ሰበር ዜና – ዐቃቤ መንበሩ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸው ተሰማ

  • ዕርቀ ሰላሙንና የፓትርያሪክ ምርጫውን በተጓዳኝ እንዲካሄድ ለማስወሰን ታስቧል
  • ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉት አባቶች አቋምና ብዛት እየተጠናከረና እየጨመረ ነው
  • የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቅዱስ ሲኖዶሱ ደብዳቤ ጽፏል
  • ከ4ው ፓትርያሪክ ጋራ ፊት ለፊት መወያየት ቀጣይ የመነጋገሪያ ነጥብ ነው ተብሏል

ቅ/ሲኖዶስ በነገው ዕለት አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ለመቀመጥ በሚዘጋጅበት ዋዜማ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ በይፋ መጠየቃቸው ተሰማ፡፡ ዐቃቤ መንበሩ ጥያቄውን ያቀረቡት ለመንግሥት አካል በጻፉት ደብዳቤ ነው ተብሏል፡፡ ደብዳቤው የተጻፈው ሁለት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት (አቶ ኣባይ ፀሃዬ እና ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም) በሳምንቱ መጨረሻ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ቢሮ ተገኝተው ከተወያዩ በኋላ መኾኑ ተገልጧል፡፡

ጥያቄው ስለቀረበበት ምክንያት የዜናው ምንጮች ሲያስረዱ÷ ‹‹ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ›› በሚል ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ የሚደረገውን ዝግጅት በሚቃወሙ ብዙኀን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ከፓትርያሪክ ምርጫው ጋራ ግንኙነት የለውም፤ ሁለቱም በተጓዳኝ/በትይዩ ሊከናወኑ ይችላሉ›› በሚሉ ጥቂት ነገር ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው በሚባሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በተያዘውና ከዕለት ወደ ዕለት እየተካረረ በመጣው ፍጥጫ ሳቢያ ነው ብለዋል፡፡

ከቅ/ሲኖዶስ አባላት አልፎ የአገልጋዩና ምእመኑ አጀንዳ የኾነው የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት እንዲሁም ቀጣይ አመራር ጉዳይ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ አቋም በማራመድ የሚታወቁትን ብፁዓን አባቶች (ለመጥቀስ ያህል÷ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልንና ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን) ሳይቀር በተለያየ ጎራ ያሰላለፈ መኾኑ ለጉዳዩ ክብደት በአስረጅነት ተጠቅሷል፡፡

የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ፣ ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም በጽርሐ መንበረ ፓትርያሪኩ ሲጀመር የምልአተ ጉባኤው ቀዳሚ አጀንዳ የዕርቀ ሰላሙ ቀጣይነት እንደኾነ ተነግሯል፡፡ በነገው አስቸኳይ ስብሰባ ከኅዳር 26 – 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ በተደረገው ሦስተኛው ዙር ጉባኤ አበው ላይ የተሳተፈው የዕርቀ ሰላም ልኡክ የደረሰበትን ‹‹የውሳኔ ሐሳብና ተያያዥ ጉዳዮች በሪፖርት መልክ አቅርቦ›› /የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ እንደገለጹት/ መወያየትና ከጥር 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም በሎሳንጀለስ ካሊፎርኒያ ለሚካሄደው አራተኛውና ወሳኙ ዙር ጉባኤ አበው ቀጣይ የመነጋገሪያ አቋሞችን ማስቀመጥ ዋነኛው ቁም ነገር ነው፡፡

የዜናው ምንጮች ባደረሱት ጥቆማ÷ በአንዳንድ የምልአተ ጉባኤው አባላት ሊነሡ ከሚችሉ የመነጋገሪያ አቋሞች መካከል÷ ‹‹ከአራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ገጽ ለገጽ ተገናኝቶ መወያየት›› እንደ ነጥብ ሊያዝ እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ‹‹በመንግሥት ጫና ከመንበረ ፕትርክና ተባረርኹ፣ ተበደልኹ ያሉ እርሳቸው ብቻ ናቸው፤ ድርድሩም መካሄድ የሚገባው ከእርሳቸው ጋራ ነው፤›› የሚሉ የቅ/ሲኖዶሱ አባላት÷ በውጭ የሚገኙ ሌሎች አባቶች በደል ደርሶብናል ባለማለታቸው ዋናው ድርድር ከአራተኛው ፓትርያሪክ ጋራ ብቻ መኾን እንደሚገባው ይከራከራሉ፡፡

በሹመት ቀደምትነት ያላቸውና በአምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የተሾሙት አባቶች በተደራዳሪነት የማይሳተፉበት የዕርቀና ሰላም ውይይት በዳላስ ቴክሳስ ለሦስተኛ ጊዜ ለማካሄድ ዝግጅት በሚደረግበት ሰሞን÷ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ወደ አሜሪካ ተጉዘው ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ እንዲገናኙ ቀርቦ የነበረው ሐሳብ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ናቸው በሚባሉ የቅ/ሲኖዶሱ አባላት ተቃውሞ የተነሣ ሳይሳካ መቅረቱ ታውቋል፡፡ ዐቃቤ መንበሩ ከአራተኛው ፓትርያሪክ ጋራ አድርገውታል የተባለው የስልክ ውይይት በይፋ መታወቁም ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹን ደስ እንዳላሰኛቸው ነው የተነገረው፡፡

የዕርቀ ሰላም ልኡኩ ወደ አሜሪካ ከተጓዘም በኋላ የልኡካኑን አባላት በአካል ወይም በስልክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ለማገናኘት በአቡነ መልከጼዴቅ ተደርጓል የተባለው ሙከራ ‹‹ከተልእኳችን ውጭ ነው›› በሚል ሳይሳካ መቅረቱ ተዘግቧል፡፡ በአንጻሩ አሁን ‹‹ጠባችን ይኹን ድርድራችን ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብቻ ነው›› የሚለው የመነጋገሪያ አቋም ሐሳብ መነሻ የጉዳዩን ተከታታዮች አጠያይቋል፡፡ ጥቂቶቹም የሐሳቡ መነሻ የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫና እነርሱ ‹‹ወገንተኝነት ይታይበታል›› የሚሉት አካሄዱ እንደኾነ በመግለጽ ‹‹በዚህ አደራዳሪ አንቀጥልም፤ ከቀጠልንም ድርድሩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብቻ ይኾናል›› መባሉን ይጠቅሳሉ፡፡

አነስተኛ ቁጥር ባላቸው ጳጳሳት የተደገፈውና በመንግሥትም ዘንድ ተይዟል የተባለው አቋም÷ ዕርቀ ሰላሙ ከፓትርያሪክ ምርጫው በተጓዳኝ እንዲካሄድ ሲኾን ይኸው አቋም የነገው አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ውሳኔ ኾኖ እንዲወጣ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ መኾኑ ታውቋል፡፡ ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ተፈጽሞ በአንድነት ወደ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ እንሂድ›› አልያም ‹‹አራተኛው ፓትርያሪክ በሕይወት እያሉ መንበሩ በእንደራሴ ይጠበቅ›› የሚሉትን ‹‹የዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› ደጋፊዎች አማራጮች መንግሥት እንደማይቀበለው የገለጹት ምንጮቹ÷ የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ሠምሮ ዕርቅ ከተፈጸመ በኋላ መንግሥት ዋስትና ወደ አገር ለሚገቡት አባቶች ደኅንነት ዋስትና እንዲሰጥ በውጭ ባሉት አባቶች ዘንድ በቀጣይ መደራደሪያነት ተይዟል የተባለውንም ሐሳብ እንደማይቀበለው ተናግረዋል፡፡ በምንጮቹ ግንዛቤ ይህ የመነጋገሪያ ሐሳብ ‹‹አጀንዳውን ከጳጳሳቱ ወደ መንግሥት ለማዞርና ውዝግቡን ለመቀጠል የታቀደበት ነው፡፡››

የሰላምና አንድነት ጉባኤውን ተሰሚነት ባላቸው ሽምግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች አጠናክሮ የዕርቅና ሰላም ሂደቱን መቀጠል ሌላው የአስቸኳይ ስብሰባው አጀንዳ ነው፡፡ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት ደብዳቤ መላኩ የተገለጸ ሲኾን ስለ ደብዳቤው ዝርዝር ይዘት የተገለጸ ነገር ባይኖርም በምልአተ ጉባኤው ሊታዩ የሚገባቸውና ቀጣዩን የሰላም ጉባኤ የተመለከቱ ሐሳቦች ሊይዝ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

የሰላምና አንድነት ጉባኤው የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙን በመቃወም ላወጣው የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡካን ‹‹ይቅርታ እንዲጠይቅ›› መጠየቃቸውና ይቅርታ ካልጠየቀና አካሄዱን ካላስተካከለ በአደራዳሪነቱ አብረው እንደማይሠሩ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል፡፡ አሁን የሰላምና አንድነት ጉባኤው በላከው ደብዳቤ ስላወጣው መግለጫ ማብራሪያ የሰጠበት፣ ለዕርቅና ሰላሙ መልካም ፍጻሜ ሲባልም ቅ/ሲኖዶሱን ይቅርታ የጠየቀበት ሊኾን ይችላል ተብሏል፡፡ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ የታገዱትንና ከአገር በግዳጅ እንዲወጡ የተደረጉትን ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁንና ሌላውን ልኡክ የተመለከተ ጉዳይም ሊነሣበት እንደሚችል ተጠብቋል፡፡

ታኅሣሥ 8 ቀን መጽደቁ ተዘግቦ የነበረው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አከራካሪ አንቀጾችም በአስቸኳይ ስብሰባው ላይ ዳግመኛ ለውይይት እንደሚቀርብ ተገልጧል፡፡ ‹‹ሕጉ መጽደቅ ያለበት ምልአተ ጉባኤው በአግባቡ በተጠበቀበት ኹኔታ ነው›› በሚል ለዳግመኛ እይታ ተጋልጦ ሳለ÷ ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ከመስጠት አኳያ በአወዛጋቢ ውሳኔ እንደተሠየመ የተነገረለት የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ቅቡልነት አከራካሪ ሊኾን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው አባላት ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተገኝተው ሥራቸውን እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ የተሰጠበትን ደብዳቤ አግባብነት መፈተሽና የደብዳቤውን መሻር የሚያስከትል ውሳኔ እንዲወሰን መሟገት በጥብቅ የሚያስቡበት ብፁዓን አባቶች ቁጥር ጥቂት አለመኾኑም የስብሰባውን ሂደት ከባድ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡

Advertisements

One thought on “ሰበር ዜና – ዐቃቤ መንበሩ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸው ተሰማ

  1. Misganaw Zerihun January 15, 2013 at 9:38 am Reply

    In my view this is the most critical time ever happened in our church’s long term history. it is also a time for us to be tested in choosing the truth against the false decisions. we have been commemorating the works and endurance of our saints and martyrs how they gone through and overcome the challenges ever faced during their stay here on earth.it is also a time for paying every kind of devotion against every type of challenges and problems which may be hinder in the establishment of peace and unity of our own church. we should not allow any one’s foreign to our church’s interference. Government is often saying as though religion and government are separate and should not interfere one to each others affair. Therefore government is foreign to our church’s liturgical activities. it has no power to break the doctrine and dogma of our religion and the church’s canonical administration,too. Because being faithless and atheist is the right to be but to disturb and put ones hand against others who strictly follow according to the principle and the rules of faith is a crime that has to be condemned by every peace loving groups. We should better to die than to loose our religion and see a unified church separated here and there because this is the mission of our long term rival, the devil, but the devil never able to put our church into vain. So the spiritual fathers please try to abide by the rules and regulations of your heavenly bestowed religion and church’s problem to rightly and justly alleviated and never be challenged with a temporary assigned secular governments enforcement which may in one or another way look for the problem to remain as it before. and hence you should be wise enough like our fore fathers who had ever been putting the dogma and doctrine of their church under any kind of influence and pressure subject to violation of its dogma and doctrine. We all are responsible for the peace and unity of our church, we do not want to see an ever divided and hostile groups of synods here and there because we want to have a single shepherd to the congregates as it is the God’s commandment. Our Government often concerns for our earthly life to be stable and maximized with the shortage of the requirements to our daily life while we alive however God has taught us we are not monolithic creature in life that ends up with our body death here on on earth but have a dual life in which the life in heaven is eternal and priority have to given for such life because this secured only by a strict and diligent follow up of the instructions and order bestowed to us from God. So the cadres and supporters of the secular government please do not force us to break the law of God so as to maintain your temporary interest up on our religion and the churches administration.We have no option except to keep the dogma and doctrine our church, our fathers have got a prime responsibility and accountability. please I once again remind for all concerned groups
    to think the martyrs era to follow rather than fail to accomplish your duties and responsibilities rightly. May God give us the peace and unity we get thirst of it and give us the rightly chosen spiritual father free of any sort of debate and hostile among the fathers and the congregates.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: