የሰላም እና አንድነት ጉባኤው አባላት ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ ታገዱ

 • እገዳው ጉባኤው ካወጣው መግለጫ ጋራ የተያያዘ ሊኾን እንደሚችል ተገምቷል
 • እገዳውን የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ የጠ/ቤ/ክ ዋና ሥራ አስኪያጁ አያውቁትም ተብሏል

በሀገር ውስጥ በሚኖሩት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና በውጭ አገር በስደት በሚገኙት አባቶች መካከል የዕርቀ ሰላም ንግግር እንዲካሄድ በማድረግ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሁለት አባላት ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እንዳይገቡ መታገዳቸው ተሰማ፡፡

ከኅዳር 26 – 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ በተካሄደው ሦስተኛ ዙር ጉባኤ አበው÷ በሰላምና አንድነት ጉባኤው የሚሠየሙ ልኡካን ወደ ሁለቱም ምልአተ ጉባኤ በቅርቡ ተልከው ለዕርቀ ሰላሙ ስኬት የማግባባት ሥራ እንዲሠሩ በተደረሰበት ስምምነት መሠረት የተላኩት ሁለቱ ልኡካን በትላንትናው ዕለት አዲስ አበባ ደርሰው ዛሬ ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለመግባት ሲሞክሩ ነበር በጥበቃ አገልግሎቱ መታገዳቸው የተሰማው፡፡

ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ

የእገዳ መመሪያው ለጥበቃ አገልግሎቱ ያስተላለፈው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት እንደኾነ ቢገለጽም፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ስለ ትእዛዙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ፣ መመሪያው ለጥበቃ አገልግሎቱ የተላለፈው በቃል እንጂ በደብዳቤ አለመኾኑም ነው የተመለከተው፡፡

ስለ ጉዳዩ የተጠየቁ አስተያየት ሰጪዎች÷ እገዳው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ታኅሣሥ 12 ቀን ካወጣውና ‹‹በዘለፋ የተሞላ፣ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣ ሚዛናዊነትን ያልተከተለ፣ አሳሳች ትርጉም የሰጠ፣ የአደራዳሪ ወይም የአስታራቂ መርሕን የጣሰ፣ የተጀመረውን የሰላም ጉዞ የሚያደናቅፍ›› በማለት የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡካን ከተቃወሙት መግለጫ ጋራ የተያያዘ ሳይኾን እንደማይቀር ገልጸዋል፡፡ የእገዳ መመሪያው ‹‹ከመንግሥት የተላለፈ ነው›› የሚሉ ሌሎች ምንጮች በበኩላቸው÷ ከዕርቀ ሰላሙ ይልቅ ለፓትርያሪክ ምርጫው ቅድሚያ በመስጠት አስመራጭ ኮሚቴው እንዲቋቋም ከፍተኛ ድጋፍ የሰጡ ሊቃነ ጳጳሳትን ይወቅሳሉ፡፡

እንደተባለው የእገዳ ትእዛዙ በመንግሥት አካል የተላለፈ ከኾነ መንግሥት÷ ‹‹አቡነ መርቆሬዎስ ይመለሱ ወይም አይመለሱ የማለት ሕገ መንግሥታዊ መሠረት እንደሌለው፣ ለሰላምና ጸጥታ ሲባል የተጀመረውን ዕርቀ ሰላም ሲደግፍ መቆየቱን፣ ሲኖዶሱ በስደት ላይ ያሉት ፓትርያሪክ እንዲመጡ ቢያደርግ የሚቃወምበት ሕገ መንግሥታዊ መሠረት እንደሌለውና በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንደማይገባ›› በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ በኩል የተገለጸውን ሐሰት እንደሚያደርገው ተገልጧል፡፡ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላት ላይ ብቻ ሳይኾን ‹‹ከምርጫው በፊት ዕርቀ ሰላም ይቅደም›› በሚል በግልጽ ወጥተው በመናገር ላይ በሚገኙ አገልጋዮች ላይ በአሁኑ ወቅት እየደረሰባቸው የሚገኘው የደኅንነት ወከባም የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ ስለ መንግሥት አቋም ከሰጡት ማብራሪያ ጋራ በቀጥታ እንደሚጋጭ ተዘግቧል፡፡

የቅ/ሲኖዶሱ የዕርቀ ሰላም ልኡካን የሰላምና አንድነት ጉባኤው ባወጣው መግለጫ ፈጽሞታል ያለውን ስሕተት በግልጽ አምኖ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ሓላፊነቱንም በአግባቡ እንዲወጣ፣ ይህ ካልኾነ ግን በጉባኤው አማካይነት ለመደራደር ፈቃደኛ እንደማይኾን ታኅሣሥ 16 ቀን 2005 ዓ.ም ባወጣው የተቃውሞ መግለጫ አስታውቋል፡፡ ይኸው የተቃውሞ መግለጫ ባስቀመጠው ግዴታ ሳቢያ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ይፋዊ ይቅርታ ይጠይቅ እንደኾን የታወቀ ነገር ባለመኖሩ ሁለቱ ልኡካን ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋራ ለመነጋገር የሚችሉበት አገባብ ግልጽ አልኾነም፡፡ ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙት የጉባኤው አባላት በያዙት መርሐ ግብር መሠረት ከመንግሥት አካላት ጋራ በመገናኘት ስለ ዕርቀ ሰላም ሂደቱ እና የጉባኤው አያያዝ ያስረዳሉ ተብሏል፡፡

የዕርቀ ሰላም ጉባኤው እየገጠሙት ባሉት ውስጣዊና ውጫዊ ዕንቅፋቶች ጋራ በተያያዘ፣ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለዕርቀ ሰላም ሂደቱ አግባብነት ባላቸው ሊቃውንትና ባለሞያዎች እንዲጠናከር እየቀረቡ ባሉት ትችቶች ሳቢያ አንዳንድ የጉባኤው አባላት ሐላፊነታቸውን ሂደቱን በማያስተጓጉል፣ ውጤቶቹን በሚያስጠብቅ አኳኋን ማስተላለፍ እንደሚሹ እየገለጹ መኾናቸው ተሰምቷል፡፡ ትላንት አዲስ አበባ የደረሱት ሁለቱ የሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላት ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ እና መ/ር አንዱዓለም ዳግማዊ ናቸው፡፡

Advertisements

2 thoughts on “የሰላም እና አንድነት ጉባኤው አባላት ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ ታገዱ

 1. Gebremikael December 27, 2012 at 10:09 pm Reply

  Please leave your post with PDF we have hard time
  To read every thing you post because I don’t have
  Amharic font on my phone ok?thank you.

 2. jfdkslj;fksa December 28, 2012 at 5:35 am Reply

  መጀመሪያ እኮ እናንተ እራሳችሁ ጸረ-ሰላም ናችሁ፤ ቅቤ አንገጓች ትሆናላችሁ፤ ጸረ-ሰላም፣ ጸረ-ኦርቶዶክስ ናችሁ!!!!!! ስለዚህ በእምነታችን ንግዳችንን አታጣጡፉ፤ ሌላ እንቨስትመንት ፈልጉ፣ ምንፍቅናችሁንም በአዳራሽ/ስቴዲዬም ብታደርጉት ይሻላችኋል፣ ፓለቲከኛም ከሆናችሁ ወይ ብረት አንግቡ አልያም የምርጫ ምልክታችሁን ለጥፉና ለምርጫ ቅረቡ፣ የኢሳት የውስጥ ኃይል ብቻ መሆን ብዙም ውጤታማ አያደርጋችሁም ብረት ብታነግቡ ይሻላችኅል፣ ፓስተር ኀይለጊዮርጊስ እንደዛ ይሻልህል፡፡ ጸረ-ኢትዮጵያ ነህ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: