በጳጳሳት የሚመራ የኮፕት ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል

  • የልኡካን ቡድኑ ቆይታ በኮፕት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሰፊ ሽፋን ይሰጠዋል
  • የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የራስዋ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዲኖራት እገዛ ያደርጋል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊና

ልማታዊ አገልግሎት ‹‹አብረው ለመሥራት ያስችላቸዋል፤ ለዚህም ኹኔታዎችን ያመቻቻል›› የተባለ የጋራ የሥልጠና መርሐ ግብር ሊያካሂዱ ነው፡፡ በምስጢራተ ቤተ ክርስቲያንና በመንፈሳዊ አገልግሎት ላይ እንደሚያተኩር የተነገረውን ይህን የጋራ የሥልጠና መርሐ ግብር ያስተባበረው የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ነው፡፡ ሥልጠናውን የሚሰጡት ኻያ ያህል የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልኡካን ሲኾኑ ቡድኑ ከብፁዓን ጳጳሳት ጀምሮ ካህናትን፣ መዘምራንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን እንደሚያካትት የኮሚሽኑ ምንጮች ለሐራ ዘተዋሕዶ ገልጸዋል፡፡

ታዋቂው የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ

ታዋቂው የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ

ከታኅሣሥ 11 – 15 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሚካሄደው የመጀመሪያ ዙር የጋራ ሥልጠና መርሐ ግብር÷ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎችና ካህናት፤ ከሰባክያነ ወንጌል፤ ከመንፈሳዊ ኮሌጆች መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ደቀ መዛሙርትና የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር፤ ከሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ከማኅበረ ቅዱሳን የተውጣጡ 270 ያህል ልኡካን በቋሚነት ይሳተፋሉ፡፡ ሥልጠናው በሚቆይባቸው አምስት ተከታታይ ቀናት ከእኒሁ አካላት ከእያንዳንዳቸው የተውጣጡ አንድ ሺሕ፣ አንድ ሺሕ (በአጠቃላይ ከ5000 በላይ) ተወካዮች ሥልጠናውን በቋሚነት ከሚሳተፉ 270 ሠልጣኞች ጋራ በተጠቀሱበት ቅደም ተከተል መሠረት በተለዋጭነት እንደሚሳተፉ ተገልጧል፡

በግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብዙኀን መገናኛዎች (በተለይም በቴሌቪዥን ጣቢያዎቻቸው) ሰፊ ሽፋን እንደሚሰጠው ለተነገረው የጋራ ሥልጠና መርሐ ግብር ከማኅበረ ቅዱሳን እና ከነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር ጋራ በተቀናጀ አኳኋን የተቋቋመው ኮሚቴ ሲያደርግ የቆየው ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ እንደኾነ ተዘግቧል፡፡

ሁለቱ አብያተ ክርስቲያን ለረጅም ከዘለቀው ግንኙነታቸው (ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን) አንጻር÷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከውጭ አገር የሚተላለፍ የራስዋ የቴሌቪዥን ቻናል እንዲኖራት የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እንደምትሻና ለዚህም ተጠናቅቆ በቀረበው ምክረ ሐሳብ መሠረት ፋይናንሳዊ ድጋፍ እንደምትሰጥ ተመልክቷል፡፡ የአሁኑ የጋራ ሥልጠና መርሐ ግብር በዚህ ረገድ ምቹ ኹኔታዎችን እንደሚፈጥር ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

His Grace Ab Samuel

ብጹእ አቡነ ሳሙኤል የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ

ይኸው የመጀመሪያ ዙር የጋራ ሥልጠናና ልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር አጠቃላይ ወጪ በኮሚሽኑ የሚሸፈን ሲኾን በቀጣይ ዙር የጋራ ሥልጠናና ልምድ ልውውጥ መርሐ ግብር ደግሞ በተመሳሳይ ደረጃ የተዋቀረ ልኡክ ወደ ግብጽ እንደሚያመራ የኮሚሽኑ ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በሕክምና ሞያ ላይ ያተኰረ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የበጎ ፈቃድ ልኡካን ቡድን በቅርቡ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከፍተኛ የጤና አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል፡፡

Advertisements

One thought on “በጳጳሳት የሚመራ የኮፕት ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል

  1. andadirgen December 14, 2012 at 6:28 am Reply

    ባሉ በርቱ ሰዎች ቀጥታ የናተን ገጽ ለመጎብኝት እስኪችሉ ድረስ በአንድ አድርገን በኩል ጽሁፋሁን እናስተዋውቅላችኋለን .. እስከ መጨረሻው ለመዝለቅ እንጂ ለማቋረጥ አትስሩ….

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: