የአስመራጭ ኮሚቴው መርሐ ግብር የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡን የጣሰ ነው

 • የኮሚቴው መሪ ዕቅድ የጸደቀው በቋሚ ቅ/ሲኖዶስ መመሪያ መሠረት አይደለም
 • በዕጩዎች ላይ የሕዝብ አስተያየትና ጥያቄ የማስተናገጃው ጊዜ 15 ቀን አይሞላም
 • የኮሚቴው ሰብሳቢ ከመግለጫው ቀን በፊት በኮሚቴው ስብሰባዎች አልተገኙም

የስድስተኛውን ፓትርያሪክ ምርጫ እንዲያስፈጽም የተሠየመው ኮሚቴ፣ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው መግለጫ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡንና ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ የሰጠውን መመሪያ የጣሰ መኾኑ ተገለጸ፡፡

‹‹፮ው ፓትርያሪክ የሚሾሙበትን ቀንና የምርጫውን ሂደት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ ለማድረግ›› በሚል ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ÷ ምርጫውን የሚያስፈጽምበትን መሪ ዕቅድ ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ አቅርቦ እንዳጸደቀ ጠቅሶ ነበር፡፡ ይኹንና የመንበረ ፓትርያሪኩ ሐራዊ ምንጮች ዘግይተው እንዳስታወቁት፣ የኮሚቴው መሪ ዕቅድ በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ መሠረት÷ ኮሚቴው በተቋቋመ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማሰናዳት የሚገባውን ዝርዝር የድርጊት መርሐ ግብር ለቅዱስ ሲኖዶሱ አቅርቦ ሊታይና ሊወሰንበት ይገባ ነበር፡፡ በዚህም አገባብ ተፈጻሚ እንዲኾን ኮሚቴው በቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ መመሪያ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ነገር ግን ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በኮሚቴው ይፋ የተደረገው መሪ ዕቅድ በሕገ ደንቡ መሠረት ቅ/ሲኖዶሱ ያላየውና ያልወሰነበት እንደኾነ ነው ምንጮቹ የሚያስረዱት፡፡

መግለጫው በተሰጠበት ዕለት ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩና ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ሌላ ከመግለጫው ጋራ ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላቸው አምስት ያህል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአዳራሹ ተገኝተዋል፤ የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ግን በአካባቢው ጨርሶ አልታዩም፤ ይህም የኮሚቴው የድርጊት መርሐ ግብር እና አካሄድ ከቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት ዕውቅናና ቁጥጥር ውጭ ለመኾኑ  በአስረጅነት ተጠቅሷል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣንና ለአስመራጭ ኮሚቴው በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ በተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት (የኮሚቴውን ሊቃነ መናብርት የመሠየም፤ የዕጩ ፓትርያሪኮችን የማጽደቅ፤. . .) ዙሪያ በኮሚቴው አባላት መካከል ክርክሮች ተነሥተው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

asmerach com

የአስመራጭ ኮሚቴው መግለጫ ሲነበብ

ምንጮቹ የሚያቀርቡት ተጨማሪ አስረጅ፣ የምርጫው ሂደት ዕዝና ቁጥጥር በሌላ እጅ ስለመውደቁ ይጠቁማል፡፡ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በሕገ ደንቡ መሠረት በቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ኾነው ተመርጠዋል፡፡ በተሰጣቸው ሓላፊነት መሠረት ግን የኮሚቴውን ስብሰባዎች በመንበረ ፓትርያሪኩ ተቀምጠውና በጽ/ቤቱ ተገኝተው አልመሩም፡፡ በመግለጫው ላይም ተገኝተው ጋዜጣዊ መግለጫውን ያነበቡት ከሀገረ ስብከታቸው ዕለቱኑ ተጉዘው እንደገቡ ነው፡፡ ብፁዕነታቸው በመንበረ ፓትርያሪኩ እንዲገኙና መግለጫውን እንዲያነቡ የተደረገው ‹‹በወረደላቸው ቀጭን ትእዛዝ ነው›› ይላሉ የዜናው ምንጮች፡፡ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ግን በውሳኔያቸው የጸኑ ይመስላሉ – ከሀ/ስብከታቸውም ንቅንቅ አላሉ፡፡

በሌላ በኩል፣ የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ባወጣው የምርጫ መርሐ ግብር መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም በኮሚቴው በሚያቀርብለት ዕጩዎች ላይ ተስብስቦ በመወያየት የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ለዕጩ ፓትርያሪክነት የታመነባቸውንና ይኹንታ ያገኙትን አምስት አባቶች ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፤ ከሦስት ቀናት በኋላ የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ይካሄዳል፡፡ ይህ የምርጫ መርሐ ግብር በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ 2/ሰ ከተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ጋራ የሚጣረስ ነው፡፡

በሕገ ደንቡ መሠረት÷ አስመራጭ ኮሚቴው ለፓትርያሪክነት ይበቃሉ ያላቸውን ዕጩዎች ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ ለ15 ቀናት ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፤ በእነዚህ ቀናት ውስጥም በዕጩዎች ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ካሉ ይቀበላል፡፡ በዚሁ ንኡስ አንቀጽ ፊደል ተራ ቁፅር (ሸ) እንደተመለከተው÷ ኮሚቴው ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን ዕጩዎች የመጨረሻ ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፣ ችሎታቸውና ልምዳቸው ጋራ ለሕዝብ የሚገልጸው፣ የምርጫውን ቀንና ቦታም የሚያስታውቀው ከሕዝብ የሚቀርቡለትን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ መርምሮና አጣርቶ የሚቀበለውን ከተቀበለ፣ የማይቀበለውን ከጣለ በኋላ መኾን ይገባው ነበር፡፡

ኮሚቴው ጥር 30 ቀን ይፋ ባደረገው የምርጫ መርሐ ግብር ግን፣ ዕጩዎቹን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ከማቅረቡ በፊት የ15 ቀናት ይፋዊ ጊዜ በመስጠት በዕጩዎቹ ላይ ከካህኑና ምእመኑ ጥያቄና አስተያየት እንደሚቀበል የሚያመለክት የሥራ ዕቅድ የለውም፡፡ በምትኩ እንዲሁ በደፈናው ‹‹ስድስተኛው ፓትርያሪክ ሊኾን ይገባል የምትሉትን በአካል በመቅረብና በፋክስ በመላክ ጠቁሙ›› ብቻ በማለት ነው ያስታወቀው፡፡ ይህም ኾኖ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የታዩ ጥቂት አስተያየቶች፣ በአንድ በኩል ዕጩ ለመጠቆም የተሰጠው የስምንት ቀናት ጊዜ በቂ እንዳልኾነ ሲተቹ በሌላ ወገን ደግሞ ለፓትርያሪክነት ብቁ ናቸው ያሏቸውን የራሳቸውን ዕጩዎች ዝርዝር በማቅረብ እገሌን ወይም እገሌን ብንመርጥ ማለት ጀምረዋል፡፡ በነገሩ ሁሉ ‹‹የገዘፈ ግፍ››ና በርካታ እንከን እንዳለ ከሚያምኑቱ ወገን እንኳ ‹‹ጥሩ አባት ለማስመረጥ ታሪካዊ አጋጣሚው አይለፈን›› በሚል ይኾናል፤ ይበጃል ላሉት አባት ግልጽ የምርጫ ዘመቻ ውስጥ የገቡም አሉ፡፡

የኾነው ኾኖ የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የካቲት 16 ቀን የሚወያይባቸው ዕጩዎች÷ ካህኑና ምእመኑ እንደ ዕጩ ፓትርያሪክ ለይቶ የማያውቃቸው፣ በጥያቄና አስተያየት ያልተቻቸው ሊኾኑ ነው እንግዲህ፡፡ በምርጫ ሕገ ደንቡ አንቀጽ 3 ንኡስ አንቀጽ 2 እና 3 እንደተደነገገው ግን የሕገ ደንቡ ዓላማዎች፡- ‹‹በካህናትና ምእመናን ዘንድ አመኔታ የሚኖረው ቋሚና ወጥ የኾነ የቅዱስ ፓትርያሪክ ምርጫ ሥርዐት›› ስለማስፈን፤ ካህናትና ምእመናን በግልጽ የሚያውቁትና በመተማመን የሚሳተፉበት የምርጫ ሂደት እንዲኖር›› ስለማድረግ ነበር፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት በዓለም ዙሪያ የሚሰማው የዕርቁ ይቅደም አቤቱታ እንዳለ ኾኖ የገዛ ሕገ ደንቡን እንኳ ያላከበረው የምርጫ አስፈጻሚዎች ጥድፊያ ጥቂት የማይባሉ ታዛቢዎችን÷ የምርጫው ሂደት እንዲያው ለአጃቢነት የሚካሄድና ስድስተኛው ፓትርያሪክ አስቀድሞ የተወሰነ መኾኑን ክፉኛ እንዲጠረጥሩ፣ መጠርጠር ብቻ ሳይኾን እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡ ‹‹የተያዘው ማስመረጥ ሳይኾን ማስቀመጥ ነው›› ይላሉ አንድ ሓራዊ አስተያየት ሰጪ፡፡ ግእዝ በመሥመር ላይ የጡመራ ብሎግ ለነ አባ እንቶኔ የካቲት ማርያምን በማስታወስና ምርጫው ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱን ለጥፋት ኀይሎች አሳልፎ የሚሰጥ›› እንደኾነ በመግለጽ አስፈጻሚዎች ‹‹ከማደናገሪያ ሽር ጉድ›› እንዲጠበቁ አሳስቧል፡፡

Advertisements

4 thoughts on “የአስመራጭ ኮሚቴው መርሐ ግብር የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡን የጣሰ ነው

 1. Agew February 13, 2013 at 6:46 am Reply

  Do you think that you are helping the church by doing such oversimplified analysis? In my opinion you want to perpetrate the division and guiding the laity for further division and hence demise of the church.

  When someone faces such trying times, he/she search for a mechanism by which one passes the challenge without harming the individual or the institute. But if you over emphasize on negatives, little details and openings the result is more division, the followers loose trust on the church and finally this will drive the people out of the church. Then mission accomplished for people like you. Nothing else!!! I am not sure what other workable proposal you have (considering the present quagmire from both sides) for the church and election pf the patriarch.

  I am sorry if you are really from the church. However, if you are from the other part, you are here for a purpose.

 2. andadirgen February 13, 2013 at 9:28 am Reply

  ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ

 3. Chiqunu February 13, 2013 at 11:25 am Reply

  I have read the the election guideline from MK website. The question is what MK is doing when the guideline is over looked ? MK was boasting as a guardian of the church’s Kenona and we have witnessed a lot of actions that are against the the church’s canona and guidelines. Hence, at least MK should not be part of the process by electing the new patriarch as the process is led by undercover politics and it is clear who will finally win. Hence, MK should-not act like fool opposition parties who are being used as the election was democratic.

 4. Haymanot Rtet February 14, 2013 at 5:58 am Reply

  Dear Chiqunu:

  I think you should be informed that MK (only the Management, not the members in general) is one of the perpetrators of the reconciliation process. Moreover being member of the so called “electoral committee”, being represented by one silly person, it is trying its best to create another historical mess on the Holy, United and One Church.

  If you are member of MK, please do not get angry rather try to shape your organization, discuss the issue with brothers and sisters. The so called amerar, should be responsible.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: