‹‹የጳጳሱ ቅሌት›› መጽሐፍ ጸሐፊ በ‹‹የጳጳሱ ስኬት›› ይቅርታ ጠየቀ

 • በ‹‹የጳጳሱ ቅሌት›› መጽሐፍ ‹‹ጸሐፌ ትእዛዝ ወይም አቀናባሪ ብቻ ነበርኹ›› ያለው ጸሐፊው ‹‹ተከሥተ ዘሪሁን››÷ በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤል ላይ የውሸትና የፈጠራ ታሪክ በማዘጋጀት ረገድ የአፅራረ ቤተ ክርስቲያንና የተሐድሶ መናፍቃን ተልእኮ አስፈጻሚ የኾኑት እነ እጅጋየሁ በየነ እና አሰግድ ሣህሉ ዋና አስተባባሪ እንደነበሩ ገልጧል፡፡
 • የመጽሐፉ ዓላማ ‹‹ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በምእመናንና በቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ያደናገጣቸውና በብፁዕነታቸው የአስተዳደር ብቃት ለሙስና መንገዱ ያልተመቻቸላቸው አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ከተሐድሶ መናፍቃን ጋራ በመኾን የብፁዕነታቸውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለማጥፋት የጣሩበት ነበር፡፡››
   

  ‹‹የጳጳሱ ስኬት››

  ‹‹የጳጳሱ ስኬት››

 • ‹‹ተከሥተ ዘሪሁን›› በሚል የብዕር ስም የሚታወቀው ግለሰብ ‹‹የጳጳሱ ስኬት›› በተሰኘው የአሁኑ መጽሐፉ ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒንም ‹ይቅርታ› ጠይቋል፡፡
 • ሐምሌ 4 ቀን 2002 ዓ.ም በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል የተመረቀው የአቡነ ጳውሎስ ‹‹ሐውልተ ስምዕ›› ሐሳብ አመንጪ ‹‹ተከሥተ ዘሪሁን›› እንደነበርና የተሠራበትም ገንዘብ ከቃሊቲ ደብረ ምጥማቅ ቁስቋም ማርያም ቤተ ክርስቲያን መወሰዱን ያስታወሱ ወገኖች በበኩላቸው÷ ጸሐፊው ይቅርታ የጠየቀው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ የደብሩ አስተዳዳሪ እንደኾነ በመግለጽ የይቅርታውን ቅንነት ይጠራጠራሉ – ግለሰቡ በነካ እጁ የሐውልቱን መቆም ሐሳብ በማመንጨትና በአቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት ዋዜማ ሥራውን በጽሑፍ በመደገፍ በእነ እጅጋየሁ በየነና ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ እንዲነበብ ስላደረሰው በደልም ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ይጠይቅ እንደኾነ ይጠብቃሉ፡፡
 • በመጽሐፉ ገጽ 7 ላይ የሚከተለው ቃል ሰፍሯል፡- ‹‹የጳጳሱ ስኬት መጽሐፍ ጸሐፊ ‹ተከሥተ ዘሪሁን› ነው፡፡ ተከሥተ ዘሪሁን ማለትም ትርጉሙ ዘሪሁን ተገለጸ፣ ታወቀ፣ ተረጋገጠ፣ ተደረሰበት፣ ንስሐ ገባ፣ ሊቀ ጳጳሱን አቡነ ሳሙኤልን ይቅርታ ጠየቀ ማለት ነው፡፡››
 • ‹ተከሥተ ዘሪሁ› ይቅርታ የጠየቀው አቡነ ሳሙኤልን ብቻ አይደለም፤ በ‹የጳጳሱ ቅሌት› መጽሐፍ አለስማቸውና አለግብራቸው ‹‹በፈጠራ በተቀናበረ ታሪክ›› ተጠቅሰዋል ያላቸውን ግለሰቦችንም ጭምር እንጂ፡፡
 • በ‹‹የጳጳሱ ስኬት›› መጽሐፍ የተደበላለቁ ስሜቶችና አስተያየቶች እየታዩ ነው፤ ከእኒህም የሚበዙት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን ከወቅቱ የፕትርክና ምርጫ ሂደት ጋራ በማያያዝ ‹‹ከፍለው እንዳጻፉት›› ሲናገሩ፣ መጽሐፉ ከአቡነ ጳውሎስ ኅልፈት በፊት መጻፍ እንደነበረበት የሚተቹት ደግሞ በስሙ የሚጠረጠረውን ግለሰብ በ‹‹ጥቅመኝነት›› የሚወነጅሉ ናቸው፡፡ እውነቱን ውለን አድረን እናየዋለን፡፡
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: