የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ መርሐ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች

የ፮ው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ዛሬ፣ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ቡራኬ ሥራውን እንደጀመረ ያስታወቀውና በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሰብሳቢነት የሚመራው አስመራጭ ኮሚቴው፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጠው ባለዘጠኝ ነጥብ ጋዜጣዊ መግለጫ ለ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ ሂደት የወጣውን የምርጫ መርሐ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡

በዐቃቤ መንበሩ ጸሎት የተከፈተው የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫው አስፈላጊነት÷ ‹‹የምርጫውን ሂደትና 6ኛው ፓትርያሪክ የሚሾሙበትን ቀን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ ለማድረግ›› እንደኾነም ተመልክቷል፡፡

ኮሚቴው ባወጣው የምርጫ መርሐ ግብር መሠረት፡-

 • እግዚአብሔር የወደደውን በመንበሩ ያስቀምጥ ዘንድ ከየካቲት 1 – 8 ቀን የጸሎት ጊዜ ነው፡፡
 • ከየካቲት 1 – 8 ቀን ከሊቃነ ጳጳሳት መካከ ከካህናትና ምእመናን ይፋዊ የዕጩ ፓትርያሪክ ጥቆ በአካል በመቅረብና በፋክ ይካሄዳል፡፡
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአስመራጭ ኮሚቴ ተጣርተው በቀረቡለት ዕጩ ፓትርያሪኮች ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ለመወሰን የካቲት 16 ቀን ይሰበሰባል፡፡
 • በአስመራጭ ኮሚቴው ቀርበው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን ይኹንታን ያገኙት አምስት ዕጩ ፓትርያሪኮች የካቲት 18 ቀን 2005 ዓ.ም ለሕዝብ ይፋ ይደረጋሉ፡፡
 • የ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ ኀሙስ የካቲት 21 ቀን ተካሂዶ በዚሁ ዕለት ምሸት 12፡00 የተመረጠው አባት በብዙኀን መገናኛ ይፋ ይደረጋል፡፡
 • የተመረጠው አባት በዓለ ሢመት የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያን መሪዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ የኢ/ኦ/ተ/ቤያን ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል፡፡

ሌሎች የመግለጫው ዐበይት ነጥቦች፡-

 • አስመራጭ ኮሚቴው መሪ ዕቅዱን ለቋሚ ሲኖዶስ አቅርቦ አጸድ     ቋል፡፡
 • በምርጫ የሚሳተፉት ብ    ፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራት፣ ካህናትና ምእመናን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንዲሁም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ጠቅላላ ቁጥር 800 ነው፡፡
 • የ6ው ፓትርያሪክ መራጮች ቁጥር ካለፉት አምስት የፓትርያሪክ መራጮች ቁጥር ጋራ ሲነጻጸር በእጅጉ የላቀ ነው፡፡
 • በውጭ የሚገኙ ካህናትና ምእመናን ለዕጩ ጥቆማ በፋክስ ቁጥር 011- 156-77-11 እና 011-158-0540 መጠቀም ይችላሉ፡፡
 • የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በወሰነው መሠረት የአራቱ አኀት አብያተ ክርስቲያን፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያን ማኅበር፣ የአፍሪካ አብያተ ክርስቲያን ም/ቤት ተወካዮች እና በቋሚ ሲኖዶስ የሚመረጡ ምእመናን የአስመራጭ ኮሚቴ በሚሰጣቸው ልዩ መታወቂያ ምርጫውን እንዲታዘቡ ይጋበዛሉ፡፡
 • ከብፁዓን ሊቃ ጳጳሳት፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ሠራተኞች፣ ከአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ከሰንበት ት/ቤት እና ከማኅበረ ቅዱሳን የተውጣጡት 13 አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ የተቋቋመው ታኅሣሥ 10 ቀን ነው፡፡

በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ የተገኙት የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት፡-

asmerach com

ፎቶ ማኅበረ ቅዱሳን

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ (ሰብሳቢ)፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ (ምክትል ሰብሳቢ)፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (አባል)፣ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ (ጸሐፊ)፣ መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን ገ/ጻድቅ፣ ጸባቴ ኀይለ መስቀል ውቤ፣ ንቡረ እድ አባ ዕዝራ ኀይሉ፣ አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ፣ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድ፣ አቶ ታቦር ገረሱ፣ አቶ ባያብል ሙላቴ (ጋዜጣዊ መግለጫውን አስተናብረዋል) እና ዲያቆን ኄኖክ ዐሥራት ናቸው፡፡

ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከልም ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ተገኝተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው መጨረሻ የተለያዩ ስሜቶች ተነበዋል፤ ተደምጠዋል፡፡ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች መርሐ ግብሩ በእጅጉ የተቻኮለ መኾኑን ከመተቸታቸውም በላይ ተመራጩ አስቀድሞ መታወቁን ሲነጋገሩ ተሰምተዋል፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይመልከቱ

 

Page 01page 02page 03page 04  page 05

Advertisements

8 thoughts on “የ፮ኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የምርጫ መርሐ ግብር ዋና ዋና ነጥቦች

 1. Anonymous February 7, 2013 at 7:34 pm Reply

  PATRIYARIC ****KELQEDON**** Le-2gna gize Ye-Mimenan rasmitat,ye-BETEKIRISTIAN kancer liseyemu new!!!!

 2. hailu February 7, 2013 at 11:51 pm Reply

  Assembly of gangsters convened to do just another blander on our mother church.
  It was illegal 21 years ago when the late Aba Paulos was assigned, and it is even shamfully illegal now to assign a 6th cadre patriarch.

  The legitimate Patriarch remains His Holiness Abune Merkorios according to the church’s cannon law.

 3. anonymous February 8, 2013 at 5:34 am Reply

  አይ ማኅበረ ቅዱሳን አየር ላይ ቀረቻ! በጎን በሚድያ እርቅ ይቅደም በጎን ደግሞ በፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ በካድሬዋ ተወክላ በሁለት ቢላ ስትከትፍ ስትከትፍ ቆይታ አሁን ከመራጮች ዝርዝር ውጭ ሆነች። ለስሙ ከተለያዩ አካላት በሚለው ዝርዝር ውስጥ ከማኅበሩ አባላትም እንደሚገኙ ያመልክይ እንጂ በተራ ቁጥር 6 የመግለጫው ነጥብ ላይ በዐቢይ ዘርፍ ተዘላለች። ያው በተለያዩ ጉድጉዶች በሂደት አራት ከሰንበት ትምህርት ቤት የሚለው ተከፍሎ ይሰጣት መባሉ አይቀርም። እየከፈሉ መውሰድ እየቆረሱ ማቆርቆዝ አይሆንም ትላላችሁ። ለስሙ ተወካይ አላት ተባለ። ምን ሲሠራ ከርሞ ነው ቢያንስ ሁለት ከማቅ ሳያስብል የቀረው?

 4. Anonymous February 8, 2013 at 8:44 am Reply

  maninebm akateh malet new

 5. Anonymous February 8, 2013 at 1:51 pm Reply

  አለማወቅ ሀጢያት አይደለም 53 ሀገረ ስብከት አለ 53 * 12=636 የቀረው የማን መስሎህ ነው?ዋናው እግዚአብሔር የወደደውን ነው የሚመርጠው ማህበሩን ለቀቅ አድርጉት

 6. Anonymous February 9, 2013 at 6:46 am Reply

  u are a lost sheep. u don’t know what u are talking!! what do u expect from MK? Just a blind hate!!

 7. Anonymous February 9, 2013 at 8:08 am Reply

  በዚሁ መግለጫ በገጽ ሁለት ላይ “በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 17 ቁጥር 2 መሰረት “የቤተክርስቲያኗ መሪ በሞት በሚለዩ ጊዜ ከአርባ እስከሰማንያ ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ አዲስ ፓትርያርክ ይመረጣል” ይላል። ከዚህ በተጨማሪም ይህ ሕግ ቤተክርስቲያኗ አምስት ፓትርያርኮችን ስትመርጥ እንደተሰራበት በመግለጽ አሁንም ስድስተኛው ፓትርያርክ የሚመረጠው በዚሁ ሕግ መሰረት እንደሆነ ያትታል።
  ነገር ግን አምስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ የተመረጡት 4ኛው ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዪስ በሕይወት እያሉ ነውና ይኸው ቤተክርስቲያኗ አምስት ፓትርያርኮች ስትመርጥ ተግባራዊ ተደርጓል የተባለውን ሕግ አፈፃፀም ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል።
  በተጨማሪም የአስመራጭ ኮሚቴውን አባላት የሆኑት የሰንበት ት/ቤት እና የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮቹ› ከተቋሞቹ ዕውቅና ውጭ የተመረጡ እንደሆነ ይነገራል። በተለይም የማሕበረ ቅዱሳን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነው አቶ ባያብል ሙላቴ ማህበሩ በይፋ ወክሎና መርጦ የላከው ሰው መሆን አለመሆኑ በሚመለከተው አካል አለመረጋገጡ የማህበሩን አቋም ጥያቄ ውስጥ የከተተው ነገር ሆኖ ተገኝቷል። እናንተስ ምን አያችሁበት?

 8. Anonymous February 9, 2013 at 8:35 am Reply

  ለማኅበረ ቅዱሳን አባ ሳሙኤል ይሻሉታል ወይስ አባ ማቴዎስ? ስውር ጫወታው እዚህ ላይ ነው። በየትኛው እንደሚጠናቀቅ ለጊዜው እልባት ላይ አይድረስ እንጂ የሩጫው መቋጫ ከሁለቱ ባንዱ ላይ ይደመደማል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: