ስብሓት ነጋ ቤተ ክርስቲያን ልትበታተን እንደምትችል አስጠንቀቁ!!

 • ‹‹አሁን መጠንቀቅ ያለብን ትበታተናለች፡፡ ብዙ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ሊፈጠሩ ይችላሉና በቅንነት ገምግመን እንዴት እንሂድ? እንቀይስ? ጊዜው አሁን ነው፡፡››
 • ‹‹በሂወት ያላችኹ ጳጳሳት ምሕረትን አውርዱላት፡፡››

/አቶ ስብሓት ነጋ ስለ አቡነ ጳውሎስ ሞት በተዘጋጀው የሐዘን መግለጫ መዝገብ ላይ ካሰፈሩት/

 ይህን መረጃ ያገኘነውና የምናቀርብላችኹ÷ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በኋላ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በዕርቀ ሰላም በማረጋገጥ እና ስድስተኛውን ፓትርያሪክ በመሾም መካከል የተከፋፈሉ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አቋም መልክ ለይቶ በወጣበት ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡ ከዚህም በመነሣት ተቋማዊ አነዋወራችን የሚያስጨንቃቸው ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያን በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደኾነች በማመን ከፓትርያሪክ ምርጫው በፊት ሰላሟና አንድነቷ እንዲቀድም የተባበረ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡

አቶ ስብሓት ነጋ

አቶ ስብሓት ነጋ

ቤተ ክርስቲያን አገራዊ ግዴታዋን ስትወጣ እንደነበረችና ለወደፊትም ታላቅ ሚና ሊኖራት እንደሚችል የጻፉት የኢትዮጵያ የሰላምና ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተርና የህወሓት መሥራቹ አቶ ስብሓት ነጋ÷ ‹‹አሁን የት ነች ብለን እናስብ፤ ደኅና ናት ወይ?›› በማለት ይጠይቃሉ – በአቡነ ጳውሎስ ኅልፈት የተሰማቸውን ሐዘን በጽሑፍ በገለጹበት መዝገብ፡፡

አቦይ ስብሓት ቤተ ክርስቲያን ‹‹የት ነች? ደኅና ነች?›› ብለው መጠየቃቸውን በራሱ በክፋት አናየውም፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ካለፉት ዘመናት ባልተለየ ኹኔታ ለኻያ አንድ ዓመታት ብሔራዊ ክብሯ ተዋርዶና ተቋማዊ ነጻነቷ ተደፍሮ እንድትዳከም የተደረገችው÷ ‹‹ኦርቶዶክሱን ማምከን ሙስሊሙን ማስከተት›› /Neutralizing the Church and Mobilizing Muslims/ በሚለው የእነ አቦይ የበረሓ ስትራቴጂ መኾኑን ስናስብ ግን ምናልባትም ጸጽቷቸው አልያም ከአቡነ ጳውሎስ የቀረውን የቤት ሥራ ‹ለማስቀጠል› ሊኾን ስለሚችል በጥንቃቄ እንመለከተዋለን፡፡ አሁን በቅርቡ እንኳ ‹‹ከአማርኛ ተናጋሪዎችና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት ›› ማለታቸው መች የሚረሳ ነው!!

አቦይ ስብሓት በሐዘን መግለጫቸው ‹‹ከአቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በኋላ አመቺ ኹኔታ የተፈጠረ ይመስለኛል›› ቢሉም በአቡነ ጳውሎስ ‹ሌጋሲ› (በእርሳቸው አገላለጽ ትተውልን በሄዱት ካህናትና ጳጳሳት) ግና ጥርጣሬ ያላቸው ይመስላሉ፡፡ የካህናቶችዋ መንፈሳዊ ብቃትና አንድነት ጉዳይ ለአቦይ ስብሓት ጥያቄ ነው፤ ከ‹‹ጠባብነትና ትምክህት›› ነጻ መኾናቸውም እንዲሁ፡፡ የትምክህተኝነቱ ባይገባንም የጠባብነቱ ለም አፈር ግን የማን ነገረ ሥራ እንደኾነ ከአቦይ ስብሓት ኅሊና የሚሰወር አይመስለንም፡፡

ከኅትመት ውጪ በኾነችው የፍትሕ ጋዜጣ ‹‹አይረቡም›› ብለው ከሞለጯቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምን እንደቀራቸው እንጃ እንጂ አቦይ ስለ ጳጳሳቱ አንድነትና ብቃትም የተጨነቁ ይመስላሉ – ‹‹አቡነ ጳውሎስ ትተውልን የሄዱት ቤተ ክርስቲያንና ጳጳሳቱ ደኅና ኹና፣ መሪዎቿም አንድነታቸውን ጠብቀው ብቃታቸው ተጠናክሮ፣ ባጭሩ ጠንካራ ቤተ ክርስቲያን ትተውልን ከኾነ ቅርሳቸው እየተዘከረ ይኖራል፡፡››

አቦይ ስብሓት ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ መጪ ኹኔታ ያሰፈሩልን ሐሳብ እንደ ‹ንግር›/ትንቢት/ ባንቆጥረውም የወቅቱን የሀገር ውስጥና የውጭ ኹኔታችንን በማስተዋል /በአዲስ አበባ ከሀገረ ስብከት መዋቅር ተለይቶ በቦርድ ለመመራት የሚያስቡ አጥቢያዎች አሉ/ እንዲሁም ከጉዳዩ ጋራ በተያያዘ አቦይ የነበራቸውን የቀደመ ቅርበት በማስታወስ እየነዘረ፣ እየጠዘጠዘ እንደማያስተኛ ሕመም ኾኖብናል፡፡ አቦይ እንዲህ ይላሉ÷

ሰው ያልፋል፤ ተፈጥሮ ነው፡፡ አሁን መጠንቀቅ ያለብን ትበታተናለች፡፡ ብዙ

 የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ሊፈጠሩ ይችላሉና በቅንነት

 ገምግመን እንዴት እንሂድ? እንቀይስ? ጊዜው አሁን ነው፡፡ አመቺ ኹኔታ

  የተፈጠረ ይመስለኛል፡፡

ስብሓት ነጋ ስለ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በጽሑፍ ያሰፈሩት የሐዘን መግለጫ

ስብሓት ነጋ ስለ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በጽሑፍ ያሰፈሩት የሐዘን መግለጫ

አቡነ ጳውሎስ ‹‹ሰውና ወንድም በመኾናቸው›› ዕረፍታቸው በጣም እንደሚያሳዝናቸው በሐዘን መግለጫቸው መግቢያ ላይ የገለጹት አቦይ ስብሓት የሐዘን መግለጫቸውን ሲያጠናቅቁ ‹‹ነፍሳቸውን ይማርልን›› በማለት ተሰናብተዋል፡፡ ለሊቃነ ጳጳሳቱ ግን መልእክት አላቸው÷ ‹‹ዋና ነገር ምሕረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ፡፡ በሂወት ያላችኹ ጳጳሳት ምሕረትን አውርዱላት፡፡››

አቶ ስብሓት ነጋ ስለ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በጽሑፍ ያሰፈሩት የሐዘን መግለጫ

አቡነ ጳውሎስ ሰውና ወንድም በመኾናቸው ዕረፍታቸው በጣም ያሳዝነናል፤ ያሳዝነኛል፡፡ ትተውልን የሄዱት ቤተ ክርስቲያንና ጳጳሳቱ ደኅና ኹና፣ መሪዎቿም አንድነታቸውን ጠብቀው፣ ብቃታቸው ተጠናክሮ፣ ባጭሩ ጠንካራ ቤተ ክርስቲያን ትተውልን ከኾነ ደሞ ቅርሳቸው እየተዘከረ ይኖራል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሃገራዊ ግዴታዋን ስትወጣ የነበረች፣ ለወደፊቱ ታላቅ ሚና ሊኖራት የሚችል ስለኾነች አሁን የት አለች ብለን እናስብ !! ደኅና ናት ወይ? የካህናቶችዋ መንፈሳዊ ብቃትና አንድነትስ? ከጣባብነትና ከትምክህት ነጻ ናቸው? ሰው ያልፋል፤ ተፈጠሮ ነው፡፡ አሁን መጠንቀቅ ያለብን ትበታተናለች፡፡ ብዙ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ሊፈጠሩ ይችላሉና በቅንነት ገምግመን እንዴት እንሂድ? እንቀይስ? ጊዜው አሁን ነው፡፡ አመቺ ኹኔታ የተፈጠረ ይመስለኛል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡ ዋና ነገር ምሕረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ፡፡ በሂወት ያላችኹ ጳጳሳት ምሕረት አውርዱላት፡፡

ምንጭ፡- ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ የ፹ ቀን መታሰቢያ ልዩ እትም መጽሔት

Ab Pawlos 80 Ken

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ጳውሎስ የ፹ ቀን መታሰቢያ ልዩ እትም መጽሔት

Advertisements

9 thoughts on “ስብሓት ነጋ ቤተ ክርስቲያን ልትበታተን እንደምትችል አስጠንቀቁ!!

 1. Anonymous December 26, 2012 at 6:35 am Reply

  I think YOU( hara zetewahdo) are from TEHADSO or may be you are the messenger of EFDR.

 2. comment December 26, 2012 at 6:55 am Reply

  እናንተን ይከፋፍላችሁ!!! ጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸረ-ኦርቶዶክስ ናችሁ!!!!! የተሀድሶ የውስጥ ክንፍ መሆናችሁን፤ ነቅተናል፤ ስማችሁን ለምን ለወጣችሁት ‹‹አባ ሰላማ›› መባሉ ስለተነቃባችሁ ነው፡፡

 3. Getnet Mesfin Aregu December 26, 2012 at 7:05 am Reply

  ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በቅዳሴው ስለክርስቶስ “የምትወዱት አልቅሱለት” ይላል በግፍ መከራ መቀበሉን ሲያስብ፤ እኔ ደግሞ ስለእናንተ “የምትወዱዋቸው አልቅሱላቸው” እላለሁ ሰይጣን በድንቁርና በክህደት ግፍ በእናታችሁ ላይ እንድትነሱ መውደቋንም በየዕለቱ እንድትመኙ አድርጓችኋል፡፡ ያደረባችሁ እንጅ እናንተማ በአርአያው ንጹሕ አድርጎ የፈጠራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ማስተዋሉን ያድላችሁ!!!

 4. TachewN December 26, 2012 at 7:39 am Reply

  Although this is not different from shedding crocodile tears from this perplexing and controversial individual, the information that he has given us is extremely important. thank you…now, the job remaining is to accelerate the work started and make it mass based…by the way he may also have ideas about the solutions as he himself was the master of the problem itself…it may therefore be important to arrange an interview with him…

 5. Gebremikael December 26, 2012 at 10:21 pm Reply

  Pls leave your post with PDF please.

 6. Bekeme December 27, 2012 at 6:50 am Reply

  It is always a mystery (i think it is also the corner stone of our underdevelopment) why we talk about the background of the person rather than the issue. If a person comes with a little bit different idea we give him/her a name. Hence, to protect their names people don’t bring out their ideas and with out diffident ideas change/development can not be achieved. This is common in the political, social and religious spheres. We only should be critical on the issue at hand including how much the information is reliable. We don’t need to defame people on whatever ideas they are bringing. Let’s ideas fight rather than we fight each other by drawing a lines. Hara provided enough and tangible evidence on the report and we all know that our Church is at critical stage in terms of its unity.

  On Hara blog i have seen a very special character of the media, which we mostly don’t see it on Ethiopian media, Independence and inclination to the truth without supporting any group interest. These days that kind of media are very important. We Ethiopian brought up to think if you are not my supporter then you are my enemy thinking and that will be a major challenge for your continuous Independence and standing with the truth. You have to be strong enough to withstand this challenge.

  For the readers, please let us think and act in civilized way and challenge the idea/report with evidence rather than simple name calling.

 7. Kinetewahedo December 27, 2012 at 10:28 pm Reply

  አምላከ ዋልድባ ኢታርምም በክልኤ፡ወኢትጸመም ይእዜ፡
  አምጣነ ጊዜነ ኮነ እንተ አራዊት ጊዜ።

  ትርጉም:-

  የዋልድባ አምላክ ሆይ በሁለት ነገር ዝም አትበል አሁንም ቸል አትበል፡
  ጊዜአችን የአውሬዎች ጊዜ ሆኗልና።
  Read more on

  http://taborbetekine.blogspot.de/

 8. Kinetewahedo December 27, 2012 at 10:29 pm Reply

  ሐውልተ ኢያሱ ብሉይ ወሐውልተ ጴጥሮስ አብ ሐዲስ በኀቤነ፡
  እስመ ኢፍሉጣን ብሉይ ወሐዲስ መጻሕፍቲነ፡
  ወእግዚአብሔር ሕያው ጸሐፈ ቦሙ ትዕዛዘ ቃሉ እሙነ፡

  ትርጉም:-

  በእኛ ዘንድ የኢያሱ ሐውልት ብሉይ የጴጥሮስ ሐውልት ሐዲስ ነው፡
  ብሉይና ሐዲስ መጽሐፎቻችን አይለያዩምና፡
  ሕያው እግዚአብሔርም የታመነ የቃሉን ትዕዛዝ ጽፎባቸዋልና።
  http://taborbetekine.blogspot.de/

 9. Anonymous December 28, 2012 at 3:59 am Reply

  ato bekeme netsa media (independence media ) belo eko neger yalem were new esum kesera egna gen mechem mech yemnognew lebetekrstan new ena haran yankolebabsu meslot ayesastu lemens yalem ewketacheenen kemenfeswewew endabalekalen?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: