ሰበር ዜና – የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴን ከሓላፊነት አነሣ

 • ውሳኔው ጥቂት አመራሮች ለጳጳሳቱና ለመንግሥት የገቡትን ቃል ያረጋገጡበት ነው
  • የዕርቀ ሰላም ደጋፊ አባቶችና አገልጋዮች በከፍተኛ የደኅንነት ወከባ ውስጥ ናቸው
  • ወከባው ወደ አገር የሚመለሱቱን የዕርቀ ሰላም ልኡካንንም ይመለከታል ተብሏል
  • ‹‹ደኅንነቱ›› በመባል የሚታወቁት አቡነ ቀሌምንጦስ ዋነኛ ጠቋሚና አስጠቂ ኾነዋል
  • ‹‹ደኅንነቱ›› ጳጳስ የማኅበሩ አመራሮች ሚናቸውን እንዲለዩ አስጠንቅቀዋል
  • ጦማሪዎች ለእውነትና ለቤተ ክርስቲያን እንጂ ለርካሽ ወገንተኝነት ሊሠሩ አይገባቸውም !!

‹‹ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ›› የሚለውን የማኅበረ ቅዱሳን መፈክር ‹‹ቅድሚያ ለምርጫው›› ወደ ማለት የቀየሩት ጥቂት የማኅበሩ ሽንፍ እና ግዝ አመራሮች÷ ከዕርቀ ሰላሙ በፊት ፍቅርና አንድነት እንዲቀድም፣ የምእመናኑም ድምፅ እንዲደመጥ ጥሪ ያስተላለፈው የማኅበሩ አንጋፋ አመራርና አባል ዲ/ን ኢንጂነር ዓባይነህ ካሴ ከሓላፊነቱ ተነሥቶ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ወሰነ፡፡

የመንበረ ፓትርያሪኩ ምንጮች ለሐራ ዘተዋሕዶ እንደገለጹት÷ የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ ውሳኔውን ያሳለፈው ትላንት፣ ታኅሣሥ 14 ቀን 2005 ዓ.ም ምሽት በተጀመረና እስከ እኵለ ሌሊት በዘለቀ ስብሰባ ነው፡፡ የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ ታኅሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ በዳላስ ቴክሳስ በተካሄደው የዕርቀ ሰላም ጉባኤ ስለወጣው የጋራ መግለጫ እና ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሰላም ኹኔታ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት አስተያየት ነው፡፡ ለውሳኔው መሠረት ናቸው የተባሉ ክሦችም ‹‹በማኅበሩ ያለህን ሓላፊነት አላግባብ ተጠቅመኻል››፣ ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ ብለኻል››፣ ‹‹ቀኖና ተጥሷል ብለኻል››፣ ‹‹በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምሥራቅ፣ በምዕራብ ያለው ሕዝብ እንዲነሣሣ ቀስቅሰኻል›› የሚሉትና የመሳሰሉት እንደነበሩ ምንጮቹ አስረድተዋል፡፡

ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ

ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ

የዲ/ን ዓባይነህን የሬዲዮ ቃለ ምልልስ በአመዛኙ ከዐውዳቸው ውጭ የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት ክሣቸውን ያጠናቀሩት ጥቂት ሽንፍ እና ግዝ የማኅበሩ አመራሮች÷ ዲ/ን ዓባይነህ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡና ከማኅበሩ አባልነትም እንዲታገዱ ወይም እንዲወገዱ መሟገታቸው ተዘግቧል፡፡ ይህ የጥቂት ሽንፍና ግዝ አመራሮች ሙግት ማኅበሩ በስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ለመሳተፍና ቅድሚያ ሰጥቶ ለመሥራት የደረሰበትን ውሳኔ በሚቃወሙና በግብታዊ የአቋም ለውጡ ላይ ማብራሪያ በሚጠይቁ የአመራር አባላቱ ጠንካራ ተግዳሮት እንደገጠመው ተነግሯል፡፡

ውሳኔው ዲ/ን ዓባይነህ በሚያገለግሉበት በኤዲቶሪያል ቦርድ ጽ/ቤትም ብርቱ ተቃውሞ የገጠመው ሲኾን ውሳኔውን ሊደግፍ የሚችል ምንም ዐይነት መነሻ ከጽ/ቤቱ አለመቅረቡም ተገልጧል፡፡ ይህም የችግሩ ዋነኛ መነሻ በኾነውና ማኅበሩ ራሱን – የአብዛኛውን አመራሩንና መላው አባላቱን አቋም – በመፃረር ከዕርቀ ሰላሙ ይልቅ በምርጫው ላይ አተኩሮ ለመሥራት ያሳለፈው ውሳኔ÷ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ቅድሚያ ሰጥቶ ከመቆም አንጻር በማኅበሩ አመራር ውስጥ ወሳኝ ልዩነት ለመፍጠሩ ጉልሕ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡

በጥቂት ሽንፍና ግዝ የማኅበሩ አመራሮች በተገፋው በዚህ ውሳኔ ‹‹ርምጃ ወስደን ውጤቱን እናሳውቃችኋለን›› የሚል ቃል የተገባላቸው ለፓትርያሪክ ምርጫ የተደራጁ ሊቃነ ጳጳሳትና ሂደቱን በቅርበት የሚከታተለው የመንግሥት አካል ይደሰቱ ይኾናል፡፡ የውሳኔው መንፈስ ግን

ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ የማኅበሩ ትጉሃን አባላትና አጋር አካላት ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን በመሠዋት ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት የደከሙትን ድካም በማኅበሩ ህልውና ስም በሚነግዱ ጥቂት የማኅበሩ ሽንፍና ግዝ አመራሮች ዘንድ ሚዛን እንደማይሰጠው የተረጋገጠበት ነውና ከፍተኛ ቁጣ ሊቀሰቅስ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡ ዲ/ን ዓባይነህ የኤዲቶሪያል ቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ኾነው የተመረጡት ማኅበረ ቅዱሳን ፲ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ነው፡፡

ከትላንቱ የሥራ አመራር ጉባኤው ስብሰባ በፊት የማኅበሩ ሥራ አመራር ጽ/ቤት አባላት ባለፈው ሳምንት ዐርብ ምሽት ዲ/ን ዓባይነህን እንዳነጋገሯቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በንግግሩም ‹‹በማኅበሩ ያለህን ሓላፊነት አላግባብ ተጠቅመኻል›› ለሚለው ክሥ ዲ/ን ዓባይነህ÷ ከማኅበሩ አሠራር አንጻር ይቅርታ ሊጠይቁበት እንደሚችሉ ነገር ግን በማኅበሩ ያላቸውን ሓላፊነት እየጠቀሱ በተለያዩ ሚዲያዎች ጽሑፎችን የሚያበረክቱና ቃለ ምልልሶችን የሚሰጡ የማኅበሩ ሓላፊዎች በዝምታ የታለፉበትን ኹኔታ በመጥቀስ፣ በእርሳቸው ላይ ይህ ክሥ መጠናቀሩ ከቅንነት የመነጨ ስለመኾኑ አጠያያቂ እንደሚያደርገው አሳስበዋል፡፡

የተጣሰው ቀኖና እንዲታረም፣ ሰላምና አንድነት እንዲመጣ ዲ/ን ዓባይነህ እንደ አንድ አማራጭ ያቀረቡት ‹‹የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበር መመለስ›› ለቀጣዩ ፓትርያሪክ ምርጫ የተነሣሣውን የተደራጀ የጳጳሳት ቡድን ይኹን ጉዳዩን የሚከታተለውን የመንግሥት አካል አላስደሰተም ተብሏል፡፡ ይኸውም ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበር ይመለሱ›› በሚለውና ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ይፈጸም›› በሚለው መካከል ልዩነት የሚያደርገው የማኅበሩ አቋም÷ ‹‹ዕርቀ ሰላሙን እንጂ አራተኛው ፓትርያሪክ ወደ መንበር ይመለሱ የሚለውን አልደገፍም›› በማለት ለጳጳሳቱ እና ለመንግሥት አካል ሲሰጥ የቆየው ገለጻ የማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሓላፊ ከሰጡት አስተያየት ጋራ ተጋጭቷል በሚል ነው፡፡ የማኅበሩ አቋምና የኤዲቶሪያል ቦርዱ ምክትል ሓላፊ ዲ/ን ዓባይነህ አስተያየት መጋጨት በተደራጁት ጳጳሳትና በመንግሥት ዘንድ ማኅበሩ ‹‹እንዳመቺነቱ የሚያንጸባርቀው የተደበቀ እና የአደባባይ አቋም›› እንዳለው፣ ይህም በ‹‹አታላይነት፣ ከፋፋይነት›› እንዳስቆጠረው ተገልጧል፡፡

ዲ/ን ዓባይነህ በአስተያየታቸው÷ ‹‹ሁለታችንም አጥፍተናል፤ ቀኖናውን የጣስነው በጋራ ነው›› በሚል ከተሰራጩት መረጃዎችበመነሣት የቀኖና ጥሰትና ጥፋት በሁለቱም ወገኖች ዘንድ ካለ ‹‹ሁለቱም በጋራ ለሠበሩት ቀኖና የጋራ ሓላፊነት ወስደው በጋራ መጠገን እንደሚችሉ›› ተናግረዋል፡፡ ‹‹ቀኖና ተጥሷል ብለኻል›› በሚለው ጥቂት የማኅበሩ አመራሮች ሪፖርት መሠረት ግን÷ በአምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከተሾሙት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ከዕርቀ ሰላሙ በፊት ለቀጣይ ፓትርያሪክ ምርጫ የሚተጉት የተደራጁ ጳጳሳት፣ ‹‹ቀኖና ተጥሷል ከተባለ የእኛ ሢመት (ጵጵስና) ጥያቄ ውስጥ ይገባል፤ ዋጋ (ተቀባይነት) አይኖረውም›› በሚል የተነገራቸውን ክሥ አጉልተው አቅርበዋል፡፡ ከዚህም በመነሣት ‹‹ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ይሰጥ›› እያለ የሚጠይቀው ሕዝብ ድምፅ እንዲደመጥ፣ ሕዝቡም ከማንም ተጽዕኖ ይመጣል ብሎ ሳይሰጋ እንቅስቃሴውን በመግባባት፣ በመነጋገር እንዲያጠናክር በዲ/ን ዓባይነህ ጥሪ መተላለፉ ‹‹ለዐመፅ እንደማነሣሣት ተቆጥሯል፡፡››

በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች የተገፋው የሥራ አመራር ጉባኤው ውሳኔ መነሻ ከኾኑት ጳጳሳት መካከል የከምባታ ሐዲያና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ አንዱ ሲኾኑ የአስመራጭ ጉባኤው አባልም ናቸው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በኾኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ‹‹ደኅንነቱ›› በሚል የሚታወቁት አቡነ ቀሌምንጦስ ከኢሕአዴግ አራት ድርጅቶች አንዱ የኾነው ብአዴን አባል እንደኾኑና ከድርጅቱም ከፍተኛ ካድሬዎች መመሪያ እንደሚቀበሉ ይነገርባቸዋል፡፡

አቡነ ቀሌምንጦስ

አቡነ ቀሌምንጦስ

አቡነ ቀሌምንጦስ ከአቡነ ጎርጎሬዎስ እና አቡነ ሳዊሮስ ጋራ በመተባበር ‹‹ከምርጫው ይልቅ ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› በሚል የሚታወቁትን ብፁዓን አባቶችና አገልጋዮች በመጠቆምና በማስጠቆም በከፍተኛ የደኅንነት ጫና ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በፓትርያሪክ ምርጫውና በዕርቀ ሰላሙ መካከል አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ በተዘገበበት ወቅት የማኅበሩን ሁለት አመራሮች አስጠርተው ‹‹አንዴ ምርጫ አንዴ ዕርቅ አትበሉ፤ አቋማችኹን ለዩ›› በማለት እንዳሳሰቧቸውም ተነግሯል፡፡ ‹‹ስሜን በብሎግ ልታጠፉ ተዘጋጅታችኋል›› በማለትም እንዳስጠነቀቋቸው ተገልጧል፡፡ ‹‹አባቶቻችን በሚያሰጋ ኹኔታ ተከፋፍለዋል፤ ልናግዛቸው ይገባል፤ ምርጫውን ደግፈን ይበጃል የምንለውን ሐሳብ እንሰጣለን›› በሚል ገለጻ የታጀበው የማኅበሩ ግብታዊ የአቋም ለውጥ የተሰማውም ከዚህ የአቡነ ቀሌምንጦስና መሰሎቻቸው ዛቻና ማስፈራሪያ በኋላ ነው ይላሉ የማኅበሩ ምንጮች፡፡

አቡነ ቀሌምንጦስ በዚህ ሳያበቁ የዕርቀ ሰላም ልኡኩን በመወከል በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ መግለጫ የሰጡትን ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስንም ማጣጣላቸውና በብፁዕነታቸውም ‹‹ቆይ÷ እዚያ ኾነው እንደሚደነፉት መስሏቸዋል›› በሚል መዛታቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ በመነሣት ይህ ዘገባ በሚጠናቀርበት ሰዓት ከአሜሪካ ወደ አገር ቤት በመልስ ጉዞ ላይ ስለመኾናቸው የተነገረው የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ አዲስ አበባ እንደደረሱ ከመንግሥት አካላት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሊገጥማቸው እንደሚችል ተመልክቷል፡፡ አቡነ ቀሌምንጦስና የእርሳቸው መሰል አሰላለፍ የያዙ ጳጳሳት ያሻቸውን ቢሉም በአቋማቸው በጸኑት ብፁዓን አባቶች ዘንድ በከፍተኛ የመንፈስ ጽናት የተያዘው ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ የመስጠት ዝንባሌ አለመለወጡን ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

 

መርገፍ፡- የማለዳ ያህል በሚቆጠረው የጡመራ ልምዳችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ለእውነትና ለቤተ ክርስቲያን ሲሉ ብቻ መጦመር ምን ያህል ድካምና መሥዋዕትነት እንደሚጠይቅ በተጨባጭ እንረዳለን፡፡ ተቋሙ መንፈሳዊነት የራቀው፣ ያረጀና ያፈጀ አሠራር የተጠናወተው ከእኒህም የሚወለደው ሙስና እና ጎጠኝነት የተንሰራፋበት መኾኑ በመሠረታዊ ምክንያትነት ቢጠቀስም የዘርፈ ብዙ ሀብት ምንጭ የኾነው አገልጋዩና ምእመኑ ባይተዋርነት ግን ቀዳሚ ሓላፊነቱን ይወስዳል ብለን እናምናለን፡፡

ከባይተዋርነቱ በላይ የሚያመው ግን ለእውነት አለመተባበር በፈንታውም ‹‹እገሌ ደጋፊው ብዙ ነው፤›› በሚል ብቻ ስሕተቱ ከተራራ ገዝፎ የሚታየውን አካል ከትችት ነጻ ለማድረግ የሚፈጸመው የማሞላቀቅ አያያዝ ነው፡፡ ይኸው አያያዝ ከመንገደኛው ሰው የተለየ መረጃና ዕውቀት ይዞ የማሳወቅን፣ የማጋለጥን፣ የማሳመንና የማስተማርን ሥራ መሥራት በሚገባቸው ሚዲያዎች ላይ ሲታይ ደግሞ ሕመሙ ይጸናል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የዘመኑን ዕውቀትና ክህሎት የያዘው ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን በዕውቀቱ፣ በገንዘቡና በሞያው ለማገልገል ያስችለው ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀለት መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ዕውቅና የተሰጠው ማኅበር መኾኑን ሐራውያን እናውቃለን፡፡ በዚህም መሠረት ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ አገልግሎት መጠናከርና መስፋፋት ዓምድና መሠረት የኾኑ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ልማታዊ የአገልግሎት ፍሬዎች ማበርከቱንና በማበርከት ላይ መኾኑንም ምናልባትም ለማኅበሩ እንቆረቆራለን ከሚሉት በተሻለ ሐራውያን በቅርበት እንገነዘባለን፡፡

ግና÷ ማኅበሩ ከተሰጠው መተዳደሪያ ደንብ፣ ከሚሸፍነው የአገልግሎት አድማስ እና ከሚያቅፋቸው አባላቱ ሞያዊ ስብጥርና አቅም አኳያ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅራዊ ችግር በመሠረታዊነት ለመለወጥ በቂ ሥራ እንዳልሠራ – ከሌላ ከማንም ሳይኾን ከገዛ አመራሮቹና አባላቱ – የሚነሣው ምሬት ደግሞ ይሰማናል፤ በቂ ሥራ አለመሥራት ብቻ ሳይኾን ቀደም ሲል በተሠሩ ሥራዎች ማኅበሩ ያዘመራቸውን የአገልግሎት ፍሬዎች (ውጤቶች) ወደኋላ የሚመለሱ የማኅበሩ የውስጥ ድክመቶችም እንዳሉ ስንገነዘብ ደግሞ ዕረፍት የሚሰጠን አይኾንም – በተለይም በከፍተኛ አመራሩ የሚፈጸሙ ስሕተቶች፡፡

በ2003 ዓ.ም መጋቢት ወር በተላለፈው የቅዱስ ሲኖዶስ የውሳኔ ቃለ ጉባኤ መሠረት በመካሄድ ላይ የሚገኘው የዕርቀ ሰላም ጉባኤ÷ ‹‹የቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት የሚጠበቅበት፣ የሰላም ወዳዱ ሕዝበ ክርስቲያን የአስተዳደር ችግር በሰላማዊ መንገድ የሚፈታበት ነው፤›› ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሠራ በኅትመቶቹ ርእሰ አንቀጾች፣ መልእክቶችና ትምህርቶች ሲያስታውቅ፣ ሲያስገነዝብ ቀጥተኛ የተግባር እንቅስቃሴ ሲያደርግም መቆየቱን እናውቃለን፡፡

ባለፈው ሳምንት ዐርብ ዕለት ከቀትር በኋላ እንዳረጋገጥነው ግን ሽንፍ እና ግዝ (conformist and subservient) ብለን በምንጠራቸው ጥቂት የማኅበሩ አመራር አባላት ግፊትና ውሳኔ ማኅበሩ ከቀደመ አቋሙና ውሳኔው ጋራ በሚጋጭ አኳኋን ቅድሚያ ለምርጫው ሰጥቶ እንደሚሠራ መግለጹ ታውቋል፡፡ ሰላምን በምትሰጠው የሰላም ባለቤት በኾነችው ቤተ ክርስቲያን ‹‹ምርጫውን ሰላማዊ ለማድረግ›› በሚል ከተመደቡ የመንግሥት ሹም ጋራም የምትሠራ የማኅበሩ አመራርም መመደቧ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡

ይህም ብቻ ሳይኾን በዕርቀ ሰላሙ ዙሪያ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት የሞከሩ ዘጋቢዎችም ምን ያህል እንዲሸማቀቁ እንደተደረጉ ሰምተናል፤ ‹‹ታሪካዊ ስሕተት መሥራት የለብንም፤ ቤተ ክርስቲያን መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት፤ እንድረስላት፤ አመራሩ ይህን በአግባቡ አልተረዳውም፤ ለሕዝቡ የኾነ ነገር ማለት አለብን፤›› ያሉ የአመራር አባላት የሚያዳምጣቸው አለመኖሩ ያሳዝናል፡፡ ከዕርቀ ሰላሙ ፍጻሜ በፊት ሂደቱን የሚያሰናክል ምንም ነገር እንዳይደረግ ገዳማውያን አባቶች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን እንዲያሳስቡና ገዳማውያኑም ስለዚህ ጉዳይ እንዲያዝኑና እንዲጸልዩ ማሳሰቢያ በተሰጠበት ማግሥት የአቋም ለውጡ መታየቱ የጤና ነው ወይ አያሰኝምን?

ሐቁና የሐራውያን ዘገባ መንፈስ ይኸው ነው፡፡ በቀረበው መረጃ ርግጠኝነት ላይ ማንም ጥርጣሬ ሊገባው አያስፈልግም፡፡ የዘገባው ዓላማ ግብ ማኅበሩ ከጊዜው በፊት ታሪካዊ ስሕተት እንዳይፈጽም ማንቃት፣ ጉዳዩ ከአባሉም ባሻገር የሰፊው አገልጋይና ምእመንም በመኾኑ ለአደባባይ ፈተና (public scrutiny) እንዲጋለጥ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ በማኅበሩ ግብታዊ የአቋም ለውጥ የተደናገጠውና ግራ የተጋባው አባል የአመራሩን አቋም እንዲጠይቅና አመራሩ ከስሕተቱ በጊዜው እንዲታረም ከማበረታታት ይልቅ ለማኅበር በማሰብ ስም የሚካሄድብን ስም ማጥፋትና የእነማን ይኾኑ አሠሣ የሚፈይደው ነገር አይኖርም፡፡

ታሪካዊ አቋም በወሰድንበት ዐቢይ አጀንዳ የተፈጠረን ልዩነት አንድ የሚያደርግ አዲስ/የረባ መረጃ ሳይዙ የሰነበተ/የተቃረመ ዜና እየደጋገሙ ርካሽ ወገንተኝነትን ለማሳየት መሞከርም ትርፉ ትዝብት ነው፡፡ ‹‹እንደወረደ የመዘገቡ›› እና ‹‹የልምድ ማነሱ››፣ ‹‹የእናሳስባለን››፣ ‹‹ግለሰብን ማእከል ያደረገ›› ገለመኔ ‹‹የጨቡ አራድነት›› /geezonline እንዳለው/ እንኳ ይቆየን፤

Advertisements

45 thoughts on “ሰበር ዜና – የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴን ከሓላፊነት አነሣ

 1. Hello December 25, 2012 at 12:06 am Reply

  አይ ተሐድሶ መናፍቅ፣ ስምህን ለውጠሽ መጣሽ? ነቄ ብለናል። ጊዜያችሁን አታጥፉ፤ ሰሚ አታገኙም።

  • selam December 25, 2012 at 11:00 am Reply

   አይ ተሐድሶ መናፍቅ፣ ስምህን ለውጠሽ መጣሽ? ነቄ ብለናል። ጊዜያችሁን አታጥፉ፤ ሰሚ አታገኙም።

 2. anbesaw December 25, 2012 at 12:56 am Reply

  We know you very well…you are opportunistic and “Hilikegna”. You think that nothing will be done without you…..you are thirsty of fame……
  MK is doing its job with help of God while you guys are busy in accomplishing “someboday’s” agenda. We know who u are, please do not waste ur time…..”Hodachewu Amilakachewu Yehonachiwu…, Kalegna tikikl yelem bilachiwu yemitasibu…” nachiwu. I am worried abt your last fate….you will end up in a Menafikan gora unless you repent.

  Taabiwu

 3. Tikikil December 25, 2012 at 12:58 am Reply

  Mahibere Kidusan I am so proud of you!!!!!!!!!!

 4. tewahido December 25, 2012 at 2:13 am Reply

  Degmo bezih metachihu!!! we the members of Mk know what is going on.For this Case, Mk is well known.we have all the information. Critically I know you are among the bodies who are trying to disintegrate the church and the members. Thanks to God,we know you very earlier.That is the work of God.Let alone Mk, you are saying that the church should give priority for reconciliation. Mk has started since 1991 to shout about the Unity of the Church.It is not new for it.May be it is new for you,may be if it is real.MK’s standing is the same yesterday,Today and Tomorrow. Sira Ameraru is the the real representative of the members. Whatever differences are there,they will inform to the members. and with the Will of God,the differences were solved and will be solved ,if any..
  How much you like to see Mk as disintegrated,you said ከሓላፊነቱ ተነሥቶ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጠው ወሰነ on the other side you said ጥቂት ሽንፍ እና ግዝ የማኅበሩ አመራሮች÷ ዲ/ን ዓባይነህ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡና ከማኅበሩ አባልነትም እንዲታገዱ ወይም እንዲወገዱ መሟገታቸው ተዘግቧል.It is very controversial.If few of the sira amerar kedegefu how can be the decision made? you said the employees and members under Editorial Section did not support the decision.In mk if sira amerar decides ,noone can say i don’t agree or support.this is totally fallacy
  don’t try to cheat.God knows everything.
  May God give you peaceful mind..

 5. Yayal December 25, 2012 at 4:17 am Reply

  Nekanbish bilenal eko mindin new esu? Lemaegnawum yetelatin aselalef mawek aygodam bilen engobegnishalen enji teamaninetish enquan werdual zektualem! And wendime endih bilual ሲጅምሩ ቲፎዞ ለማፍራት፣ የአንባቢያንን ቁጥር ለመጨመር ኦሮቶድክሳዊ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን፣ መረጃዎችን ማስነበብ ይጀመሩና ቀስ በቀስ ደግሞ ሸተት ሸተት ይላሉ። ታዲያ በዚህ ጊዜ «ተሐድሦ ሆይ ስምሽ ለውጠሽ መጣሽ?» ማለት ይገባል። Silezih nekanibish enibelat wegen!

 6. selam December 25, 2012 at 6:06 am Reply

  menale yelele were bataweu? yelekes gezeachuen bekenetu atatefu. MK yemeserawen yemeyawek maheber new….

 7. Tsadiqe December 25, 2012 at 6:11 am Reply

  Menew enantes tehetena yegodelewe negeger batetsefu.Tegesten,Fekeren astemerun.Lehulum gize alew.

 8. Getnet Mesfin December 25, 2012 at 6:20 am Reply

  “ሐቁና የሐራውያን ዘገባ መንፈስ ይኸው ነው፡፡ በቀረበው መረጃ ርግጠኝነት ላይ ማንም ጥርጣሬ ሊገባው አያስፈልግም፡፡” ማስረጃዉንም እንፈልጋለን፤ ያለበለዚያ ግን መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ ይሁዳን እንደጠየቀው “ወዳጀ ሆይ ከወዴት መጣህ?” ስንል እንጠይቃለን!!!

 9. zelalem December 25, 2012 at 6:31 am Reply

  am an independent reader but your hasty generalization is not good.you wrote the article because of criticized by andadrigen. the reason is that he put his reason why mk is in the right track.to believe your article u didn’t put a reason more than rumors. please don’t be emotional.

 10. dawit yohannes December 25, 2012 at 9:52 am Reply

  ኣይ ወንድሜ ዌብ ሳይትን ለማስትዋወቅ ማቅን መክሰስ ኣያስፈልግም ነበር።ለወደፊቱ መስበክ ብቻ ኣያፀድቕም፤መንፈሳዊነት በጣም እንደሚጎልህ ያየሁበት ነው፤፤ ብዙ በኣገልግሎት መኖርህ ዋስትና ኣይሆንም፤፤ለራስ ዕወቅ፤፤

  • Anonymous January 1, 2013 at 2:19 pm Reply

   you are really devil protestant.you believe on devil church which fabricated on abroad.

 11. Gebre Ztewhado December 25, 2012 at 10:04 am Reply

  ግብራችሁ ዛሃራም(ቀባዣሪ) ሆነብን ስለዚህ ስማችሁን ቀይሩት

 12. Sayezana December 25, 2012 at 12:00 pm Reply

  በጣም የሚገር ነው። የዘገባው ባለቤቶች መረጃ አገኘን ብለው ዘግበዋል። በቃ። አይ ይህ ትክክል አይደለም የሚል ሌላ መረጃ በማቅረብ የቀደመውን በቀላሉ ውድቅ ማድረግ ይችላል። ዘገባው ደግሞ በቀላሉ ሊጣራ የሚችል ነው። ውሎ አድሮም እውነቱ ይወጣል። ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ፤ ለምንድ ነው ይህ ሁሉ ማሸማቀቅ? መድረኩም አዲስ ነው። በርቱ ተበራቱ ከማለት ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ስለምን? ለቤተ ክርስትያን በመቆርቆር? አይመስልም። ፈርዶብን ከመታገስና ዕድል ከመስጠት ይልቅ ሁሉን እንደባላጋራ አናት አናቱን እያሉ ማኮሰስና ማሳጣት አንድም እርምጃ ወደፊት አያስኬድም። አላስኬደምም። አሁን ማኅበሩ ተነካ ተብሎ ይህን ያህል?! ዘይገርም ነው። ከዚህ የበለጠ እናታችን ቤተ ክርስትያን በከፋ ሁኔታ ላይ አይደል ያለችው?! ታዲያ አብሮ ተባብሮና እጅ ለእጅ ተያይዞ እንደመስራት፤ ነቃንብህ ነቃንብሽ መባባሉ እስከመቼ? መጠላለፉስ መቼ ነው የሚያበቃው? ያለፈው የመከራ ዘመን አይበቃም? በሉ ደግሞ አንተ ተሀድሶ ነቃንብህ በሉ። ሁሌ አቅጣጫ ማስቀየር። እውነትን ፊት ለፊት ማየት መልመድ አለብን። እስኪ እግዚአብሔር ሀገራችንን ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን። እንደ እኛማ አያያዝ ቢሆን እሰከ አሁን ሁሉን ድራሹን አጥፍተነው ነበር።
  ቸር ይግጠመን

 13. Wubalem December 25, 2012 at 12:49 pm Reply

  አንበሳው እና ያያል ከላይ የሰጣችሁት የሞተ እና የበሰበሰ የጅል ሀሳብ መሆኑን አሁን ልታውቁ ይገባል ይልቁንስ የማያነቅፈው አድርጋችሁ የምትቆጥሩትን ማኅበር ለመታደግ ከአሁን የተሻለ ጊዜ እንደሌለ እወቁ እንደ መንደር ማስታወቂያ መለጠፉን ተውት እና ለቤተክርስቲያን ሰላም ሥሩ እርሱን የማትፈልጉ ከሆነ ደግሞ በቃችሁ አርጅታችሁዋል ሕዝቡ አንቅሮ እየተፋችሁ ነው ይልቁንስ ጤነኛ ዓላማ ይዞ የተነሣውን ማኅበር አትበጥብጡት ራሳችሁን ከቅስፈት አድኑ

 14. Wubalem December 25, 2012 at 1:11 pm Reply

  I am truly annoyed with what is going on. You guys seem very close to informations. I have very much concern and love to MK. But the shaking that we are currently looking is unlike the behavior of this association. There seems too much influence from the Gov. And there are few conformist and subservient messengers who rely on the earthly Gov not by the Heavenly God.

  On the recent issue of Hamar we have read that MK will strive for the peace and reconciliation of the church prior than any other agenda including ‘selection” not election of the 6th Patriarch. What a paradigm shift encountered, else than piracy. MK belongs to me too. I would do anything for the salivation of the Church and MK. The conformists cannot dictate the way they like. የማኅበሬን መልካም ዝና እና ስም ሲያጠፉ እና ሲያስጠፉ እነደምን ዝም እላለሁ

  • Hello December 25, 2012 at 6:33 pm Reply

   የማኅበሬን መልካም ዝና እና ስም ሲያጠፉ እና ሲያስጠፉ እነደምን ዝም እላለሁ

  • Anonymous January 5, 2013 at 10:07 pm Reply

   What a fool!!! U think mk is a gate to heaven.

 15. anbesaw December 25, 2012 at 4:32 pm Reply

  Wubalem
  You are one of the writer and “Kesari” person. Serving Church in a tough condition is not the same as talking on a website….. If you are a true christian, let us know your real name and stand. Sunday Schools and MK are clear on their stand and ready to secrify themselves. Let me tell you again, we know who u r….We know your plan…..If you cannot serve and leave what u preach and write, please keep your mouth shut and repent. Trust me The Church has been through several challenges…..but people like you bark here and there to shut the mouth of institutions under church because you lost all the fame at Sunday School, MK, Serk Gubaeyat…… Just sit and read and listen what u have been preaching. People who learned from you know how far you came off the line (Tihibit and Wude Kentu MEshat are killing you).

  We know you !!!!

 16. kibra December 25, 2012 at 5:02 pm Reply

  ahhh…you little mind who write this article, am so sorry. i did not expect you to this trush level. i know who you are…the so called group whose name is started by the A.A.T.M for four of you. Shame on you. I know how you tried to demolish the Mk in all directions since 1997. pls get confession from your holy father. ” Hara” satehonu ” Zaram” new. Amelkam kidusan lebe yiestachihu.

 17. TachewN December 25, 2012 at 7:18 pm Reply

  I am really sorry about what I am reading as comments on this article which gives only information and not more than that…what a shame on most of? Was the goal of MK originally when we strived a lot in the jungles and mountains enduring all sufferings from every direction ultimately having people like you, so called anbesaw, yayal, etc? which one is your primary agenda? saving the church or defending the mk leadership? Do you think MK’s leadership is inerrant like the Catholic’s pop? Come on guys! please try to make use of the information and act accordingly! If your issue is about the truthfulness of the info, you can ask the mk office or if your issue is supporting the decision of the mk leadership irrespective of its nature and trying to make those who oppose it keep silent, that is the biggest mistake you are committing and please listen to this wake up call and save your association if you will!!!

 18. Anonymous December 26, 2012 at 3:45 am Reply

  ere atrebum

 19. tarekegn December 26, 2012 at 4:28 am Reply

  ድስጥ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም ይባላል የእናንተም ስም መቀያየር ለውጥ አያመጣም ተሐድሶ ተሐድሶ ነው

 20. Anonymous December 26, 2012 at 9:44 am Reply

  ayyyyyyy menafikan ……..meche yihon lib yemitigezut (beka dabilosin beletachihut iko)

 21. libbelu December 26, 2012 at 9:46 am Reply

  ayyyyy……menafikan mech yihon lib yemitigezut( yegibir abatachihun beletachihut iko)

 22. Desu December 26, 2012 at 10:32 am Reply

  Disseminating false information Doesn’t drug back the true aim of MK about the EOC ,but it is crises of Tehadiso.

 23. Anonymous December 26, 2012 at 2:46 pm Reply

  አይ ተሐድሶ መናፍቅ፣ ስምህን ለውጠሽ መጣሽ? ነቄ ብለናል። ጊዜያችሁን አታጥፉ፤ ሰሚ አታገኙም።

 24. tewahido December 26, 2012 at 4:47 pm Reply

  For me depending on real information is given priority.there is no question on that.If Mk sira Amerar changed the position of Dn Abayneh Kassie,we will accept it.Because we believe that the decision may benefit the Church as well as Mk.If any one having a question on the decision,he/she can ask.It is open for all.I will ask you ,the Harawiyan.,what is the benefit you will gain disclosing this issue on your media?If you believe that the decision is wrong,go there and ask why and how it happens.If you are not from the church,leave alone Mk and the church.It is not your business..The other thing, the decision made or to be made by Mk Sira Amerar is Mk decision. we the members will accept it.This is Mk,one of the associations in EOTC.If sth wrong is there,the members will ask on Annual meeting or they can claim with their respective centers……In Mk there is clear and open room for discussion and deal.
  May God give us Love,Unity and Integration.
  Stand for the sake of the Church not for your personal interest..
  Believe in Synergy,not in individualism.

  • Hello December 26, 2012 at 11:01 pm Reply

   @tewahido December 26, 2012 at 4:47 pm :-

   Well said!

 25. Anonymous December 26, 2012 at 11:33 pm Reply

  I am very proud of my Orthodox believers, you know why they differentiate sheep from fox. Go get your full we know you!!!! Weather you change your name or come with new cover you are who you are anti Orthodox Tewahido. Let me confirm you this you can not achieve your goal, we are the true children of God. Losers!!!!!!

 26. Tomas December 27, 2012 at 6:26 am Reply

  Hulachihum Gedel GIbu!!!!

 27. Tomas December 27, 2012 at 6:28 am Reply

  MK m hone Tehadso Ekul Yebetekrstian Telatoch Nachhu!!!

  • Ben December 27, 2012 at 10:47 pm Reply

   ግን አንተ ተሃድሶን ትመርጣለህ አይደል ጴንጤው?

 28. Stand with the Church not with a group December 27, 2012 at 7:20 am Reply

  በጣም የሚገር ነው። የዘገባው ባለቤቶች መረጃ አገኘን ብለው ዘግበዋል። በቃ። አይ ይህ ትክክል አይደለም የሚል ሌላ መረጃ በማቅረብ የቀደመውን በቀላሉ ውድቅ ማድረግ ይችላል። ዘገባው ደግሞ በቀላሉ ሊጣራ የሚችል ነው። ውሎ አድሮም እውነቱ ይወጣል። ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ፤ ለምንድ ነው ይህ ሁሉ ማሸማቀቅ? መድረኩም አዲስ ነው። በርቱ ተበራቱ ከማለት ይህ ሁሉ ውርጅብኝ ስለምን? ለቤተ ክርስትያን በመቆርቆር? አይመስልም። ፈርዶብን ከመታገስና ዕድል ከመስጠት ይልቅ ሁሉን እንደባላጋራ አናት አናቱን እያሉ ማኮሰስና ማሳጣት አንድም እርምጃ ወደፊት አያስኬድም። አላስኬደምም። አሁን ማኅበሩ ተነካ ተብሎ ይህን ያህል?! ዘይገርም ነው። ከዚህ የበለጠ እናታችን ቤተ ክርስትያን በከፋ ሁኔታ ላይ አይደል ያለችው?! ታዲያ አብሮ ተባብሮና እጅ ለእጅ ተያይዞ እንደመስራት፤ ነቃንብህ ነቃንብሽ መባባሉ እስከመቼ? መጠላለፉስ መቼ ነው የሚያበቃው? ያለፈው የመከራ ዘመን አይበቃም? በሉ ደግሞ አንተ ተሀድሶ ነቃንብህ በሉ። ሁሌ አቅጣጫ ማስቀየር። እውነትን ፊት ለፊት ማየት መልመድ አለብን። እስኪ እግዚአብሔር ሀገራችንን ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን። እንደ እኛማ አያያዝ ቢሆን እሰከ አሁን ሁሉን ድራሹን አጥፍተነው ነበር።
  ቸር ይግጠመን

 29. Anonymous December 27, 2012 at 9:30 am Reply

  Min.yishalal.hulum.lewere.bicha.new.yemiserut

 30. Anonymous December 27, 2012 at 1:29 pm Reply

  ሀራ ትርጉሙ ምንድ ነው

 31. anonymous December 30, 2012 at 5:18 pm Reply

  አንዳንድ ከጨቅላነት በላይ ርቀው ያልሄዱ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት እጅግ ይገርማል መድረኩን ሰላገኙ ብቻ መዘላበድ ክርስቲያንነት አይደለም እስከኪ በዚህ የጡመራ መድረክ ከቀረቡት ጽፈፎች የትኛው ይሆን ከእውነት የራቀ መረጃውን ይዞ ማጣራት ሲገባ በደፈናው ማቅራራት ያስገመግማችሁዋል ማኅበረቅዱሳን የማይሳሳት እንደ ካቶሊክ ፓፓ ነው ለማለት የቃጣችሁ ንስሐ ግቡ ተሐድሶነት ትምህርተ ቤተክርስቲያንን ማዛባት እንጂ ማቅን መተቸት አይደለም ማቅ ሃይማኖታቸን ነው የምትሉ እንደሆነ ተሐድሶዎች እናንተው ናችሁ ይልቁንስ በውስጣችሁ የተሞላውን የክፋት ካባ አውልቃችሁ ወደ መንፈሳዊነት ተመለሱ ስትሞገቱ ማምለጫችሁ ሰውነ ማጥላላት አይሁን

 32. anonymous December 31, 2012 at 9:42 am Reply

  ሐራ ዘተዋሕዶ እውነትም የተዋሕዶ ወታደር እጅግ በርቱ ገና ከመጀመራችሁ አናት አናታችሁን ለማለት የሚፈልጉት የተነኩት እና የእነርሱ ጀሌዎች ናቸውና ዕውቅዎሙ ለገበርተ እኪት በእርግጥ አንድ ሰው ብዙ የሚሆንበትም ጊዜ አለ አንዱን መንካት እኛንም መንካት ነውና ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ አይደለም አሁን ትኩረታችን መሆን ያለበት በአንዲት ቤተክርስቲያን አንድነት ላይ መሆን አለበት የማቅን የውሰጥ ጉዳይ ከድል በኍላ እንመለስበታለን ቅድሚያ የሚሰጠው የቤተክርስቲያን ጉዳይ መሆን አለበት እርሱዋ ስትታመም ሁላነንም ያመናል አባቶች ታርቀው ሊያስታርቁን ይገባል

 33. Anonymous December 31, 2012 at 2:10 pm Reply

  man ale yalneka ? your strategy is known by every body menafkan

 34. Be Mature January 2, 2013 at 12:28 pm Reply

  አንዳንድ ከጨቅላነት በላይ ርቀው ያልሄዱ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት እጅግ ይገርማል መድረኩን ሰላገኙ ብቻ መዘላበድ ክርስቲያንነት አይደለም እስከኪ በዚህ የጡመራ መድረክ ከቀረቡት ጽፈፎች የትኛው ይሆን ከእውነት የራቀ መረጃውን ይዞ ማጣራት ሲገባ በደፈናው ማቅራራት ያስገመግማችሁዋል ማኅበረቅዱሳን የማይሳሳት እንደ ካቶሊክ ፓፓ ነው ለማለት የቃጣችሁ ንስሐ ግቡ ተሐድሶነት ትምህርተ ቤተክርስቲያንን ማዛባት እንጂ ማቅን መተቸት አይደለም ማቅ ሃይማኖታቸን ነው የምትሉ እንደሆነ ተሐድሶዎች እናንተው ናችሁ ይልቁንስ በውስጣችሁ የተሞላውን የክፋት ካባ አውልቃችሁ ወደ መንፈሳዊነት ተመለሱ ስትሞገቱ ማምለጫችሁ ሰውነ ማጥላላት አይሁን

 35. anonymous January 4, 2013 at 11:46 am Reply

  አንዳንድ ከጨቅላነት በላይ ርቀው ያልሄዱ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት እጅግ ይገርማል መድረኩን ሰላገኙ ብቻ መዘላበድ ክርስቲያንነት አይደለም እስከኪ በዚህ የጡመራ መድረክ ከቀረቡት ጽፈፎች የትኛው ይሆን ከእውነት የራቀ መረጃውን ይዞ ማጣራት ሲገባ በደፈናው ማቅራራት ያስገመግማችሁዋል ማኅበረቅዱሳን የማይሳሳት እንደ ካቶሊክ ፓፓ ነው ለማለት የቃጣችሁ ንስሐ ግቡ ተሐድሶነት ትምህርተ ቤተክርስቲያንን ማዛባት እንጂ ማቅን መተቸት አይደለም ማቅ ሃይማኖታቸን ነው የምትሉ እንደሆነ ተሐድሶዎች እናንተው ናችሁ ይልቁንስ በውስጣችሁ የተሞላውን የክፋት ካባ አውልቃችሁ ወደ መንፈሳዊነት ተመለሱ ስትሞገቱ ማምለጫችሁ ሰውነ ማጥላላት አይሁን

  እንዲህ ያልከው አንጀቴን አራስከው እንዲህ እንጂ አነጋገር….ማኅበረቅዱሳን የአመራሮች ብቻ ሳይሆን የእኛም ነው ማንም ደግሞ ከማንም የተሻለ አያስብለትም ሁላችንም እኩል ያገባናል

 36. anonymous January 4, 2013 at 12:07 pm Reply

  ዛሬስ የልቤን ልናገር
  የጡመራ መድረክ ገና ዛሬ ከማየቴ ያነበብሁት አሳዛኝ ነገር አጥንቴን ሰበረው።
  ማቅ ዛሬ ባለበት ወንበር ላይ የቆመው እነማን ባለሙት መሰላችሁ ። እኔ ማቅን ያወቅሁት በእነ ዲያቆን ዓባይነህ ካሤ አማካይነት ነው እና ማኅበሬን ምን ነካው ብየ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ። እውነት ለመናገር ከሆነ ለማቅ ሁለመናቸውን ሰጥተው ቀን እና ሌሊት ከደከሙለት ጥቂት ወንድሞች እና እኅቶች መካከል አንዱ እና በቆራጥ አቋሙ የሚታወቀውን አንጋፋውን ወንድማችንን እንዲህ ባሉ መውጫ እና መግቢያ በጠፋባቸው ጥቂት አመራሮች ፍጹም መለካዊ ወሣኔ የምናጣው ይመስላችሁ ይሆንን? ወቅቱ እናት ቤተክርስቲያን የተሰበረውን ወገብ ለመጠገን ደፋ ቀና የምትልበት ሆነ እንጂ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታለፍ አልነበረም። ቢሆንም ከእንግዲህ ዝም ላለማለት ተስማምቻለሁ።
  ከአንዴም ሁለት ጊዜ ከፍተኛ ደመወዝ የሚቀበልበትን ሥራ እየጣለ በዋና ጸሐፊነት ማቅን የመራ ማን ነው? እርሱ አይደለምን? እጅግ በጣም ተወዳጅ የሆኑ ሁለት መጻሕፍትን አዘጋጅቶ በነጻ ለማኅበሩ ያበረከተ አይደለምን? ከቶ ከእርሱ አጠገብ የሚደርስ ካሁኑ አመራር ውስጥ ማን ነው? ዝም ስንል አለማወቅ ተደርጎ ከሆነ ዋጋ ያስከፍላል። ያኔ እነ ዲን ኤፍሬም እሸቴ ዲን ዳንኤል ክብረት ግርማ ወልደ ሩፋኤል በዋናው ማዕከል ተፍ ተፍ ሲሉ አብሮ የነበረ በአመራሩ እየመራ በስበከቱ እየሰበከ በጽሑፉ እየጻፈ ሁለገብ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ወንድም እናንተ ከቶ እነማን ናችሁ እና ይህን አደረጋችሁ? አሁንም ውሣኔያችሁን እንድታስተካክሉ እመክራለሁ።

  • anonymous January 6, 2013 at 10:07 am Reply

   Thanks anonymous, jan 4, 2013 at 12:07 pm

 37. ሃይማኖት ርትእት April 14, 2013 at 9:08 am Reply

  አሃ ……ይሄ ማኅበር ወደ የት እየሄደ ነው………በመንፈስ ጀምሮ በሥጋ ለማጠናቀቅ………..የሚገርም ሩጫ……እኔ ራሴን እፈትሻለሁ………ስለ ማቅ የነበረኝ አመለካከት ክፉኛ አየተዛባ መሆኑ ይታየኛል……..

 38. hiwi April 1, 2014 at 2:14 pm Reply

  i dont think about this because every thing have there time but……………………….

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: