የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በፕሬዝዳንቱ ተጻፈ የተባለውን ደብዳቤ አያውቁትም

  • ቡድኑ ለሁለቱ ሲኖዶሶች ደብዳቤ ይጽፋል
  • ኢንጅነር አራጋው ጥሩነህ የቡድኑ አባል አይደሉም
  • ፕሬዝዳንቱ በግል የጻፉት ደብዳቤ በደብዳቤ ይሻራል
  • ‹‹የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አለ፤ [አራተኛው ፓትርያሪክ] እንደ አንድ ተወዳዳሪ መቅረብ ይችላሉ›› /አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ/
  • ‹‹ዕርቀ ሰላሙ ሲኖዶሱ ለሚያካሂደው የፓትርያሪክ ምርጫ እጅግ አጋዥ ነው›› /የአገር ሽማግሌዎች ቡድን/ 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ለአራተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና ለዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ‹በግል› እንደጻፏቸው የተገለጹትና ‹‹ስሕተት ኾኖ በመገኘቱ ተፈጻሚ እንደማይኾንና እንዲመለስ›› ስለተባሉት ደብዳቤዎች በብዙኀን መገናኛ መዘገ

/አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ/

/አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ/

ቡን ተከትሎ ከአገር ሽማግሌዎች ቡድን፣ ከመንበረ ፓትርያሪኩ እና ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋራ ቆይታ ካደረጉት የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ የተለያዩ አስተያየቶች እና ስጋቶች እየተደመጡ ነው፡፡

ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምንና ሻለቃ ኀይሌ ገብረ ሥላሴን ጨምሮ ስድስት አባላት የሚገኙበት የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በደብዳቤው ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ከፕሬዝዳንቱ ጋራ ውይይት ተደርጓል ስለመባሉ እንደማያውቁ፣ በደብዳቤው ላይ ስማቸው የተጠቀሱት ኢንጅነር አራጋው ጥሩነህ የቡድኑ አባል እንዳልኾኑ፣ ከእርሳቸው ጋራም የአርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንትና የአገር ሽማግሌዎች ቡድን አባል የኾኑት ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ አባተ በግላቸው እንጂ የቡድኑ ውክልና እንደሌላቸው ለመንግሥት አካላትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ማብራሪያ በመስጠት ተጠምደው መዋላቸው ተዘግቧል፡፡ ቡድኑ ጉዳዩን በተመለከተ ለብዙኀን መገናኛ መግለጫ እንደሚሰጥም ተጠቁሞ የነበረ ቢኾንም ቆይቶ ደግሞ መግለጫው ተሰርዞ ለሁለቱም ሲኖዶሶች ደብዳቤ እንደሚጽፉ ተነግሯል፡፡

የአገር ሽማግሌዎች ቡድኑ መስከረም 26 ቀን 2005 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዕርቀ ሰላሙን አስመልክቶ በጻፈውና ለሐራ ዘተዋሕዶ በደረሰው ደብዳቤው የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስንና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በማስታወስ÷ ችግሩ እልባት ሳያገኝ እየተጓተተ በመቆየቱ የቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም ሳይመለስና ሳይረጋገጥ አባቶች አረፍተ ዘመን እየገታቸው በመሄዱ የችግሩ አሳሳቢነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ያመለክታል፡፡ ቡድኑ በዚሁ ደብዳቤው ዕርቀ ሰላሙ ሲኖዶሱ ለሚያካሂደው የፓትርያሪክ ምርጫ እጅግ አጋዥና በውጭ ያሉትንም አባቶች አሳታፊ ቢያደርግ ጠቀሜታው የጎላ እንደኾነ ገልጾ ለተፈጠረው መከፋፈል ‹‹የቅዱሳን ፓትርያሪኮች የሚመረጡበት ሕግ ያለመውጣቱ መኾኑን›› በብዙ ምሁራንና ምእመናን እንደ መንሥኤ እንደሚጠቀስ አውስቷል፡፡ በዝግጅት ሂደት ላይ የሚገኘው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ትኩረት ቢሰጠው ‹‹ዕርቁን ፍጹም እንደሚያደርገውና ወደፊትም ተመሳሳይ ስሕተት እንዳይከሠት ዋስትና ሊኾን እንደሚችልም›› ያለውን እምነት ገልጧል፡፡

የመንበረ ፓትርያሪኩ ምንጮች በበኩላቸው ደብዳቤው በአንድ በኩል በመንግሥት ኾነ ተብሎ የተዘጋጀና በዳላስ ቴክሳስ የዕርቀ ሰላም ጉባኤ በማካሄድ ላይ በሚገኙት ተነጋጋሪዎች መካከል አለመግባባት (ውጥረት) በመፍጠር ለማሰናከል የታቀደ እንደኾነ ተደርጎ መወሰዱንና ከእርሱም ጋራ ተያይዞ በቀጣዩ ፓትርያሪክ ምርጫ ሂደት ፍላጎቱን ለመጫን ያለውን ውጥን እንደሚያጋልጥ ይናገራሉ፡፡ ሌላው የምንጮቹ አስተያየት በደብዳቤው ስማቸው የተጠቀሱት ኢንጅነር አራጋው ጥሩነህ ከአምስተኛው ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጀምሮ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ አገር ቤት በማምጣት ዕርቅ ለማውረድ ሲወድቁ ሲነሡ የነበሩ መኾናቸውን በማስታወስ÷ የአቡነ ጳውሎስን ኅልፈት ተከትሎ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበር ለመመለስ ‹‹በአካባቢ ተወላጅነት ተሰባስበዋል›› ከተባሉ ግለሰቦች ጋራ ያደረጉትን ቡድናዊ ማግባባት የሚነቅፍ ነው፡፡

ዛሬ ማምሻውን ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋራ ቆይታ ያደረጉት የፕሬዝዳንት ግርማ ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ ፕሬዝዳንቱ ‹‹በግለሰቦች ሐሳብ ላይ በመመሥረት በግላቸው ጻፉት›› ለተባለው ደብዳቤ በቃል የሰጡት ማስተባበያ ወደ ጽሑፍ ተቀይሮ ደብዳቤው በሌላ ደብዳቤ እንደሚሻር አስታውቀዋል፡፡ የፕሬዝዳንቱ ‹ትክክለኛ ሐሳብ ነበር› በማለት አማካሪው የገለጹት ነጥብም ቀደም ሲል ‹‹የዕርቀ ሰላሙን ሂደት በመላ ከማደናቀፍና በምርጫው ሂደት ፍላጎቱን ከመጫን›› አንጻር የተገለጸውን ስጋት እንደሚያጠናክር የጉዳዩ ተከታታዮች ያስረዳሉ፡፡ አቶ አሰፋ ፕሬዝዳንቱ ለማለት የፈለጉትን ሲገልጹ፡- ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ የራሷ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አላት፤ በዚያ መሠረት አራተኛው ፓትርያሪክ እንደ አንድ ተወዳዳሪ ኾነው መቅረብ ይችላሉ፤ ወደ አገር ተመልሰው በምርጫው መሳተፍ የሚችሉበትን ኹኔታ ለማመቻቸት እንጂ መንበር ላይ ይቀመጡ ለማለት አይቻልም፤ መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባምና፡፡›› 

በብዙዎች አስተያየት መንግሥት ‹‹በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት›› የሚለውን የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ እንዳሻው እንደሚጠቀምበት ይህ የአቶ አስፋ ንግግር በቂ ማሳያ ኾኖ እየተወሰደ ነው፡፡Picture 006Picture 007

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: