ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ ለጥር 6 አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ጠራ

 • በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለታሪካዊና ወሳኝ ጉባኤ ተጠርተዋል
 • አደራዳሪው አካል በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የዕርቀ ሰላም ሂደቱ እንደሚቀጥል ይጠበቃል
 • የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ የጸደቀበት እና አስመራጭ ኮሚቴው የተቋቋመበት መንገድ ዳግመኛ ይታያል
 • በአ/አ የቀሩት የሰላም ልኡክ መ/ር አንዷለም ዳግማዊ ከዐቃቤ መንበሩ ጋራ ተወያዩ

ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ፣ ታኅሣሥ 23 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት ባካሄደው ስብሰባ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲጠራ ወስኗል፡፡

አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ÷ የዕርቀ ሰላም ንግግሩ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት በአዲስ አነጋጋሪ አካል ስለሚቀጥልበት ኹኔታ፤ ታኅሣሥ 8 ቀን የጸደቀው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ እና አወዛጋቢው የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ የተቋቋመበትን መንገድ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን፣ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ከዕርቀ ሰላሙ ሂደት አኳያ ያለውን አግባብነት ዳግመኛ በማጤን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሰላምና አንድነት ወሳኝና ታሪካዊ የኾነ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

በዚሁ ወሳኝና ታሪካዊ ውሳኔ ይተላለፍበታል ተብሎ ለሚጠበቀው አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ÷ በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት ለሚገኙ፣ በቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ለሚችሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥሪው እንደሚተላለፍላቸው ተገልጧል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ የስብሰባ ሥነ ሥርዐት መሠረት÷ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ጉዳይ ከጠቅላላው አባላት ከአራት ሦስት እጅ መገኘት ይገባቸዋል፤ አስተዳደርን የሚመለከት ሲኾን ደግሞ ከጠቅላላው አባላት ከሦስት ሁለት እጅ መገኘት ያስፈልጋቸዋል፡፡

አሁን ምልአተ ጉባኤው ለአስቸኳይ ስብሰባ የተቀጠረባቸው አጀንዳዎች (የዕርቀ ሰላሙ አጀንዳዎችና አቋሞች፣ የፓትርያሪክ ሹመትና የምርጫ ሕገ ደንቡ) በአንዳንዶች ዘንድ አስተዳደራዊ ይዘቱ አመዝኖ ቢነገርም በተለይም በሹመት ቀደምትነት ባላቸው በርካታ አረጋውያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ኾኖ በመወሰዱ ቅ/ሲኖዶሱ በተሟላ ቁጥር ተገኝቶ በስምምነት እንዲወስንባቸው ማስፈለጉ ተዘግቧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ ኾነው በቋሚነት የሚሰበሰቡ 51 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት (ከእኒህ ሦስቱ በሕመምና በዕርግና) ያሉት ሲኾን በታኅሣሡ ስብሰባ ‹‹ስንጠራችኹ ትመጣላችኹ›› በሚል እንዳይገኙ የተደረጉት በውጭ አህጉረ ስብከት የሚገኙ ከዐሥር ያላነሱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለጥር 6 ቀን የአስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ መጠራታቸው የግድ እንደኾነ ተነግሯል፡፡

ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱና እርሱን ለማጠናከር የተመረጡት ተጨማሪ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በዛሬው ስብሰባ የዕርቀ ሰላም ልኡኩ ሪፖርቱን ማቅረቡ ተዘግቧል፡፡ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ታኅሣሥ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ያወጣውና የዕርቀ ሰላም ልኡኩ ተቃውሞታል የተባለው መግለጫም ውይይት ተካሂዶበታል ተብሏል፡፡ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ‹‹ቅ/ሲኖዶሱን በመግለጫ ዘልፏል›› በሚል ማክረሪያ ነጥብ የዕርቀ ሰላም ጉባኤው ተስፋ እንደተሟጠጠ የሚገልጡ አቋሞች በመንበረ ፕትርክና አላሚዎች የተራመዱ ቢኾንም የዕርቀ ሰላም ሂደቱ አሁንም ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት በሌላ አነጋጋሪ አካል መቀጠል እንጂ መስተጓጎል የለበትም የሚለው የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ጠንካራ መከራከሪያ ተቀባይነት አግኝቶ አስቸኳዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ መጠራቱ ተገልጧል፡፡

በተያያዘ ዜና የሰላምና አንድነት ጉባኤው ልኡክ ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከአገር በግዳጅ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ በሀገር ቤት የቀሩት ሌላው ልኡክ መ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ÷ ዛሬ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዲገቡ ተፈቅዶላቸው ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ጋራ መወያየታቸው ተሰምቷል፡፡ የሰላምና አንድነት ጉባኤው አንዳንድ አባላት በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ላይ በተወሰደው ርምጃ ምክንያት ‹‹እኛ ሂደቱን ከዚህ አድርሰናል፤ ጉባኤው በማንኛውም አደራዳሪ ቢተካም ከሥር ኾነን እንላላካለን›› ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በአገር ውስጥና በውጭ በስደት በሚገኙት ብፁዓን አባቶች ዘንድ ዕውቅናና ተቀባይነት አግኝቶ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ሲሠራ የቆየ አካል መኾኑ ይታወሳል፡፡

 

የጉባኤውን ውሎዎች በተጨማሪ ዜናዎች ይከታተሉ

Advertisements

9 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ ለጥር 6 አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ጠራ

 1. zelalem January 1, 2013 at 1:25 pm Reply

  this is nice news i heard from hara tewahedo! i found the effort to satisfy our need is similar with your name ! keep it up reporting unbiased information’s ! God bless you!

 2. Anonymous January 1, 2013 at 2:17 pm Reply

  It is good news let US all pray for for better to our church

 3. mebrat January 1, 2013 at 8:06 pm Reply

  Hara Tewahedo, Thank you for your Unbiased report. Keep on your good way of reporting. Don’t be disappointed by the discouraging news about you. በርቱ ለትክክለኛ ዜናችሁ:: በዚሁ ቀጥሉ:: የኛው የሆኑ ድረ-ገጾች ለምሳሌ አሐቲ ተዋህዶ ስለናንተ በሚጽፉት አትረበሹ:: አሐቲ ተዋህዶ ”ዲ/ን አባይነህ ካሴ በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆነው አልተመረጡም::” በሚል ርእስ ባወጡት ጽሁፍ በጣም አዝኜባቸዋለሁ::

  ጽሁፋቸው በጣም እጅግ በጣም ብዙ እንከኖች አሉት ለምሳሌ:
  1. ማህበረ ቅዱሳን ምንም አይነት ጥፋት ቢያጠፋ መነካት እንደሌለበትና የሚሰራው ስራ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ እንኳን ቢሆን መሸፈን እንዳለብን ይናገራል:: ይህ ጤንነት አይደለም:: ማህበረ ቅዱሳን የሚኖረው ቤተክርስቲያን ስትኖር ነው:: እኔም ማህበረ ቅዱሳን መወቀስ አለበት እያልኩ አይደለሁም:: ማህበሩ ለቤተክርስቲያናችን በተለይ በግቢ ጉባኤያት ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች አካባቢ በጣም የሚያስመሰግነው ስራ እየሰራ ነው:: ማህበሩ የራሳችን ነው ልንንከባከበው ይገባል ነገር ግን በውስጡ ያሉ ሰዎች ስህተት ሲሰሩ ዝም ብሎ ማየትና ስህተታቸውን መደበቅ ጤነኛነት አይደለም::

  2. የተከበሩትን ዲ/ን አባይነህ ካሴን ፍጹም በማይመጥናቸው መልኩ ያጥላላቸዋል:: ዲ/ን አባይነህ ካሴ ምንም አይነት የሰሩት ጥፋት የለም:: ከVOA ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ሰምቸዋለሁ እንዲያውም ቀድቼ አስቀምጨዋለሁ:: በጣም የሚያስከብራቸውና የሚያስመሰግናቸው ቃለ ምልልስ ነው ያደረጉት:: ለቤተክርስቲያን አንደነትና ሰላም የሚቆረቆር ሰው በዲ/ን አባይነህ ቃለ ምልልስ ሊኮራ ይገባው ነበር::

  3. የማህብረ ቅዱሳንን ስህተት አውጥቶ ለአንባቢያን የሚያቀርብን ሁሉ ከተሐድሶ ይመድቡታል:: ለምሳሌ እናንተን ስለ ዲ/ን አባይነህ ካሴ ያለውን እውነታ ስላወጣችሁ ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ከነ ‘አባ ሰላማ’ መድቧችኋል:: ይህ ፍጹም ስህተት ነው::

  እናንተ ግን በነሱ ማዘን የለባችሁም:: ከቻላችሁ ተቀራርባችሁ አብራችሁ በመነጋገር ስሩ:: በርግጥ እናንተን እስካሁን የኛ ትሁኑ የተሐድሶዎች መሆናችሁን አልለየንም:: እንደኔ ግን ማንም ይጻፍ ማን ሚዛናዊ ዘገባ እስካቀረበ ድረስ ተሐድሶ ነው መናፍቅ ነው ወዘተ ማለት አስፈላጊ አይመስለኝም:: እስካሁን ያቀረባችሁት ተሐድሶ የሚያስብል ነገር የላችሁም:: ተሐድሶነት የሚያሳይ ሳይሆን ማንም ሰው ሊሳሳት የሚችለውን በሩጫ ሪፖርት ስላረጋችሁ የተሳሳታችሁት በጣም ጥቃቅን ነገሮች አሉ:: እነኛ ስህተቶች ግን በጣም ኢምንት ናቸው:: እንደስህተት ሊቆጠሩም አይገባቸውም:: ጥቃቅን ስህተቶቻችሁ ደግሞ የሪፖርት እንጂ የሐይማኖት ስህተት አይደለም::

  ለአሐቲ ተዋህዶ ስህተታቸውን እንዲያርሙ ትላንትና ጽፌላቸው ነበር እስካሁን ግን ፖስት አላረጉትም:: ከቻላችሁ ቀርባችሁ ተነጋገሩ:: አንተ እንዲህ ነህ እንተ እንዲያ ነህ መባባል አይጠቅምም:: መተራረም ነው ለክርስቲያን የሚገባው::

 4. anonymous January 2, 2013 at 1:04 pm Reply

  እኔም ወዳጄ መብራት በሰጡት ሀሳብ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ ማቅ እጅግ በጣም ለትውልድ እና ለታሪክ የሚተርፍ ሥራ የሠራ ታላቅ ማኅበር ነው ይሁን እንጂ የሰዎች ስብስብ የፈጠረው እንደመሆኑ እንከን የሌለበት ለሚመስላችሁ አትሳሳቱ መተቸቱ መጠላቱን አያሳይም እንዲስተካከል ትችቱን ይቀበል የክርስቲየያን ማኅበር ነውና ለመሆኑ እንደ ዲያቆን ያረጋል እና ዲያቆን ዓባይነህ ተሐድሶን የተዋጋ ማን ይሆን ፊት ለፊት በዓደባባይ ተሐድሶን በጥብዐት ሲያወግዙ የምናውቃቸውን መምህራችንን ማንም እንዲነካብን አንሻም ነገር ግን ከማቅ ጋር የተፈጠረ ችግር ያለ አይመስለኝም ጥቂት አመራሮች ማቅን ይወክላሉ ብሎ መናገር በጣም ያስቸግራልና ልዩነቱ የሚፈታበት መንገድ ቢኖር ደስ ይለኛል አባላቱ ዝምታን ከመረጡ ግን ነገ የሚመጣው ያስፈራል እነ ቢያብል ይፈቱታል ማለት ግን ጅልነት ነው

 5. anonymous January 2, 2013 at 1:33 pm Reply

  ይቺን ተጨማሪ የጡመራ መድረክ በማግኘታችን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ሚዛናዊ ለመሆን ሁልጊዜ ሞክሩ እንጂ አትደነቃቀፉ

 6. Alemu k February 26, 2013 at 9:07 pm Reply

  Please use PDF version for ur informative posts, because it is easy to access for mobile users and non amharic font users

  Thank u

 7. Demeke Yeneayhu July 16, 2013 at 10:42 pm Reply

  የተዋሕዶ ሠራዊትየተዋሕዶ ሠራዊቶች፥
  እናት ቤተ፡ክርስቲያን እንዲህ ኣይነት ውርደት ስታስተናግድ የት ነበራቹህ፥ አሁንስ የት ናቹህ?
  http://memhirgirma.wordpress.com/

 8. Anonymous August 30, 2013 at 2:29 pm Reply

  hara tewahido dedeboch nachihu sewnekemenkef kemamat leafta enkuwan yematezegeyu yekrstena tsebaye yelelachehu weshetamoch menafekan nachihu awekenebachehuwal betam yemiyasazenew gin betekristiyanen agaletachehu lebaedan setachehuwat e/r bederachehun ayasatachehum abatochen yekebereta aterar enkuwan mekebel yakatachehu alemaweyan nachehu enaneten bilo tebakiwoch terefe menafekan nachehu neseha gibu .

 9. hani August 30, 2013 at 7:02 pm Reply

  yehenen yemitsefuten begeletse enawekachewalen betekersitianen leshetu yetezegaju nachew.gene dese yemelew medhenealem hulunum yasayenal.enezehu sewoch nachew abatoch laye begenezeb sew eyelaku eyewenejelu yalut.egna memenan zeme belen eyayen new gene bebeatekristeyan lay aned neger bemeta zeme belen yeminaye endayemeslachew.abatoch laye enedefelegachew afachehun kefetu yehe lenesu mesekelachew new.gene bemedeya kelede yelem.eyanedanedesh mejemeria beteshen astedader.enetewawekalen.wera tetachew sira seru.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: