የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ቅ/ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴ ከመሠየም እንዲታገሥ ጠየቁ

  • አራተኛው ፓትርያሪክ ስለሚመለሱት ኹኔታ ምልአተ ጉባኤው እንዲመክር ጠይቀዋል
  • የልኡካኑ አብሮ መቀደስ በአንዳንድ አባቶች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞታል ተብሏል

ከኅዳር 26 – 30 ቀን 2005 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ በተካሄደው የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ የተሳተፈውና ከአራት ቀናት በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለስ የተገለጸው የቅዱስ ሲኖዶስ ልኡካን ቡድን አባላት÷ በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ላይ በመወያየት ላይ የሚገኘው ምልአተ ጉባኤ ሕጉን ከማጽደቅና አስመራጭ ኮሚቴ ከመሠየም እንዲታገሥ መጠየቁ ተሰማ፡፡ የልኡካን ቡድኑ ከዕርቀ ሰላሙ ንግግር በኋላ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ከሊቀ ጳጳሱ አቡነ ፋኑኤል ጋራ ለተፈጠሩት አስተዳደራዊ ችግሮች መፍትሔ ለማበጀትና ሊቀ ጳጳሱ በሀ/ስብከቱ ጸሐፊ ላይ ያስተላለፉትን ውግዘት እንዲያነሡ በመሥራት ላይ መኾኑ ተዘግቧል፡፡

ብፁዕ አቡነ ገሪማና አቡነ አትናቴዎስ

ብፁዕ አቡነ ገሪማና አቡነ አትናቴዎስ

ብፁዕ አቡነ ገሪማን (በሰብሳቢነት)፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስንና ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን በልኡካን ቡድኑ አባልነትና ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን በጸሐፊነት የያዘው የልኡካን ቡድኑ÷ ለቅዱስ ሲኖዶሱ በጻፈውና በስብሰባው ላይ በንባብ በተሰማው ባለሁለት ገጽ ደብዳቤው÷ አራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አገራቸው ስለሚመለሱበት ኹኔታ በስደት በሚገኙት አባቶች የተሰጡትን ምክንያቶች መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ምልአተ ጉባኤው የሚያካሂደው ምክክር አስፈላጊ መኾኑን አመልክቷል፡፡

ደብዳቤው አያይዞም÷ የዕርቀ ሰላሙ ቀጣይ ንግግር ከጥር 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም በካሊፎርኒያ – ሎሳንጀለስ እንደሚካሄድ መወሰኑን፣ ሂደቱ ከመልካም ፍጻሜ እንዲደርስ ሁሉም ወገን ለሰላሙ መሰናክል የኾኑ ማናቸውንም ሥራዎች ከመሥራት ትዕግሥት እንዲያደርግ ስምምነት ላይ መደረሱን ለዚህም መፈረማቸውን፣ የሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላት ወደ ሁለቱም ወገኖች ተጉዞ የማግባባት ሥራ እንዲሠራ የሚጠበቅ መኾኑን በማስታወስ፣ ምልአተ ጉባኤው እኒህን የሚያደናቅፉ ውሳኔዎች ከማሳለፍ እንዲታገሥ ተማፅኗል፡፡

በደብዳቤው ላይ ከምልአተ ጉባኤው አባላት የተለያዩ ሐሳቦች ተደምጠዋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ ሦስት አባላት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንደመኾናቸው በምልአተ ጉባኤው ስብሰባ ላይ ተገኝተው በሕጉ ረቂቅ ይኹን በአስመራጭ ኮሚቴው አባላት አደረጃጀት ላይ ሐሳብ የመስጠት መብታቸው እንዲጠበቅ የተናገሩ ብፁዓን አባቶች÷ የዕርቅና ሰላም ቀን እንደማይመሽ በማጠየቅ የልኡካኑን ደብዳቤ ሐሳብ ደግፈዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የልኡካን ቡድኑ አባላት በውግዘት ከተለያዩ አባቶች ጋራ አብረው ስለመቀደሳቸውና ስለመጸለያቸው (በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል) ትኩረት በመስጠት፣ የመጨረሻ ነው በተባለ የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ ‹‹ቀን ቀጥረው ለመምጣትም ሥልጣኑ አልነበራቸውም›› በሚል የልኡካን ቡድኑን በአቋም ለመቃወም መዘጋጀታቸው ተገልጧል፡፡

 

አቡነ ቀውስጦስ

አቡነ ቀውስጦስ

የቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብሳቢዎች ከኾኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል 32 አባቶች ብቻ በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የምልአተ ጉባኤው ስብሰባ÷ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ 16 ያህል ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አለመሳተፋቸው ታውቋል፡፡ ከሕመም ጋራ በተያያዘ በስብሰባው ለመሳተፍ አልቻሉም የተባሉትን ብፁዓን አባቶች ትተን በተለይም በሀገር ውስጥ እያሉ በምልአተ ጉባኤው ላይ ያልተገኙት አባቶች (እንደ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ)÷ ዕርቀ ሰላሙን ከማስቀደም አንጻር ባላቸው አቋም ከስብሰባው መታጎላቸው ‹‹ከምርጫው ይልቅ ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ወገኖችንትኩረት ስቧል፡፡

 

ለዕርቀ ሰላሙ ብዙዎች ያሳደሩት ተስፋ ለምልሞ ከመልካም ፍጻሜ የሚደርስ ከኾነ ለሳምንት ያህል የተደከመበት የምርጫ ሕግ ማጽደቅና የአስመራጭ ኮሚቴ ማቋቋም ድካምና ውሳኔን ጥቅም አልባ እንደሚያደርገው ተገምቷል፡፡ ‹‹ከምርጫው ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም›› የሚሉ ወገኖች አራተኛው ፓትርያሪክ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ በሚለው አቋም ላይ ጥንቃቄ በማድረግ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሕይወት እስካሉ ድረስ መንበሩ በዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ወይም በእንደራሴ እንዲመራ ይሟገታሉ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: