ቅ/ሲኖዶስ ስለ ዐራተኛው ፓትርያሪክ፣ ዕርቀ ሰላምና ስለ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች

 1. ሥልጣነ ፕትርክና ሲፈልጉ ተረከቡኝ፣ ሲፈልጉ መልሱኝ እየተባለ የሚከራከሩበት ሥልጣን ባለመኾኑ ዐራተኛውን ፓትርያሪክ ወደ መንበረ መመለስ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ውስጥ ሥርዐተ አልበኝነት እንዲሰፍን መፍቀድ ነው፡፡ ከዚህም ጋራ አምስተኛው ፓትርያሪክ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው የተሠራው የኻያ ዓመታት ሥራ ደምስሶና ሠርዞ ወደኋላ በመመለስ ዐራተኛው ፓትርያሪክ ብሎ መቀበል ፍጹም የማይቻል በመኾኑ፣ የቀድሞው ዐራተኛ ፓትርያሪክ በፓትርያሪክነት የሥልጣን ደረጃ እንደማይቀበል ቅዱስ ሲኖዶስ በማያሻማ ኹኔታ በድጋሚ ወስኖአል፡፡
 2. ቤተ ክርስቲያን በአሁን ጊዜ ከዚህ በላይ ያለመሪ ለብዙ ጊዜ እንድትቆይ ማድረግ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥራዋ እንዲስተጓጎል፣ መልካም አስተዳደሯም እንዲዳከም የሚያደርግ ስለኾነ ቀደም ሲል በተወሰነው መሠረት የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ቤተ ክርስቲያንነና ቀኖናው ተጠብቆ የምርጫው ሂደት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡
 3. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም የሰላምና የአንድነት መሪ እንደመኾኗ    መጠን የተጠቀሱት አባቶች የተሰጠውን የሰላም ዕድል ተጠቅመው ወደ ሰላሙና አንድነቱ ለመምጣት ፈቃደኞች ኾነው እስከተገኙ ድረስ ኹኔታዎች ሲመቻቹ ቀደም ሲል የተጀመረውን የሰላምና ዕርቅ ሂደት እስከመጨረሻው ድረስ ለማስቀጠል አሁንም ቤተ ክርስቲያናችን ዝግጁ መኾኗን ቅዱስ ሲኖዶስ በማረጋገጥ ጉባኤውን አጠናቋል፡፡

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ይመልከቱSynod Decision 001Synod Decision 002Synod Decision 003Synod Decision 004Synod Decision 005

Advertisements

5 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ ስለ ዐራተኛው ፓትርያሪክ፣ ዕርቀ ሰላምና ስለ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች

 1. Yenegewsew January 16, 2013 at 7:13 pm Reply

  Where is the seal? One more question …why it was given by Abune Abreham?…it should be by Abune Ezikeal…is weyane playing game?

 2. ግእዝ በመሥመር-ላይ January 17, 2013 at 1:23 am Reply

  ዕሺ፥በጎ፥ በጄ፥ ይኹን፥ አደርጋለኊ ማለትን ብቻ ሳይኾን፤ እንቢ፥ አሻፈረኝ፥ አልስማማም፥ አልቀበልም፥ አይኾንም፥ አይኹን ማለትንም ታዘናል፦ “ኦሆ በልዎ ለእግዚአብሔር፤ ወእንብየ በልዎ ለጋኔን!” (ያዕ 4፡7)

  ይህም በጨዋ ዐማርኛ እንዲህ ማለት ነው፦ “እ[ኽ]ንቢ በል!… እ[ኽ]ንቢ በል!” እንቢታውም ጋኔኑን ብቻ ሳይኾን፤ ጋኔን ያደረበትን ዐላዊ ኹላ ነው።

 3. T/D January 17, 2013 at 1:18 pm Reply

  Dear Hara Zetewahido,

  I appreciate the way you narrate this news. I propose that you guys give lesson to other ‘blogs’. Among all I appreciate that your unbaised reporting style.

  Keep it up.

 4. Tell January 17, 2013 at 10:26 pm Reply

  በአሁኑ ወቅት በተፈጠረ ውኔታ አንዳንድ አስተያየቶች እውነታው ሳያገናዝቡ በጭፍን ተቃውሞን ብቻ ስለሚያስተጋቡ የሚከተለውን እንድጽፍ አነሳሳኝ።-

  ስለአለፉት 20 አመታት፦
  + ወደዋላ ተመልሰን አቡነ መርቆሪዎስ እንዴት ከፓትሪያርክነት እንደተለዩ መማገት የለብንም፤ ሆኖም ግን የተለያዩ አስተያየቶች መልሰው በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ስለሚያጠነጥኑ ከእውነታዎቹ በመነሳት የሚከተለውን ማለት ፈቀድኩ። አዎን በታምራት ላይኔ(በመንግስት-“በወያኔ”) ተጽኖ የቤተክርስቲያኗ በጀት ከመንግስት እንዲለቀቅ ሲባል አሁን ከሳቸው ጋር ያሉት ጭምር ተስማምተው ፕትርክናውን “እንዳስረከቡ ” የወቅቱን መረጃ ያዩ ወገኖች የሚተነትኑት ጉዳይ ነው። ፓትሪያርክነት ደግሞ መንጋን የመጠመቅ ስራ ስለወነ፤ እንደዙፋን አንዴ እሺ እያሉ የሚለቁት ሌላ ጊዜ ደግሞ የሚናፍቁት ወንበር አይደለም። እውነተኛ የመንጋ ጠባቂ ነፍሱን ስለልጆቹ ነፍሱን አሳልፎ ይሰጣል እንጂ እያወቀ ለቤተክርስቲያን መከፈል ምክንያት አይወንም። (ማንያወቃል አባታችን ከ20 አመት በፊት ስለቤተክርስትያን ብለው ፓትራሪክነታቸውን አሳልፈው ሰጥተውስ ቢዎን)።

  ከነዚህና ከሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ወደመንበራቸው ይመለሱ የሚለው ሙግት፤ እውነታዎችን ያላገንዘበ ለቤተክርስቲያን ያለወገነ ጭፍን አመለከከት ነው።

  ስለአሁኑ ወቅት፦
  ከቀናት በፊት ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነው ወሳኔ እውነታውን ያገናዘበ ይመስላል ምክንያቱም በውጭ ያሉት አባቶችን ወደ ሂደቱ አስገብቶ አብሮ የሚቀጥለውን አባት ለመምረጥ የወሰነ ስለወነ። ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ ወገኖች ይህ ወሳኔ የሰላሙን ሂደት ይበልጥ የሚያጠናክረው እንደወነ ይገነዘባሉ። እናም በውጭ ያሉ አባቶች ያለፈው አልፎአል ብለው ለቤተክርስትያን ቅን መሪ እግዚያብሄር እንዲሰጥ ከአገር ቤት አባቶች ጋር አብረው ለመስራት መነሳት አለባቸው።

  ስለወደፊቱ፡-
  ቤተክርስቲያን ከአሁን በዋላ የሚያስፈልጋት ዘመኑን የዋጀ በሁለት በኩል የተሳለ የአለምና የአካባቢያችንን ሁለንተናዊ ሁኔታ የተረዳ ፤የቤተክርስቲያንን ተልእኮ የማስፈጸም እና የማስተዳደር ጸጋ ያለው ቅን መንፈሳዊ አባት ነው። ስለወነም ዘር፤ቀበሌ፤አካባቢ በክርስትያኖች ዘንድ ቦታ ሊኖራቸው አይገባም።

  የማይረባ ከንቱ፤ ሃይላችንን ያባከነ ያለፉት 20 አመታት ትርፍ የሌለው ክርክር ከእንግዲ ወዲህ ሊቆም ይገባል። ከማንም ወገን ይሁኑ ዘረኞችን እና ፖለቲከኞችን ይብቃቹ፤ ቤተክርስቲያን ለክርስቶስ ወንጌል ሜዳ ነች ልንላቸው ይገባል።

  እስቲ ከግብጽ ቤተክርስቲያን እንማር እንሱ ከአፍሪካ እስከ ላቲን አሜሪካ ለሰው ዘር ሁሉ መዳን ብለው ይሰራሉ ። እኛ ግን በሰሜን አሜሪካ ጠቅምጠን ከቀዬአንችን ያለውን ሰው እየፈለግን እንቆጥራለን፤ እንሾማለን ። በአንድ ወቅት በአንድ የውጭ ብሎግ ላይ አንዲት አፍሪካዊት ለምን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያ ሃዋሪያዊ ተልእኮ ለአፍሪካዊያን ወንደሞቻችን እንደማታደርስ መጠየቋን ማንቤን አስታወሳለው። በእውነት ግን መቼ ነው የኬንያ፤ የሱዳን፤የዛየር፤የጋና፤የጀማይካ… ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት እንዲቋቋሙ የምንረዳውና ሃዋርዊ ተለኮ የምናደርገውስ? ጌታ ያለን እኮ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በስሜ እያስተማራቹ ..እያሳመናቹ…እያጠመቃቹ ደቀምዛሙርቴ አድርጉ ነው። አንድ አባት ለምን መንበር ላይ አልተቀመጡም እያልን ዋናውን የክርስትና አላማ እየረሳን እንዳይሆን መንጠንቀቅ አለብን።
  እስቲ አዲስ አበባ(ኢትዬጵያ)ስትሄዱየ አህዛብ የአምልኮት ስፍራዎችን እንዴት አዳዲስ እንደወኑ ተመልከቱ፤ መርካቶም ሂዱና ማን ንግዱን እንደትቆጣተረው፤ ስንትም ክርስቶስንና ወገኖቹን የሚሰድብም መጻፍት ገበያ ላይ እንዳለ አስተውሉ። ከአዋሳ እስከ ላንጋኖ(ሶደሬ) ፤ ለምን ቤተክርስቲያን እንደሌለ ግን በሳውዳረቢያ ቋንቋ ብቻ ደጃቸው ላይ የተጻፈባቸው ብዙ ህንጻዎች መንገድ ዳር እዳቆጠቆጡ እዩ። ባህርዳርም እንደገባቹ ቅ.ጊዮርጊስ ቤ/ክ እስከምትደርሱ ስንት አዳዲስ የአህዛብ ህንጻዎች እንዳሉ ተመልከቱ። ለምንስ ባላፉት 20 አመታት የቤተክርስቲያ አባላት ቁጥር(በመቶኛ) ቀነሰ ብላቹ እራሳቹን ጠይቁ? ከነዚ ሁኔታዎች የምንረዳው፤ ጊዜው፦ የቤተክርስቲያን ልጆች ተባብረው በፍቅር ከመቼውም ይልቅ የሚሰሩበት እንጂ አንድ አባት ለምን መንበር ላይ አልተቀመጡም ብሎ የቤተክርስቲያ ሃይል የሚባክነበት አይደለም።

  ሃዋሪያው ቅ. ጳውሎስ በአንድ ወቅት እንዲ አለ… በጠላቶች ፈተና…በሃሰተኛ ወንድሞች ፈተና፤ እናም ቤተክርስቲያናችን እንደርሱ እየተፈተነች ይመስለኛል። ከቱርክ፤ ከሶሪያ፤ ከፍልስጤም፤ከየመን፤ ከሳውዲ ከነበሩ የቀድሞ ክርስቲያኖች እንማር፤እናስተውልም። አዎን ፤ አንተ የተኛ/ሽ ንቃ/ቂ! ያለሽ ይመስልሻል ተበልተሽ አልቀሻል የተባለው ወደኛ ሳይመጣ፦ አንተ የተኛ ንቃ!

  በክርስቶ ወንድማቹ ከካናዳ።

  • Ben January 19, 2013 at 2:32 pm Reply

   @ tell
   እግዚአብሄር ይባርክህ።
   የአዋሳውን በግራና በቀኝ በአረብኛ ብቻ የተፃፈ አይቼ እያዘንኩ ነበር የሄድኩት። አማርኛ ቀርቶ በአካባቢው ቋንቋ እንኳን መፃፍ አይፈልጉም።
   ስለ አቡነ መርቆርዩስም ያልከው በጣም ትክክል ነህ። ለሁሉም ልቦና ይስጣቸው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: