀ ጳጳስ፣ የአሁኑን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን በዕጩ ፓትርያሪክነት መጠቆማቸው ታውቋል፡፡

ሥራ አስኪያጆቹና ጽ/ቤቶቻቸው በእነርሱ ጥቆማ ብቻ ሳይወሰኑ በአህጉረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች የጥቆማ ብቻ ሳይኾን የመራጭነት መብት እንዲሰጣቸው አስመራጭ ኮሚቴውን መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡ ጥያቄያቸውን ያዳመጡት የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት በተለይም ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ግን ጥያቄው በምርጫ ሕገ ደንቡ ስለመራጮች የተደነገገውን እንደሚፃረር በመግለጽ በቀጥታ ውድቅ እንዳደረጉትና በተግሣጽ እንደመለሷቸው ተገልጧል፡፡

በዛሬው ዕለት በዕጩ ጥቆማው ረገድ የተሰማው ሌላ የተደራጀ እንቅስቃሴ ደግሞ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመደበኛው መርሐ ግብር ደቀ መዛሙርት ያቀረቡት ነው፡፡ በቁጥር 180 ያህል የኾኑ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት፣ የስድስተኛውን ፓትርያሪክ ምርጫ በማስመልከት ከትላንት ረቡዕ እስከ ነገ ዐርብ የሚቆይ የሦስት ቀናት የማኅበር ጸሎት እያደረጉ ነው፡፡ ደቀ መዛሙርት ለጸሎት ሱባኤው በተሰባሰቡት አጋጣሚ ስለ ኮሌጁ አስተዳደር እና ስለ መምህራኑ ተወያይተዋል፤ ጥያቄዎችንም አንሥተዋል፡፡

ከጠቅላላ ሕዝቧ ዐሥር በመቶ ብቻ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት በሚገኝባት የኮፕት ቤተ ክርስቲያን ዘጠኝ የነገረ መለኮት ኮሌጆች እንዳሉ የሚናገሩት ደቀ መዛሙርቱ÷ ከጠቅላላ ሕዝቧ ከግማሽ በላይ ለሚኾነው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ ለሚገኝባት ኢትዮጵያ ሦስት የነገረ መለኰት ኮሌጆች ብቻ በቂ እንዳልኾኑ ተናግረዋል፡፡ ከኮሌጆች የቁጥር ማነስ ባሻገር የሚመደበው በጀትና የሚሰጠው አገልግሎት አለመመጣጠን፣ ለተቋሞቹ የማይመጥኑ መምህራን መብዛት፣ በአቅም የተሻሉ መምህራን ቢኖሩም በቤተሰብና ዝምድና የተሳሰረ ነው ለሚሉት አስተዳደር ጥገኛ መኾናቸውና አካዳሚያዊ ነጻነት ማጣታቸውን ደቀ መዛሙርቱ ይዘረዝራሉ፡፡

ደቀ መዛሙርቱ በጸሎት ሱባኤ ቆይታቸው በኮሌጁ ጉዳይ ብቻ ሳይወሰኑ በአጥቢያ ደረጃ ስላለው የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርም አንሥተዋል፡፡ ‹‹በአጥቢያ ደረጃ የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት በአምስቱ ከለባት ቤተሰባዊነት የጥቅመኞች ሲሳይ ኾኗል›› ይላሉ ደቀ መዛሙርቱ፡፡ ‹‹አምስቱ ከለባት›› የሚሏቸው የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችን፣ ጸሐፊዎችን፣ ሒሳብ ሹሞችን፣ ቁጥጥሮችን እና ገንዘብ ያዦችን ነው፡፡

ደቀ መዛሙርቱ የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴውን የሚተቹት በኮሚቴው ከተካተቱት አባላት በመነሣት ነው፡፡ በተለይም ቀድሞ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሳሉ እናውቃቸዋለን በሚሏቸው የአስመራጭ ኮሚቴው ጸሐፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ላይ በመተኰር ዘረኝነትን፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በማንሰራፋት ይወቅሷቸዋል፡፡ በዚህ አስመራጭ ኮሚቴ አስፈጻሚነት ሊመረጥ የሚችለው አባት የኮሚቴውን ጸሐፊ ከሚወቅሱባቸው ጉዳዮች (ዘረኝነት፣ ሙስና፣ ብልሹ አሠራር) የጸዳ ስለመኾኑም ደቀ መዛሙርቱ ይጠይቃሉ፡፡

Ab Samuel leading...

አቡነ ሳሙኤል

የኮሌጁ ተማሪዎች ጥርጣሬያቸውን ከኮሚቴው አባላት ወደ መራጮች በማሻገር በተለይም ከየአህጉረ ስብከቱ በየሊቃነ ጳጳሳቱ በሚመራ የአስተዳደር ጉባኤ ስብሰባ ተወክለው ከሚመጡት መራጮች ድምፅን በገንዘብ/በጥቅም ለመግዛት ከፍተኛ ዘመቻ እየተካሄደና ጫናም እየተፈጠረ መኾኑን አስረድተዋል፡፡ ተጽዕኖው በውል ዘርዝረው ካላሳወቋቸው ሊቃነ ጳጳሳትም አካባቢ እንደታየ የሚናገሩት ደቀ መዛሙርቱ ምርጫው መካሄዱ የማይቀር ከኾነ ዘንድ ቀደም ሲል በየመዋቅሩና በየተቋማቱ ከተጠቀሱት የዘረኝነት፣ ሙስና እና ብልሹ አሠራር የጸዳ፤ በበሳል አመራር ሰጪነቱና በአስተዳደር ችሎታው የተመሰከረለት፣ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ግዴታዎቹን በብቃት መወጣት የሚችል ዕጩ ፓትርያሪክ እንዲጠቆም ጠይቀዋል፡ የዕጩውን ማንነትም ወስነው አሳውቀዋል፤ የሚመረጠው ፓትርያሪክ ሊያሟላቸው ይገባል፣ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንም የተደገፉ ናቸው ያሏቸውን መመዘኛዎችንም ዘርዝረዋል፡፡

በደቀ መዛሙርቱ የፓትርያሪክ መመዘኛ መስፈርት መሠረት የሚመረጠው አባት፡-

 • ባለራእይ ማለትም የቤተ ክርስቲያኒቱን ዓላማ ሁለገብ በኾነ መልኩ ለሁሉም ተደራሽ በማድረግ የሚያስፈጽም፤
 • ለሰው ልጆች እኲልነት የቆመ÷ እግዚአብሔር በአርኣያውና በአምሳሉ የፈጠረውን የሰው ልጅ ትንሽ ትልቅ ሳይል በማክበር ፍትሕ በመስጠት ማገልገልና በየትኛውም መንገድ እግዚአብሔር የሰጠውን ነጻነት ከመጥፎ ነገር መጠበቅና ማስጠበቅ የሚችል፤
 • በበጎ ሥነ ምግባሩና ትሩፋቱ የተመሰከረለት፤
 • የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት የሚጠብቅና የሚያስጠብቅ፤
 • የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት አጠናክሮ የሚቀጥል፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ክብሯ እንደተጠበቀ ከሁሉም ጋራ በሰላምና በፍቅር እንድትኖር ማድረግ የሚችል፤
 • በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስጥ መንግሥትና ሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲሁም ልዩ ልዩ ተቋማት መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ፣ በየዘርፉ ባለሞያዎችን በማማከር የሚሠራ ሥርዐት መዘርጋት የሚችል፤
 • የቤተ ክርስቲያኒቱን ሠራተኞች በሞያቸውና በክህሎታቸው በሚገባቸው ቦታ ማስቀመጥ (The right person at the right place) የሚለውን መርሕ የሚከተል፤
 • የአብነት ት/ቤቶች፣ የካህናት ማሠልጠኛዎች፣ መንፈሳዊ ኮሌጆች ተሻሽለውና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም ተጨማሪ ኮሌጆች እንዲከፈቱ የሚያደርግ፤
 • የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች በሚናገሩት ቋንቋ ሁሉ አስተምህሮዋን የሚገልጹ መጻሕፍትን እየተረጎመችና እያሳተመች ማዳረስ እንድትችል የሚያደርግ፤
 • የቤተ ክርስቲያኒቱን የገንዘብ አስተዳደር ማእከላዊ በኾነ መልኩ እንደ መንግሥት አስተዳደር ከከተማ እስከ ገጠር ላሉት አብያተ ክርስቲያን በስኬል ደረጃ እንዲዳረስ ማድረግ የሚችል፤
 • ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለሀገሪቱ የዕድገት ማነቆ እየኾነ የመጣውን ዘረኝነትንና ሙስናን የሚያስቀር ጠንካራ አስተዳደር መዘርጋት የሚችል፤
 • የቤተ ክርስቲያኒቱን ንብረቶች ማለትም ቅርሶች፣ የታሪክ ቦታዎች፣ ገዳማት በአጠቃላይ ውድ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አንጡራ ሀብቶቿን በመከባከብ መጠበቅና ማስጠበቅ ብሎም በአግባቡ መጠቀም የምትችልበትን ሥርዐት መዘርጋት የሚችል፤
 • የተዘጉ አብያተ ክርስቲያንና ገዳማትን ወደ ህልውናቸው መልሶ አገልግሎት የሚሰጡበትን ሥርዐት መዘርጋት የሚችል፤
 • የሉላዊነትን (ግሎባላይዜሽን) ጥቅሙንና ጉዳቱን በመለየት ሃይማኖት፣ ምግባርና መልካም ባህል ላለው ሕዝባችን ማስረዳት የሚችል፤
 • ከአገር ውጭ በሥራ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ተሰራጭተው ላሉ ምእመናን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚያገኙበትን ኹኔታ የሚያመቻች፤

በአጠቃላይ ዘመኑን የሚዋጅ የቤተ ክርስቲያኒቱን እሴቶች የሚጠብቅና ከአሁኑ ትውልድ አንጻርም መግባባት ይቻል ዘንድ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋራ በአግባቡ መተዋወቅ የሚችል፣ ከዓለም ቋንቋዎች አንዱ የኾነውን እንግሊዝኛን መናገርና መስማት የሚችል መኾን ይጠበቅበታል፡፡

በዚህ የፓትርያሪክ መመዘኛ መስፈርት መሠረት ደቀ መዛሙርቱ [ለፓትርያሪክነት] ለዕጩ ፓትርያሪክነት ይበቃሉ በማለት የጠቆሟቸው አባት÷ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ናቸው፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ለዕጩ ፓትርያሪክነት [ለፓትርያሪክነት] ያበቋቸዋል ያሏቸውን ብቃታቸውን ዘርዝረዋል፤ እንዲህ ሲሉ፡-

 • በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከ60 በላይ አብያተ ክርስቲያን አሳንጸዋል፡፡
 • በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ በቅ/ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን፣ በአዲሱ ቅ/ሚካኤል፣ በጎፋ ቅ/ገብርኤል፣ በላፍቶ ቅ/ሚካኤል፣ በብሥራተ ገብርኤል፣ በአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት፣ በኮተቤ ኪዳነ ምሕረት፣ በአቃቂ መድኃኔዓለም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችን አስገንብተዋል፡፡
 • ወቅታዊ ተጨባጭ ኹኔታዎችን ለማሳወቅ ለመላው አዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ካህናት በየስድስት ወሩ ሥልጠና እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡
 • ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን የአዲስ አበባን ሀ/ስብከት መንበረ ጵጵስና በሚያስገርም ኹኔታ አሳንጸዋል፡፡
 • ከ40,000 በላይ የኾኑ በደቡብ ኦሞ፣ በቤንች ማጂና በቤንሻንጉል ጉሙዝ አካባቢ የሚኖሩ ኢጥሙቃን ወገኖችን አስጠምቀዋል፡፡
 • በዲቪዲ እና በቪሲዲ ቁጥራቸው ከስድስት በላይ የኾኑ ትምህርታዊ ሥርጭቶችን ለምእመናን አሠራጭተዋል፡፡
 • ከ10 በላይ ወቅታዊ መጻሕፍትን አሳትመው አሰራጭተዋል፡፡ እኒህም፡- ባሕታውያን በዋልድባ ቁጥር 1፤ ረዐይኬ አባግዕዬ፤ ባሕታውያን በዋልድባ ቁጥር 2፤ ሰዶማውያን የኀጢአት ደመወዝ፤ ቤተ ክርስቲያንና አስተዳደር፤ Sodomites and the wage of sin፤ ድህነትና ኢትዮጵያ፤ በኢትዮጵያ የሃይማኖት መቻቻል አለን? ታሪክህን ዕወቅ፤ መሪና አመራሩ፤ ፈለገ አሚን ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሲኾኑ ከሌሎች አካላት ጋራ ተዘጋጅተው የታተሙ መጻሕፍት ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ ሁለት ሺሕ ዓ/ም፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዐተ አምልኮ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ናቸው፡፡ ከመጽሐፎቻቸው ጀርባ እንደገለጹት ለወደፊት ሊታተሙ የተዘጋጁ መጻሕፍት ደግሞ፡- እውነተኛ መሪ ማን ነው?፤ ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቋት ዘንድ ለመንጋውና ለራሳችኹ ተጠንቀቁ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን ማን ይናገር? የሚሉ ናቸው፡፡
 • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መካከል ለአምስት ቀን የቆየ ዐውደ ትምህርት እና የልምድ ልውውጥ እንዲደረግና የሁለቱ አገሮች ሰላማዊ ግንኙነት እንዲጠነክር አድርገዋል፡፡
 • ለሚማሩና ራሳቸውን ለሚያሻሽሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ፡፡
 • ከቻይና ኖሬላ ካምፓኒ ጋራ ከስድስት በላይ ለሚኾኑ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት አድባራት በአንድ ቢልዮን ብር ሆስፒታልና ልዩ ልዩ ልማታዊ ሥራዎችን ለመሥራት ተፈራርመው ነበር፤ ይህም በቻይናውያን TODAY ጋዜጣ ላይ ለዘገባ በቅቷል፡፡
 • የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ የሚቃወመውንና ብሎም ለማጥፋት የሚታገልበትን አሳፋሪ ሙስና (ብልሹ አሠራር) እና ዘረኝነት በከፍተኛ ደረጃ በመቃወም ጽኑ አቋም አሳይተዋል፡፡
 • ገዳማት ተከብረው እንዲቆዩና በልማት ራሳቸውን እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በበሳል አመራር ሰጪነታቸውና በአስተዳደር ችሎታቸው የተመሰከረላቸው አባት ናቸው፡፡ በመኾኑም ይህን ክቡር ዓለም አቀፋዊና ብሔራዊ ሓላፊነት በብቃት ይወጡታል ብለን ስላመንን፣ በተሰጠን ዕጩ ፓትርያሪክ የመጠቆም መብት መሠረት ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ዕጩ ፓትርያሪክ ይኾኑ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የጠቆምን መኾኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ አንቀጽ 7 ንኡስ አንቀጽ 1/ሰ መሠረት÷ ከቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጆች መምህራንና ደቀ መዛሙርት ከእያንዳንዳቸው ሁለት፣ ሁለት መራጮች የሚወከሉ ሲኾን ከሁለቱ አንዱ የደቀ መዛሙርቱ ተወካይ ሌላው ደግሞ የመምህራኑ ተወካይ መኾኑ ተደንግጓል፡፡ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም በሦስት ገጽ አዘጋጅተው ለአስመራጭ ኮሚቴው ጽ/ቤት ያደረሱትና ለሐራዊ ምንጮች ያስታወቁት ጥቆማቸው፣ የኮሌጁ መምህራንና የተቀሩት ሁለት ኮሌጆች (ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ እና መቐለ ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን) መምህራንና ደቀ መዛሙርት ይስማሙበት ወይም አይስማሙበት አልተረጋገጠም፡፡

ስለ ኮሌጁ ደቀ መዛሙርት ጥቆማ አስተያየታቸውን የተጠየቁ የምርጫው ሂደት ታዛቢዎች እንደተናገሩት፣ በፓትርያሪክነት መመረጥ ስለሚገባው አባት በተማሪዎቹ የተዘረዘሩት መስፈርቶች በራሳቸው ጎጂዎች አይደሉም፡፡ ይኹንና የፓትርያሪኩን ሥልጣንና ተግባራት ከአባታዊና መንፈሳዊ ተግባሩ በላይ አብዝተውና አግዝፈው የተቋማቱን ሚና በመተካት የሚያስቀምጡ ናቸው፡፡ በምትኩ የተዘረዘሩት ሥራዎች በአመዛኙ ዘመን የተሻገራቸውን የቤተ ክርስቲያኒቷን የአመራርና የአስተዳደር ተቋማት በመገንባትና በማጎልበት፤ ተገቢና ትክክለኛ መዋቅር፣ ስትራተጂና ፖሊሲ ዘርግቶ ካህኑንና ምእመኑን በሰፊው በማሳተፍ ሊመለስ ይችላል ያሉት ታዛቢዎቹ፣ በመመዘኛነት የተጠቀሱት ተግባራት በዋናነት ለፓትርያሪኩ ግለሰባዊ(?) ብቃት የሚተዉ ከኾነ የቀድሞው ፓትርያሪክ ዐይነት አስተዳደራዊ ዐምባገነንት፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር መንሰራፋቱን እንደሚቀጥል አይጠራጠሩም፡፡

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል

ታዛቢዎቹ እንደሚሉት፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ ከተቀመጠው መመዘኛ መካከል በዕድሜያቸው አነስተኛው መነሻ – 50 ዓመት – ላይ ይገኛሉ፡፡ በጥቆማው የተዘረዘረው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የሥራ ፍሬዎችም የተወሰኑት በተጨባጭ፣ የተቀሩትም በዝንባሌ ደረጃ ሐቅ ወይም የሐቅ ጠረን ያላቸው ናቸው፤ ነገር ግን ጥቂቶቹ  በተለያዩ አጋጣሚዎች በጉልሕ እየተነሣ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ሲነቀፉባቸው የነበሩትን ትችቶች ያላገናዘቡ፣ የተለጠጡና ከራሳቸው ከደቀ መዛሙርቱ መመዘኛዎች ጋራ የሚጋጩ ነጥቦች አልታጡበትም – እንደ ታዛቢዎቹ አስተያየት፡፡

‹‹የተመረጠው ፓትርያሪክ አስቀድሞ ታውቋል፤ ምርጫው ለሽፋን ነው የሚካሄደው›› ስለሚለው ጥቂት የማይባሉ ወገኖችን ትችት በተለያየ መንገድ ከሚወስዱት ታዛቢዎቹ፣ የተወሰኑት÷ የመንግሥትን ፍላጎት ቀዳሚና ዐቢይ መወሰኛ በማድረግ ከሊቃነ ጳጳሳቱ ማንኛቸውም ለፓትርያሪክነት ቢታጩ/ቢመረጡ አብዛኞቹ ፈቃዱን/ተጽዕኖውን ሊጋፉት/ሊቋቋሙት እንደማይችሉ ስላረጋገጠ (በእነርሱ ቀጥተኛ አነጋገር – መንግሥት ጳጳሳቱን ዐውቆ፣ ንቆ ስለጨረሳቸው) የተመረጠው እንዲመረጥ እንጂ ወስኖ ያስቀመጠው የለም ይላሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ለፓትርያሪክነት እንደሚመረጡ አረጋግጠው ለሚናገሩትም፣ ታዛቢዎቹ÷ ብፁዕነታቸው አንዳንድ አቋሞቻቸው የማይገመትና ለመንግሥትም የሚያስቸግር መኾኑን በመጥቀስ ይኹንታ ማግኘታቸውን ይጠራጠራሉ፡፡ ሌሎችም ብፁዕነታቸው ለውጭ አካላት የማይገቱ አቋሞች ሊወስዱ እንደሚችሉ አምነውና ይህም በተጽዕኖ አሳዳሪዎች ዘንድ እንደማይወደድ ተቀብለው ሲያበቁ ነገር ግን የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅሞ ተገማች ያልኾኑ አቋሞቻቸውን በማቀብ በቦታው መቀመጣቸውን ሊፈቅድ እንደሚችል ይተነባሉ፡፡

Advertisements

11 thoughts on “የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ዕጩ ፓትርያሪካቸውን አሳወቁ

 1. ባልቻ February 14, 2013 at 4:28 pm Reply

  አቡነ ሳሙኤል (ልደቱ አያሌው) የማህበረ ቅዱሳን አሻንጉሊት በምንም ተዓምር አይመረጡም፡፡
  ምክንያቱም አቡነ ሳሙኤል የኢህአዴግ ተቃዋሚ ናቸው፡፡

 2. ሎሚ February 14, 2013 at 5:42 pm Reply

  ከአንድ መንድሜ ጋር ስንወያይ ከአመት በፊት አአቡነ ሳሙኤል በህዝብ ፊት መልካም ሰው እንዲመስሉ በህዝብ ፊት የተሰራውን ድራማ የሚገርም ነበር እና የረጅም ሰአት ውይይቶቻችን ሁሉ እሳቸው ከአቡነ ጳውሎስ በኋል ፓትርያርክ እንደሚሆኑ የሚጠቁም ነበር። እሳቸው በዛ በታቀደ ግርግር ወቅት በመጸሀፍት ተሰደቡ ከዚያ ደግሞ ተሞገሱ። ከዛ ድምጻቸው ጠፋ። አሁን ደግሞ ብቅ አሉ።

  እውነት እላችኋለሁ ከዚያች ቀን በኋላ ለአንዲት ቀን እሳቸው ቀጣይ እንደሚሆኑ ተጠራጥሬ አላውቅም። ይብላኝ ለእነርሱ ምንጋቸውን ለፖለቲካ አሳልፈው ለሰጡ። ይብላኝ ስለመንጋው ህይወት ለሚጠየቁት ለእነርሱ።

  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ።

 3. Anonymous February 14, 2013 at 7:51 pm Reply

  Ato balcha tikikl bilewal yemifelegew ye – sibehatina ye – abay tshaye ashangulit, MENFESAWI sayhon SEYITANAWI amelekaket yalew abat new.

 4. Martha February 14, 2013 at 11:06 pm Reply

  Yegermale Babune Poulos yetseruten hulu yaba sumel adregute. Ayemeretume.Egzeabehere Yayale.

 5. Chiqunu February 15, 2013 at 5:47 am Reply

  Abune Samuel do not have any quality whatsoever to be patriarch. MK should take care not to vote for such pop to be a patriarch only because he seems to support MK. There are others who are pro-MK with better personality, spirituality, capability and other qualities. Abune samuel is a corrupted person and i know that he was taking bribes from priests, deacons, church admins and even poor people living around churches. He is running after his benefits and will not regret to scarify MK after he took his power. He has no continuity in his stands which is a dangerous behavior for a christian father. Let us focus on elder fathers with better experiences and personality such as impartiality, continuity, with real fear of God (not others) and respect to the Christians (to humans in general) besides clear vision to develop and advance the services in the church.

 6. gg February 15, 2013 at 12:32 pm Reply

  Guys, Do you know what you are writing about? I think it is about spirituality. but your words are words of devil. is it fair to call father ‘buchila’? what a hell are you writing? please analyze and write in the sound of Christianity. otherwise take away your hand from the church.

 7. MENAFQU February 16, 2013 at 5:15 am Reply

  WHY DON’T WE HAVE POPE FROM COPTS. I BELIEVE ETHIOPIANS DON’T HAVE ABILITY TO BE POPE AS STATED IN FITHA NEGEST.

 8. Haymanot Rtet February 16, 2013 at 6:02 am Reply

  Guys, How do you dare about the fathers who declined the opportunity of making peace? Who defied the history of the Holy Church by avoiding reconciliation which is one moral standard of a father in a church?

  How could you think the Holy Spirit will be amongst such fathers and let them do His will. Where is the throne of the Holy Spirit with in the Synod? Let’s pray first for the unity of the church. I know some will disagree by arguing reconciliation is a past history. Believe me this is the house of God. He can avert any thing to nothing and the vise versa. He is the Lord of Miracles.

  Let’s keep on praying. Do not bother for the “selection” of patriarch. It is already known who is assigned (not elected) to be the “patriarch”. All the process is ceremonial. All is cover up….

 9. tewahdo February 16, 2013 at 8:17 am Reply

  መናፈቃን ምነዉ ተረበሿችሁ ተጠቃሚዎቹም፡ተጎጂዎችም፡አኛዉ፡ስለሆንን፡ ሁሉንም፡ለኛዉ፡ተዉልን፡፡

 10. wondo February 16, 2013 at 1:22 pm Reply

  Yemayew comment hulu Yegermal yemiseten endemigeban endeserachen new wededenm telanm

 11. Anonymous February 17, 2013 at 8:45 am Reply

  aba samuel is unknown and has hidn agenda. pls don’t be fulish he will be the challeng of the holly senod fathers & MK.why he dislike ETTA Selection System? b/s for his personal motive to be a patriarich. to aggitate mobilize others.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: