ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ራሱንና የአባላቱን አቋም በመፃረር በፓትርያሪክ ምርጫው ለመሳተፍ ወሰነ

 • ማኅበሩ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የሰጡትን አስተያየት አስተባብሏል
 • የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ ከመንግሥት ለተመደቡት ባለሥልጣን እገዛ ትሰጣለች
 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በማኅበሩ ጥቂት አመራሮች አቋም ግራ ተጋብተዋል
 • የማኅበሩ የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሰብሳቢ የአቋም ለውጡን በመቃወም ‹‹ውሳኔው አያስማማንም፤ የማስቀድመው ዕርቀ ሰላሙን ነው›› ብለዋል፡፡

‹‹ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ አንድነት የሚያመጣ ዕርቀ ሰላም መፈጸም ከሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር አንጻር፣ ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ከማሰብ አንጻር፣ መንጋውን ከማነጽና ሐዋርያዊ አገልግሎትን ከማቅናት አንጻር ለአባቶቻችን ግዴታ ይኾንባቸዋል፡፡ የሚፈለገው ዕርቀ ሰላም እውን እንዲሆንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ለእውነት፣ ለኅሊና ምስክርነት መገዛት አግባብ ይሆናል›› – ይህ መልእክት በሐመር መጽሔት፣ 20 ዓመት ቁጥር 8፣ ታኅሣሥ 2005 ዓ.ም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የወጣ፣ በድረ ገጹም የተደገመ የማኅበረ ቅዱሳን አቋም ነው፡፡ ይህ የማኅበረ ቅዱሳን መልእክት ‹‹ከምርጫው ይልቅ ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› ከሚለውና ማኅበሩ የበለጠ ከሚታወቅበት አቋሙ የመነጨ ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በመልእክቱ ዕርቅ÷ ‹‹በቤተ መቅደሱ ዕለት ዕለት መሥዋዕት ለሚያቀርቡ፣ ብዙዎችን በጸጋ እግዚአብሔር ባዕለጸጋ ለሚያደርጉ፣ ምስጢራትንም ሁሉ ለሚፈጽሙ፣ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ምልክት ለሆኑ ከሁለቱም ወገን ያሉ ብፁዐን አባቶች የሚያስተምሩት ብቻ ሳይሆን ዘወትር እንዲኖሩት የሚጠበቅ ክርስቲያናዊ ሕይወት›› መኾኑን መክሮ ነበር፡፡ መምከር ብቻ ሳይሆን÷ ቤተ ክርስቲያን ለኻያ ዓመታት ያሳለፈቻቸው አሳዘኝ ኹኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ መደረግ የሚገባው ሁሉ መደረግ ይኖርበታል ብሎ እንደሚያምን፣ ለዚህም እንደሚሠራ አቋሙን አስታውቆ ነበር፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን

ዛሬ፣ ታኅሣሥ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ከመንበረ ፓትርያሪኩ የተሰማው ዜና ግን ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ጉዳይ ማድረግ ከሚችለው አስተዋፅኦ አንጻር በውጭም በውስጥም፣ በቅርብም በሩቅም ተስፋ ለሚያደርጉት ወገኖች ሁሉ አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡ የማኅበሩ ጥቂት አመራሮች በወሰኑት ውሳኔ ማኅበሩ ‹‹ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ›› ሲለው የነበረው መፈክር ‹‹ቅድሚያ ለምርጫው›› ወደሚለው ተለውጧል!!

የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ አባል የኾነውና በነሐሴው የማኅበሩ 10 ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአወዛጋቢ አኳኋን የተመረጠው አቶ ባያብል ሙላቴ የአስመራጭ ኮሚቴው አባልነቱን የተቀበለ ሲኾን ዛሬ በተሰማው የማኅበሩ የአቋም ለውጥ ደግሞ የፓትርያሪክ ምርጫ ሂደቱን እንድትከታተል የማኅበሩ ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሪት ዳግማዊት ኀይሌ መመደቧ ተነግሯል፡፡ አቶ ባያብል ሙላቴ ከሲኖዶሱ በተመደቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳት አማካይነት ተቋቁሞ ያለበቂ ትችትና ውይይት በቀጥታ በጸደቀው 13 አባላት ባሉት አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ አንዱ አባል መኾ ናቸው ቢታወቅም ማኅበሩን ይወክላሉ በሚል የተመረጡበት መንገድ ግን ለብዙዎች ግልጽ አይደለም፡፡

የምክትል ሰብሳቢዋ ወ/ሪት ዳግማዊት የዛሬው ምደባ የአቶ ባያብል በአስመራጭ ኮሚቴ መካተት በማኅበሩ ላይ የፈጠረው አጣብቂኝ አስተዋፅኦ ሊያደርግ እንደሚችል የሚስማሙ ተቺዎች÷ ከመንግሥት ከፍተኛ አካላት ጋራ በዕርቀ ሰላሙና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ አመላለስ መካከል ስለመለየት እንዲሁም ስለ ተተኪ ፓትርያሪክ ምርጫ በተደጋጋሚ የተደረገው ውይይት ቀጥተኛ ጫና ሳያሳድር እንዳልቀረ ይናገራሉ፡፡ ዕርቀ ሰላሙ ዕንቅፋት የሚፈጥሩ ቀኖናዊ ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት፣ ተቀባይነት የሌላቸውን ቅደመ ኹኔታዎች በማስወገድ መፈጸም እንደሚገባው የሚገልጸው ማኅበሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበር ይመለሱ የሚለውን በመቃወም የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ መፈጸም ይኖርበታል ብሎ እንደሚያምን ተመልክቷል፡፡

ይኸው የማኅበሩ አቋም በተለይም የማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ የኾኑት ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን የሰላም ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡ ወዲህ ተግዳሮት እንደገጠመው ይነገራል፡፡ ዲ/ን ዓባይነህ በማኅበሩ ያላቸውን ሓላፊነት ጠቅሰው ሲያበቁ÷ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበር መመለስ የተጣሰው ቀኖና የሚቃናበት አንድ አማራጭ መኾኑን ማስቀመጣቸው፣ ቅድሚያ ለዕርቀ ሰላሙ በማለት አሰምቶ የሚጮኸው በአራቱም ማእዝናት የሚገኝ ምእመን ድምፅ ሊደመጥ እንደሚገባው ማሳሰባቸው፤ ከማንም ተጽዕኖ ይመጣል ብሎ ሳይፈራ በመግባባት፣ መወያየት፣ መንቀሳቀስና መነጋገር እንደሚያስፈልገው መጠቆማቸው፤ የሁለቱ ወገኖች የሰላም ልኡካን አብረው መጸለያቸውና መቀደሳቸው ‹‹ታላቅ ርምጃ›› መኾኑን መናገራቸው የማኅበሩን የቀደመ አቋም የለወጡትን ጥቂት አመራሮች አለማስደሰቱ ተገልጧል፡፡

ይህን በተመለከተ የማኅበሩ አራት አመራሮች በትላንትናው ዕለት ምሽት ዲ/ን ዓባይነህን ያነጋገሩ ሲኾን በዛሬው ዕለት ማምሻውን ደግሞ ዲ/ን ዓባይነህ ለቪ.ኦ.ኤ የሰጡት ቃለ ምልልስ ማኅበሩን እንደማይወክልና የግላቸው መኾኑን በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡ ዲ/ን ዓባይነህ በሬዲዮው ቃለ ምልልሳቸው የሰጡት አስተያየት የማኅበሩ አመራሮች ከመንግሥት ከፍተኛ አካላት ባደረጉት ውይይት ካስቀመጡት አቋምና በየጊዜው ለሊቃነ ጳጳሳቱ ከሚሰጡት ማብራሪያ ጋራ ‹‹የተጋጨ ነው፤ አባቶችን የሚከፋፍል ነው›› መባሉ የማኅበሩን ጥቂት አመራሮች ዛሬ የተሰማውን ዐይነት ግልጽ ነገር ግን በታሪክ አሳዛኝ የኾነ አካሄድ ውስጥ እንዲገቡ እንዳስገደዳቸው ተተችቷል፡፡ ወዲያውም ደግሞ ‹‹ርምጃ ወስደን እናሳውቃችኋለን›› ላሏቸው እንደ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ላሉት ሊቃነ ጳጳሳት የተግባር ምላሽ መኾኑ ተመልክቷል፡፡

ወ/ሪት ዳግማዊት በተመደበችበት ሓላፊነት ‹‹የፓትርያሪክ ምርጫውን ሰላማዊ ለማድረግ›› በሚል ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለተመደቡት አቶ ትእዛዙ ደሳለኝ መረጃዎች በመስጠትና ከአባቶች ጋራ በማቀራረብ እንደምትረዳ ተጠቁሟል፡፡ በተመሳሳይ አኳኋን የማኅበሩ ጽ/ቤት ሓላፊዎች የማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ክፍሎች÷ ማኅበሩ በምርጫው ላይ በማተኮር ለሚሠራው ሥራ እንዲዘጋጁ መመሪያና ማሳሰቢያ ሲሰጡ መዋላቸው ተዘግቧል፡፡

ይኹንና ውሳኔው የማኅበሩ ከፍተኛ አመራር ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ እንዲሰጠውና በትኩረት እንዲሠራበት በሙሉ ድምፅ ሊባል በሚችል መልኩ ያሳለፈውን መመሪያ የሚፃረር መኾኑን የገለጹ ወገኖች በአቋም ለውጡ ‹‹ራሱንና ለረጅም ጊዜ በጋራ ሲሠራበት የነበረውን የአባላቱን አቋም ተፃሯል›› ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የቀድሞው የማኅበሩ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም÷ ዕርቅ ሳይፈጸም ምንም ዐይነት እንቀስቃሴ እንዳይደረግ አበው መነኰሳቱ ለአባቶች እንዲመክሩና ኹኔታውንም በጸሎት እንዲያስቡ የተማፀኑት በትላንትናው ዕለት ምሽት አምስት ብፁዓን አባቶች በተገኙበት በተዘጋውና ለስድስት ቀናት የቆየው 70 የገዳማት አበምኔቶች ከ61 ገዳማት በተገኙበት ዐውደ ጉባኤ እንደነበር ተወስቷል፡፡

የማኅበሩ የሰሜን አሜሪካ ማእከል ሰብሳቢ የኾኑት ቀሲስ በላቸው ወርቁ ከዋናው ጽ/ቤት ሓላፊዎች ጋራ በስልክ አድርገውታል በተባለ ውይይት÷ ‹‹የተወሰነው ውሳኔ ፈጽሞ አያስማማንም፤ እኛ የምናስቀድመው ዕርቀ ሰላሙን ነው፤ ባለሁበት ቤተ ክርስቲያን በምሰጠው አገልግሎት ከዚህ የማኅበሩ አቋም እለያለኹ›› በሚል ተቃውሟቸውን መግለጻቸው ተገልጧል፡፡

ለሁለት ዐሥርት ዓመታት መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ልማታዊ አገልግሎት በመፈጸም የትውልድ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኘውን የማኅበረ ቅዱሳንን ክፉ መስማትም ማየትም አንሻም፡፡ ነገር ግን÷ ከቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም የሚቀድም ነገር ደግሞ የለም፡፡ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት እስከቆመ ድረስ ሁሉም ከጎኑ ይቆማል፤ አሰላለፉ፣ ስልቱ ይህን ሲቃረን ደግሞ ብቻውን ይቀራል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት እንደሚያረጋግጥ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ አገልጋዮችና ምእመናን ታምኖበት እየተደከመበት የሚገኘው ‹‹የዕርቀ ሰላም ይቅደም›› ጥያቄ ወደ አዲስ ምዕራፍ ሊሸጋገር ባለበት ዋዜማ ማኅበሩ የወሰደው አቋም ክፉኛ ያሳስበናል፡፡ ማኅበሩ በርግጥም ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ድምፁን ከፍ አድርጎ ለማሰማት ከተዘጋጀው ምእመን ጋራ ለመሰለፍ የተዘጋጁ ብዙኀን አመራሩና አባላቱ ማኅበር ከኾነ ጊዜው ከማለፉ በፊት የዛሬውን አቋሙን ያጢን፣ ይመርምር እንላለን ! ! !

Advertisements

20 thoughts on “ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ራሱንና የአባላቱን አቋም በመፃረር በፓትርያሪክ ምርጫው ለመሳተፍ ወሰነ

 1. Balemlay Muluken December 22, 2012 at 12:28 am Reply

  Sham on Mahibere Kidusan, የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ … ወስይ አይጥ ወልዳ ወልዳ …
  ሆነሳ ምንድን ነው ነገሩ?

  • mimi December 22, 2012 at 10:02 pm Reply

   ዜናውን የጻፍከው አንተ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ለማንኛውም ብዙ ይቀርሃል፤ ለመጻፍም ለመተረትም፡፡ ስለዚህ ከሚያውቁት ብትጠይቅ ወይም ብትማር ይሻላል፡፡

 2. Alebachew Degu December 22, 2012 at 6:28 am Reply

  አንርሳ ማህበረ ቅዱሳን እኮ በቤ/ክ ስር ያለ ነው፡፡በማንም ሃሳብ ሊመራ አይገባውም፡፡የአሁኑ አቋምም ትክክል ነው፡፡

 3. sami December 22, 2012 at 6:45 am Reply

  የርእሱ መዘበራረቅ ማህበረቅዱሳን ከማህበራት ሁሉ በኮሚቴው ለመካከት ብቸኛ ተመራጭ መሆኑ ያበሳጫቸው ሰዎች የጻፉት የሃሰት ቃል መሆኑ ግለጽ ነው፡፡ ሲጀምር ማህበረ ቅዱሳን ማለት አባላቱ ናቸው!!! “የእሱንና የአባላቱን አቁዋም በመጻረር….” ይህ ምን ማለት ነው??? የተመረጡት ሰዎችም አያደርጉትም እንጅ ቢያደርጉት እንኩዋ ይህ እርዕስ ሊሆን የሚገባው እንዲህ ነው…”.ማህበረ ቅዱሳን የወከላቸው የምረጫ ኮሚቴው ኣባላት የማህበራቸውንና የአባላቱን ዓቁዋም በመጻረር በፓትሪያሪኩ ምርጫ ለመሳተፍ ዎስኑ!” ነበር! አያችሁ ምን ያህል የትርጉም ልዩነት እንዳመጣ እዚህ ላይ የሚታየው የተመረጡት ግለሰቦችን አድረባይነትና ከሃዲነት የሚገልጽ ኁኖም ግን ማኅበሩ ሊሽረው የሚችልን ስህተት እንጅ ማህበሩን የሚያሶቅስ አይደለም! ደሞኮ ማህበሩ በቀበሌኛ ሳይሆን ድረጅታዊ በሆነ መዋቅር የሚመራ የብቁ ዜጎች መናሃሪያ እንጅ እንዲህ አይነት ተራ ስህተት የሚፈጸምበት የልጅ ቤት አይደለም! ሥለ ዲ/ኢንጅነር አባይነህ ካሴም የተሰጠው መግለጫም ይህንኑ ያመራር ብቃቱን የሚያሳይ ነው! ምክንቱም ማህበሩን ወከወሎ መናገር የሚችለው ጸሃፊው፤ ሊቀ መንበሩ፤ አለያም ህዝብ ግንኙነቱ ነው! እንዳጋጣሚ ሁኖ ግለሰቡ ከማህበራቸው ጋራ የማይቃረን ነገር ነው እንጅ ሌላ ቢናገሩስ ብለን ስናስብ የመግለጫውን ትክክልነት አናያለን!! ሙሉውን ቃለ ምልልስ በጆሮየ ሰምቻለሁ! እንደኔ ሃሳብ… እያሉ እንጅ እነደ ማህበሬ እያሉ አላውሩም! የመግለጫውም ጽሁፍ እንደሚከተው ነው “በማኅበረ ቅዱሳን ያላቸውን ሓላፊነት በመጥቀስ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ ታህሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም ምሽት ላይ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም ለቃለ ምልልስ ቀርበው በወቅታዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሓሳብ መስጠታቸው ይታወሳል። ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫም ሆነ ቃለ ምልልስ መስጠት የሚችሉት የማኅበሩ ሰብሳቢ ወይም ዋና ጸሐፊ ወይም የማኅበሩ ሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ናቸው፡፡ ስለዚህ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ በቃለ ምልልሳቸው የሰጡት አስተያየት የግል አስተያየታቸው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።

  ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
  የማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት
  ታህሣሥ 12 ቀን 2005 ዓ.ም
  አዲስ አበባ
  ስለዚህ እባካችሁ መንፈስን ሁሉ እንመርመር

 4. Yohannes December 22, 2012 at 8:22 am Reply

  We have to hear from MK !

 5. gg December 22, 2012 at 12:56 pm Reply

  የእሱንና የአባላቱን አቁዋም በመጻረር ?????? ይህቺ ነገር እነደት ንች? እረ ጽሁፉ ይመ ርመር ለኔ ትርጉም የለውም::

 6. kidist December 22, 2012 at 1:08 pm Reply

  የጠላት መኖር ብዙ ያሰራልና ማኅበረ ቅዱሳን የበለጠ እንዲሰራ እነደ እናንተ ዓይነቱ ስራ ፈት እና ተንኮለኛ መኖሩ ጥሩ ነዉና በርቱበት እላለሁ። አንባቢዉ ግን ያስተዉል::

 7. Abebe December 22, 2012 at 2:23 pm Reply

  ይህቺ ነገር ወዴት ወዴት ናት?? ዲ/ን አባይነህንም: ዳግዊትንም: ባያብልንም የማህበሩ አባላትም ይሁን አባላቱ በደንብብብብ እናውቃቸዋለን:: የሚያደርጉት ወይም የተናገሩት በሙሉ መንግስትን ለመጥቀም: ቤተክርስቲያንን ለመጉዳት አባቶችን ለማጥቃት እንደማያደርጉት አንገቴን እሰጣልሁ!!! ይህንንም ጽሑፍ ወይንም ብሎጉን በጥርጣሬ ማየት ጀምሬያለሁ በበኩሌ:: አቓም ያለው አይመስልም:: አባቶችን አንዴወዲህ አንዴ ወዲያ ግሩፕ እየከፈለ የሚያምታታ መረጃ ነው

 8. anbesaw December 22, 2012 at 5:36 pm Reply

  ይህ ዓይነት በማር የተለወሰ አቀራረብ ወሬ አደጋ እንዳለው አንባቢው ያስተውል። በአንድ ተቋም ውስጥ ለዝያውም ብዙ ሺ አባላት ባለበት ተቋም ውስጥ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ማድነቅ ግን የነበረብን የሐሳብ ልዩነትን በማስተናገድ በፍቅር እና በትህትና አብሮ ለአንድ ዓላማ መስራትን ነው፤ በመቀጠልም አካሄድን በወቅቱ ማረም። ስለዝህ ከእንዲህ ዓይነቱ በማር ከተለወሰ ክፉ ወሬ መጠበቅ አለብን።
  ሰላም
  ከአሜርካ

 9. Yayal December 22, 2012 at 6:35 pm Reply

  ነቄ ብለናል፡፡ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ግን አሸበራችሁ! ማኅበሩ እንዲህ አይነት አፍራሽ ዜናዎችን ሞኒተር በማድረግ በተቻለው መጠን እንደነገሩ ክብደትና በሚያደርሰው አፍራሽ ሚና እየመዘነ ቢያንስ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ቢሰጥ መልካም ነው እላለሁ!

 10. mimi December 22, 2012 at 9:48 pm Reply

  ከዚህ ሁሉ ባትጽፉ ቢቀርስ????????

 11. eshetu December 23, 2012 at 11:26 am Reply

  Dec 22 ላይ የጻፍሁት አስተያየት የት አለ? አጠፋችሁት እንዴ?

 12. eshetu December 23, 2012 at 1:13 pm Reply

  በመጀመሪያ ከላይ “Dec 22 ላይ የጻፍሁት አስተያየት የት አለ? አጠፋችሁት እንዴ?” በጻፍሁት ጽሁፍ በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ: ፕኦስት ያደረግሁት ሌላ ጽሁፍ ላይ ነውና ወደዚህ ገጽ አምጥቸዋለሁ ……………………………..

  ወንድሞች ሆይ ምን እያላችሁ ነው? የማህበሩ አመራር ምን ማድረግ አለበት? በ መጀመሪያ ማህበረ ቅዱሳን በዚህ የአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ‘Boycott’ ሊያደርገው የሚችል የመሳተፍ መብት አለው ? ማህበሩ አልሳተፍም ብሎ ቢቀመጥ እና ተቃውሞ ቢያሰማ ከሳሾቹ ያውሉ ያሳድሩት መሰላችሁ? ምእመኑን ያሳደመ ማህበረ ቅዱሳን ነው ድሮም ብለን ነበር የአክራሪዎች እና የ አሸባሪዎች ስብስብ ነውና አሁኑኑ መፍረስ አለበት ተብሎ እርምጃ እንደሚዎሰድበት ጠፍቷችሁ ነው? ቤተመንግስቱም ሆነ ኢህአዴግ በፕሮቴስታንቶች እጅ ወድቀዋልና ሰበብ ከተገኘ ለቤተክርስቲያናችን ጥንካሬ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ደጋፊ የሆኑ አካላት የሚጠረጉበት ሰበብ እንደሚፈለግ የሚጠፋችሁ አይመስለኝም:: ታዲያ ማህበሩ አቋሙን ከማሳዎቅ ውጭ በምን ስልጣኑ ነው የሚቃዎም? ቢቃዎምስ ይህ አጋጣሚስ ለከሳሾቹ ሰርግና ምላሽ እንደሚሆን ጠፍቷችሁ ነው? ሌላው ማህበሩ በአስመራጭ ኮሚቴ እና ሂደቱን ከመታዘብ የዘለለ ለመንግስት መረጃ አቀባይ እንደሆነ አስመስላችሁ ያቀረባችሁት መረጃ ምንጫችሁ ምን ይሆን? እንደ እነ አውደምህረት እንደነ አባሰላማ ለማህበሩ ስም ማጥፊያ የሚሆን ወንጀል እየፈበረካችሁ እንዳይሆን እሰጋለሁ:: እባካችሁ በ እርግጥ ለቤተክርስቲያኗ የምታስቡ ከሆነ ማህበሩበና አባላቱ ለቤተክርስቲያናችን እየሰጡት ላለው አገልግሎት እውቅና የምትሰጡ ከሆነ ለዚህ ጽሁፋችሁ ማስተባበያ ስጡበት:: በተረፈ የማህበሩ አመራሮ በጣም አስተዋይና አርቆ አሳቢ መሆናቸውን የሚያሳይ ውሳኔ መዎሰናቸውን ለመረዳት ሩቅ ሳንሄድ ያሳለፍናቸው ጥቂት አመታት በቂ ምስክሮች ናቸው::

  ወንድሜ ሐይለኢየሱስ በርግጥ ቤተክርስቲያንን ለማገልገል ቁርጠኝነቱ ካለህ ማህበረቅዱሳን አለ ብለህ መተው የሚገባህ አይመስለኝም ማህበሩም የዘጋብህ ቦታ ያለ አይመስለኝም:: ለአገልግሎተ ቤተክርስቲያን በርግጥ ቀናኢ ከሆንህ በሰንበት ት/ቤት ወይም በሰበካ ጉባዔ አለያም በጽዋ ማህበር ከዚህ ያለፈ ወኔ እና ቁርጠኝነት ካለህም እንደ እነ ‘ደጆችሽ አይዘጉ’ ማህበር የራስህን ማህበር መስርተህ ማገልገል ስትችል ማህበሩን ለመውቀስ መሞከርህ ተገቢ አይመስለኝም::

  በመጨረሻም አቡነ ሕዝቅኤል መግለጫ አላነብም ማለታቸው ትልቁንሥህተታቸውን የሚሸፍንላቸው አይመስለኝም:: 5ኛ ብለን 4ኛ አንልም በሚል ለራስ ያደላ ክብር ምክንያት በእርቁ ሂደት ላይ ቀዝቃዛ የቸለሱ እና እርሳቸው አቡነ መርቆርዮስን ከአገር እንዳባረሩዋቸው ሁሉ አገር ውስጥ ገብተው እንዲኖሩ ፈቅጀልዎታለሁ አይነት አቋም መያዛቸው ያሉበትን የክብር ቦታ የዘነጉ የሚያገለግሉትን እግዚያብሄርን እንዲሁም የሚመሯትን ቤተክርስቲያን የረሱ እና የመንግስት ባለስልጣን ያስመስላቸዋል::

 13. TachewN December 24, 2012 at 8:45 am Reply

  To all who have commented above…I hope we all agree that anybody’s comment is respected…and yours too. I have but a few questions to all of you…are you saying that the information is not true or you don’t care about that and you are saying whatever those few leaders who are always known for their ganging decide is right and should be accepted? Don’t you believe that this group of few is working with the government? Or are you saying that still is right and is the contemporary style of religiosity?

 14. eshetu December 24, 2012 at 4:49 pm Reply

  @TachewN እኔ እምለው ማህበረ ቅዱሳን ከመንግስት ጋር ወግኖ የተገኘበት መረጃ አልቀረበም አሉባልታ እንጂ! ከማህበሩ አመራር አንድ ለ አስመራጭ ኮሚቴነት እንደተመደበ ተዘግቧል ይህ የተመደበውም የአመራር አባል ከመሳተፍ ውጭ ሌላ ምርጫ የለውም ‘ አልሳተፍም ቢል መንገድህ የጨርቅ መንገድ ያድርግልህ ከማለትም በላይ ስብሃት ነጋ እንዳለው ማህበሩ ቤተክርስቲያኗን ከማገዝ ይልቅ እንቅፋት ይሆናል ተብሎ እንዲዘጋ ይደረጋል’:: ይህ ደግሞ ማንን እንደሚጠቅም ግልጽ ነው:: ሌላው የተጠቀሰው ደግሞ በታዛቢነት አንዲት ከፍተኛ አመራር መመደቧን ነው እንደሷው ሁሉ ከመንግስትም አንድ ከፍተኛ አመራር በታዛቢነት መመደቡ ተዘግቧል:: ታዲያ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች በታዛቢነት ቀረቡ ማለት ማህበረ ቅዱሳን ለ መንግስት መረጃ አቀባይ መደበ የሚል ይዘት ሊኖረው የምችል በምን ስሌት ነው? ይህ ዓይነት አመክንዮ ጤናማ አልመስልህ አለኝ:: አንተ የተረዳኸው ካለ ብትገልጽልኝ ደስ ይለኛል::

 15. fs December 24, 2012 at 6:56 pm Reply

  ወገኖቼ ይህን ሐሳብ ለማቅረብ ያነሳሳኝ በጽሑፉ ላይ የሰፈረው ቁም ነገር ሳይሆን በአብዛኛው አስታየት ሰጭዎች ላይ ያየሁት ያላገናዘበ ወይም ገደብ የሌለው የዋህነት ነው፡፡ እኔም ወደ ዋናው ማዕከል ጠጋ ብዬ በአንዳንድ መፍቀሬ ስልጣን ወፖለቲካ የአመራር አባላት የሚሰራውን ደባ ከማየቴ በፊት እንደእናንተ ለማኅበሩ አመራር አንገቴን አሳልፌ እሰጣለሁ ባይ ነበርኩ፡፡ ዛሬ ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ ከግል ፈቃዳቸው ይልቅ የቤተክርስቲያንን ህልውና፣ ከማኅበር ፍቅር ይልቅ የቤተክርስቲያን ፍቅር የሚበልጥባቸው እውነተኛ የማህበሩ አባላትን ከአድር ባዮቹ ለመለየት ችያለሁ፡፡ ዲ/ን አባይነን፣ ወ/ት ዳግማዊትን፣ አቶ ባይብልን ማነው አንድ ያደረጋቸው፡፡ በእርግጥ በአሜሪካን የአማርኛው ድምጽ የሰጠውን ቃለ መጠይቅም እንዳደመጣችሁት፣ በማኅበሩም ጠቅላላ ጉባኤ በግልጽ ሊያስረዳን እንደሞከረው ዲ/ን አባይነህ ሁልጊዜ የቤተክርስቲያን ሕልውና ከሁሉ ነገር በላይ የሚያስቀድም እውነተኛ የተዋህዶ አርበኛ ነው፡፡ ወ/ት ዳግማዊት ብዙዎችችን እንደምናውቃት ትሁት፣ ለማህበረ ቅዱሳን ራሷን አሳልፋ የሰጠች ከግቢ ጉባኤ ጀምሮ በአዲስ አባባ ማዕከልም በዋናው ማዕከልም በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገለች አሁንም እያገለገለች ያለች እህታችን ናት፡፡ ችግሩ ግን ዳግማዊት አፍቃሪ ማህበር ናት፡፡ እርሷ የሚያሳስባት የማህበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት መዘጋት አለመዘጋት እንጂ የቤተክርስቲያን ሕልውና አይደለም፡፡ ለእርሷ የማህበረ ቅዱሳን መሪዎች በተለይም ዋና ጽሐፊው እንደ ካቶሊካዊት ፓፓ ፍፁም የማይሳሳት ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ በእርሱ እና በአጋሮቹ የታዘዘችውን ከማድረግ ወደ ኋላ ማለት ቀርቶ ለምን ይህ እኮ ከክርስትን ሕይወቴ ጋር አይስማማም ብላ የማትጠይቅ መምለኬ ዲ/ን ሙሉጌታ ናት፡፡ አቶ ባይብልን መቼም ሁላችሁም እንደምታውቁት የታወቁ ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ እርሳቸው ወደ ማህበረ ቅዱሳን ጽ/ቤትም ሆነ ወደ ቤተክህነት የሚመጡት የፓለቲካ ሥራቸውን ለመፈጸም እንጂ ለክርስትና አይደለም፡፡ ስለዚህ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሁሉ በአንድ ማየት እና ለእነርሱ አንገቴን አሳልፌ እሰጣለሁ ማለት ያላዋቂ ሰማዕትነት ነው ፡፡ ስለዚህ በዚህ አጋጣሚ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ራሳችን፣ ውስጣችን ልንፈትሽ እንጂ የሚገባው በጥቅሉ ማህበረ ቅዱሳን አትንኩበን ማለቱ ለማህበሩም ሆነ ለቤተከርስቲያን አይጠቅም፡፡

  • anbesaw December 24, 2012 at 9:37 pm Reply

   Dear Fs, you are one of those Tehadisos who pretends to be MK and an insider…..but you have to know that this is an old style of confusing people. We all know that MK is doing all his best to serve the Church….as a human being they can make a mistake individually but when we come to this specific topic, they know what they are doing. And true Tewahidowiyan know the secrifice MK is paying for the development of the church. Tehadisowiyan like you always bark on a website and MK does the job with help of God. Respecting each in MK is a tradition that came from the teaching of the church is common and that does not mean worshiping each other as you wrote it.

   All Sunday Schools and true children of Church are working with MK. It is just a fact!!!!

 16. TachewN December 25, 2012 at 7:30 pm Reply

  Anbesaw…for God sake! please stop mixing things…MK has never worked for the sunday schools and one of the biggest mistakes in its strategy is ignoring them and that had ultimately become consequential. MK paid for that and it lost the battle. The problem however is it is full of either innocent people probably like you who may love the association too much and let it die of suffocation…a piece of advice my brother…if you love mk, try to challenge the leadership and ask them whom they are working for…this may not apply for all but does for the few gangers!!!

 17. haile December 29, 2012 at 12:07 pm Reply

  Mk is an association under EOTC holy synod. It si not an independent organization. As I can understand its task is to make the youth understand the correct interpretation of the bible and serve EOTC. Although it can have opinion difference in some issues , it can not be contrary to the Holy synod except praying for God. It shall not give a chance for the enemies of orthodoxy (tehadisos, protestant,) who are turning every stone including political power to show to the government it is a destabilizing factor.

 18. Be Mature January 2, 2013 at 12:33 pm Reply

  አንዳንድ ከጨቅላነት በላይ ርቀው ያልሄዱ ሰዎች የሚሰጡት አስተያየት እጅግ ይገርማል መድረኩን ሰላገኙ ብቻ መዘላበድ ክርስቲያንነት አይደለም እስከኪ በዚህ የጡመራ መድረክ ከቀረቡት ጽፈፎች የትኛው ይሆን ከእውነት የራቀ መረጃውን ይዞ ማጣራት ሲገባ በደፈናው ማቅራራት ያስገመግማችሁዋል ማኅበረቅዱሳን የማይሳሳት እንደ ካቶሊክ ፓፓ ነው ለማለት የቃጣችሁ ንስሐ ግቡ ተሐድሶነት ትምህርተ ቤተክርስቲያንን ማዛባት እንጂ ማቅን መተቸት አይደለም ማቅ ሃይማኖታቸን ነው የምትሉ እንደሆነ ተሐድሶዎች እናንተው ናችሁ ይልቁንስ በውስጣችሁ የተሞላውን የክፋት ካባ አውልቃችሁ ወደ መንፈሳዊነት ተመለሱ ስትሞገቱ ማምለጫችሁ ሰውነ ማጥላላት አይሁን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: