የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራ እንዲጀምር የታዘዘበትን ደብዳቤ ሊሽረው ይችላል

 • ከውጭ አህጉረ ስብከት ብፁዓን አባቶች ከግማሽ ያላነሱ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል
 • የሰላምና አንድነት ጉባኤውን በተጨማሪ ሽማግሌዎች የማጠናከር አማራጭ ተይዟል

በመጪው ሳምንት ሰኞ፣ ጥር 6 ቀን 2003 ዓ.ም፣ ለዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ሪፖርትና ተጓዳኝ ሐሳቦች ቅድሚያ በመስጠት የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብስባ÷ በአወዛጋቢ ውሳኔ የተቋቋመው የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ሥራውን እንዲጀምር የታዘዘበትን የማሳሰቢያ ደብዳቤ ሊሽረው እንደሚችል ተጠቆመ፡፡

የማሳሰቢያ ደብዳቤው የተጻፈው በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊልጶስ ነው፤ በይዘቱም እስከ ጥር 30 ቀን ድረስ ከአምስት ያላነሱ ከሦስት ያልበለጡ የፓትርያሪክ ዕጩዎችን እንዲያቀርቡ የተሠየሙት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተገኝተው ሥራ እንዲጀምሩ የሚያሳስብ ነው፡፡

የመንበረ ፓትርያሪኩን አስፈጻሚ አካል ብቻ የመምራት ሓላፊነት ያለባቸው የጠ/ቤ/ክህነቱ ዋ/ሥ/አስኪያጅ÷ ይህን ዐይነቱን ማሳሰቢያ መስጠት ‹‹የማይመለከታቸውና ያለሥልጣናቸው የገቡበት ነው›› ብለዋል ኮሚቴው በቅ/ሲኖዶሱ የተሠየመበት የቀደመው ደብዳቤ ተፈርሞ የወጣው በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ፊርማ እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች፡፡Abune Filpos

                                                                   አቡነ ፊልጶስ

ይኸው የማሳሰቢያ ደብዳቤ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ወይም በቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ተፈርሞ አለመውጣቱ አስመራጭ ኮሚቴው ከመሠየሙም አስቀድሞ በመጠናከር ላይ የሚገኘውን ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ወገኖች ተቃውሞ/ትኩረት ለመቀነስ፣ በአመዛኙ ግን ዐቃቤ መንበሩና ብፁዕ ዋና ጸሐፊው በጉዳዩ ላይ ጥንቃቄ የተሞላበት አቋም ለመያዛቸው በአስረጅነት ተዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል የምልአተ ጉባኤው አስቸኳይ ስብሰባ ለጥር 6 ቀን በተጠራበት ኹኔታ አስመራጭ ኮሚቴው ጥር 8 ቀን ሥራውን እንዲጀምር መታዘዙ የቅ/ሲኖዶሱ የውሳኔ አሰጣጥና አፈጻጸም ‹‹የዕርቀ ሰላም ጉባኤው ከፓትርያሪክ ምርጫው ተለያይቶ መታየት አለበት፤ ዕርቀ ሰላሙ በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ የተጀመረ ነውና ይቀጥል፤ የፓትርያሪክ ምርጫውም ጎን ለጎን መካሄድ ይኖርበታል›› የሚል አቋም በያዙ በቁጥር ያነሱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተጽዕኖ ሥር ለመውደቁ ማሳያ ለመኾኑ የሚስማሙ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እሊህ አባቶች (አንዱ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ናቸው) ባገኙት መድረክ ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ቅድሚያ ሰጥተው ከማስተማር፣ ከመጸለይ ይልቅ ‹‹እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ አባት አናገኝም፤ ግን ጸዋሚ፣ ተሐራሚ፣ ሰጋጅ፣ ጸሎተኛ አባት እንዲሰጠን ጸልዩ›› ማለታቸውን አጠንክረው መያዛቸው ተዘግቧል፡፡

በአንጻሩ ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉና ቁጥራቸው በየጊዜው የሚጨምረው ብዙኀኑ ብፁዓን አባቶች ከወዲሁ የተለያዩ ማስፈራሪያዎች፣ ዛቻዎች፣ ጫናዎች የሚደርስባቸው መኾኑ ሲታይና ሲሰማ ተመሳሳይ ጥሪ በማስተጋባት ላይ የሚገኘው አገልጋይና ምእመን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ከጎናቸው እንዲቆም የሚያስፈልግበት ቀናት እንዲኾን አድርጎታል፡፡

የሰላምና አንድነት ጉባኤው እገዳና ወከባ ስለደረሰባቸው ልኡካኑ፣ የአገር ቤቱ የዕርቀ ሰላም ልኡካን ስለተቃወሙት መግለጫው ማብራሪያ እንደሚሰጥ ተጠብቆ የነበረ ቢኾንም የተጠበቀው አልኾነም፡፡ በአስቸኳዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ÷ የሰላምና አንድነት ጉባኤውን እንደ አዲስ በሚዋቀር አደራዳሪ አካል ለመተካት ቢታሰብም ከዚህ ይልቅ ጉባኤው ተደማጭነት ባላቸው የአገር ሽምግሌዎች ቡድን የተመረጡ አባላት ማጠናከር በውጭ ባሉትም ብፁዓን አባቶች ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኝ እንደማይቀር ተገምቷል፡፡ ከአገር ሽማግሌዎቹ መካከል እንደ ራስ መንገሻ ሥዩም፣ ፊታውራሪ ዘውዱ አስፋው እና አቶ አምኃ ወልዴ ያሉት ስማቸው ተጠቅሷል፡፡

በአስቸኳዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ለሚሳተፉት የቅ/ሲኖዶስ አባላት በጽ/ቤቱ የሚደረገው ጥሪ ተጠናቆ ተሳታፊዎቹ ወደ አዲስ አበባ – መንበረ ፓትርያሪኩ በመግባት ላይ ሲኾኑ በውጭ አህጉረ ስብከት ከሚገኙ ዐሥር ያህል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ከግማሽ በላይ ለስብሰባው እንደሚደርሱ ተገልጧል፡፡ በስብሰባው ታኅሣሥ 8 ቀን የጸደቀው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አንዳንድ አንቀጾች የሚነሣባቸው ጥያቄዎች/ተቃውሞዎች፣ ሕገ ደንቡ የጸደቀበት የስብሰባ ሥነ ሥርዐት እንዲሁም ከሕገ ደንቡ መጽደቅ በፊት ታኅሣሥ 6 ቀን በአወዛጋቢ ውሳኔ የተሠየመው የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ቀጣይነት በከፍተኛ ደረጃ ሊያከራክር እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

Advertisements

6 thoughts on “የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራ እንዲጀምር የታዘዘበትን ደብዳቤ ሊሽረው ይችላል

 1. Ben January 12, 2013 at 4:33 pm Reply

  ወዳጄ አንተው አይደለህ እንዴ አቡነ ናትናኤል የፈረሙበትን ደብዳቤ ያሳየኸን? ታዲያ ስራ ይጀምሩ ዘንድ አቡነ ፍሊጶስ ቢያሳስቡ ምንድን ነው ስህተቱ? ኸረ ረጋ እንበል።

 2. Ytb January 14, 2013 at 5:50 am Reply

  ante wusha …zim bel !! alebeleziya gudayun bedenbi tereda…!!

 3. Ytb January 14, 2013 at 5:51 am Reply

  Sorry its a reply for the first comment of ‘Ben’

  • Ben January 14, 2013 at 12:04 pm Reply

   @ ytb on
   አንተ አጋሰስ መጋዣ ( መቼም ሰደብከኝ አትልም ) የተፃፈውን እንኳን ልትረዳ፥ ምን ለማን እንደምትፅፍ አታውቅም። አየህ ረጋ ብትል አስተያየትህን እንኳ በአንድ ላይ ትፅፍ ነበር።

 4. Anonymous January 14, 2013 at 8:59 am Reply

  Ye min ergata , Kenona betekirstyan eytetase zim endet yibalal . Gibtsawiyane Abatoch ewinetegna yetewahido aribegnoch nachew . Ye minkusina tirgumu yegebachew . Be mengist tetshino fetsimew yemayirebeshu . Ke rasachew tikim yilke yebetekirstyanin andinet yemiyaskedimu . Engna kenesu linimar alchalinem . Egziabhere mechem betun ayiresam . Ye Weyane widketum eyetakarebe melkam mengist yemimetabet tinbetum eyetefetsem new ena ye betekirstyan tinsaye eruk aydelem . Harawoch yemitebekibachewin eyetewetu endehone hulu egnam yebekulachinen eniweta !!!

  • Ben January 14, 2013 at 1:10 pm Reply

   ወዳጄ መቼም የኛ ነገር ችግሩ ሰፊ ነው።
   በመጀመሪያ እኔ የፃፍኩት ሃራ ዘተዋህዶ አቡነ ፍሊጶስን ለከሰሰበት ደብዳቤ ነው።

   ሃራ ያወጣው ደብዳቤ ካላየኸው፦

   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
   ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
   ለብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ
   የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ
   ለብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
   የሰሜን ወሎና ዋግ ሕምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
   ለብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ
   የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
   ለመልአከ ምሕረት ዓምደ ብርሃን ገብረ ጻድቅ
   የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሓላፊ
   ለሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ
   የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ
   ለፀባቴ ኀይለ መስቀል ውቤ
   የደብረ ሊባኖስ ገዳም አስተዳዳሪ
   ለንቡረ እድ ዕዝራ ኀይሉ
   የርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ
   ለቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድ
   ለአቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ
   ለአቶ ባያብል ሙላቴ
   ለዲያቆን ኄኖክ ዐሥራት
   አዲስ አበባ፤

   ለ6ኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳት ለውድድር እንዲቀርቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ታኅሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ጉባኤ ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስኖአል፡፡

   ስለዚህ እናንተ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስመራጭ ኮሚቴ ኾናችሁ የተመረጣችኹ ስለኾነ ለ6ኛው ፓትርያሪክነት ምርጫ ዕጩ ኾነው የሚቀርቡ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ተወዳዳሪ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳትን፡-

   ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎች
   ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ከገዳማት አበምኔቶችና እመምኔቶች
   ከማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናን ከገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ከሰንበት ት/ቤት መንፈሳውያን ወጣቶች
   በሚሰጥ ጥቆማ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኙትን ለ6ኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ተወዳዳሪ የሚኾኑ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳት እስከ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንድታቀርቡ የተወሰነ መኾኑን እናስታውቃለን፡፡

   እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
   ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

   ግልባጭ፤

   ለዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ጽ/ቤት
   ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት

   ምንጭ ሃራ

   ደብዳቤውን የፃፉት አቡነ ናትናኤል ሲሆኑ በግልባጭ ደሞ አቡነ ፍሊጶስ ለሚመሩት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ተልኳል። ይህን ተንተርሰው አቡነ ፍሊጶስ ሰው ሳይጨምሩ ሳይቀንሱ ስራ እንዲጀምሩ መጠየቃቸው ስህተት አለው እንዴ?

   ሌላው ስለ ቀኖና አንስተሃል። ግብፅንም። ወዳጄ ግብፆች ዛሬ የደረሱበትን አትይ። በስንት ነገር ውስጥ አልፈው ነው እዚህ የደረሱት።
   ቀኖናውን ደሞ ላለፋት 20 ዓመታት ሲጣስ ሳይሆን ሲደቀደቅ እያየነው ነው። በተለይም በውጪው።

   ሲጠቃለል እርቀ ሰላሙ ቀድሞ ወደ ምርጫ ቢገቡ የተሻለና ተመራጭ ነው። ምርጫውን ካስቀደሙም ሌላው አማራጭ ነው ባያስደስትም። መቼም እርቁ አሁን ሳይሆን ፓትሪያርኩ በህይወት ሆነው ነውና የተጀመረው አዲስ ቢሾም እንኳን እርቁን ያቋርጠዋል ማለት አሳማኝ አይሆንም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: