በዝዋይ ገዳም ላይ የተነዛው የግብረ ሰዶማዊነት አሉባልታ ለፓትርያሪክነት የሚካሄደው ሽኩቻ የወለደው የጎጠኛ ቡድኖች ክስ መኾኑ ተጠቆመ

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ የኾኑ ግለሰቦች እንደሚያዘጋጁት የሚታወቀው አንድ ብሎግ÷ በብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ላይ የነዛው የግብረ ሰዶማዊነት አሉባልታ÷ በብፁዕነታቸው የበላይ ጠባቂነት የሚመራውን የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ይዞታ ለመንጠቅ የሚሞክሩ ቡድኖች የፈጠሩትና ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ የራሳቸውን ዕጩ ያዘጋጁ ጎጠኛ ቡድኖች የሚያስተጋቡት ክስ መኾኑ ተገለጸ፡፡

ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ የሀገረ ስብከቱ ምንጮች እንደሚያስረዱት፣ በገዳሙና ገዳሙ የሚገኝበት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኾኑት ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ላይ የግብረ ሰዶማዊነት አሉባልታው መናፈስ የጀመረው÷ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈት ማግሥት አንሥቶ ነው፡፡ የአሉባልታው አናፋሾች ሁለት መኾናቸውን የሚናገሩት የመረጃው ምንጮች ዋነኞቹ በገዳሙ ደቡባዊ አቅጣጫ በሚገኘው የቦጩሳ ቅዱስ ሚካኤል አጥ

ቢያ የሚኖሩና ከቀድሞው የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ካልዕ ጀምሮ በስልታዊ መንገድ ገዳሙን በማዳከም ይዞታውን የመንጠቅ ዓላማ ያላቸው ‹‹ጥቅመኛ ግለሰቦች ናቸው፤›› ይላሉ፡፡ የእኒህን ግለሰቦች ክስ ኾነ ብለው የሚያናፍሱት ደግሞ ‹‹የኦሮሞ ፓትርያሪክ እናሾማለን›› በሚል በየሆቴሉ እየተሰበሰቡ የሚዶልቱት ሙሰኛ እና ጥቅመኛ ቡድኖች መኾናቸውን ምንጮቹ ይናገራሉ፡፡

ሁለቱም አካላት በተለያዩ መንሥኤዎች የገዳሙንና የብፁዕነታቸውን ስም ለማጥፋት ይሞክሩ እንጂ በአንድ ጎራ ያሰለፋቸው ስጋት ተመሳሳይ እንደኾነ ምንጮቹ ጨምረው ያስረዳሉ፡፡ ይህም ስጋት ብፁዕነታቸው በቀድሞው ፓትርያሪክ እንደ እንደራሴም እንደ ተተኪም መታጨታቸውና ለዚህም ዓላማ ፓትርያሪኩ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋራ እንዳስተዋወቋቸው የሚነገርላቸው ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ለመኾን በመንግሥት ታጭተዋል በሚል የመነገሩ ወሬ ነው፡፡ ከፓትርያሪክ ምርጫው ጋራ ተያይዞ በብፁዕነታቸው ላይ የሚናፈሰው ሁሉ መሠረተ ቢስ እንደኾነ

ተናግረዋል የተባሉት ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ በበኩላቸው÷ ፕትርክናው እንደ ጵጵስናው ሁሉ በሰው ሠራሽ አካሄድ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ እና ም

ርጫ የሚከናወን በመኾኑ ለአሉባልታው ቦታ እንደማይሰጡት ተመልክቷል፡፡

በአዲስ መልክ የተሠራውን

ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ጥር 19 ቀን 2005 ዓ.ም የሚያስመርቀውንና መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቱ እየተጠናከረ የመጣውን የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተለያዩ አጋጣሚዎች በማዳከም ይዞታውን ለመንጠቅ የሚዳክሩት ግለሰቦች የቀድሞው ፓትርያሪክ ዜና ዕረፍት በተሰማበት ሰሞን ብፁዕነታቸው ወደ ገዳሙ እንዳይገቡ ዐመፅ እስከ ማነሣሣት ደርሰው እንደነበር ተነግሯል፡፡ ይኸው ዐመፅ የተመራው በአሁኑ ወቅት የመቂ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ /ሊቀ ካህን/ ኾኖ በመሥራት ላይ በሚገኘው መልአከ ምሕረት ጌታሁን ሞርኪ በተባለ ግለሰብ እንደኾነ የሚያወሱት ምንጮቹ÷ ‹‹ከፓትርያሪኩ ሞት በኋላ የብፁዕነታቸው ተሰሚነት ተዳክሟል›› በሚል ግለሰቡ ጥቂት የአካባቢውን ነዋሪዎች በማሳሳት ለማነሣሣት የሞከረው ረብሻ በዝዋይ መድኃኔዓለም፣ ኪዳነ ምሕረት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ቅዱስ ፋኑኤል እንዲሁም በመቂ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ትብብር መገታቱን ገልጸዋል፡፡

በምግባር ከዘቀጠበት የአመንዝረኝነትና የጥንቆላ ነውር የተነሣ ክህነቱ በሊቀ ጳጳሱ የተያዘበትና አመኔታ የነፈገችው የሕግ ሚስቱ ሳትቀር በምንጣፍ እንደለየችው የሚነገርበት መልአከ ምሕረት ጌታሁን ሞርኪ÷ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ማኅበረሰብን ‹‹ስደተኞች ናችሁ፤ ክልላችንን ለቃችኹ ውጡ፤›› በሚል ጎጠኛ ቅስቀሳውና ማስፈራሪያው የሚታወቅ እንደኾነ ምንጮቹ ይመሰክራሉ፡፡ ውለታ ቢሱ ጌታሁን ሞርኪ የገዳሙን ርስት ለመረከብ በጠላትነት ይነሣሣ እንጂ የማይገባውን ሥልጣን አግኝቶ ኑሮውን እንዲገፋ የረዳው ግን የገዳሙ ማኅበረሰብ እንደነበር ወዳጆቹ ይናገራሉ፡፡

ይህ ነው የሚባል የቤተ ክርስቲያን ይኹን ዘመናዊ ትምህርት የሌለው ጌታሁን ሞርኪ÷ ተወልዶ ባደገበት የቦጩሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ሲያገለግል ትዳር ይዞ ልጆች በመውለዱ ሊቀ ጳጳሱ ኑሮውን የሚደጉምበት የተሻለ ሥራ እንዲሰጡት ያደረጉት በዝዋይ ገዳም የሚያገልግሉ አብሮ አደጎቹ ነበሩ፡፡ ጌታሁን ሞርኪ በአብሮ አደጎቹ ልመና የተሰጠው ሥራ ማዕርገ ቅስና ከተቀበለ በኋላ በእልቅና የተሾመበት የደብረ ዘይት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪነት ነበር፡፡ ነገር ግን÷ ሥራ ከሠራተኛው በማይገናኝበት፣ ለመንፈሳዊነትና ሞያዊ ብቃት ዋጋ በማይሰጥበት ቤተ ክህነታችን የማይገባውን ሥልጣን ተቀብሎ የደብር አስተዳዳሪ የኾነው ጌታሁን ሞርኪ÷ ‹‹በጣቱ ላይ በደነቀረው የብር ቀለበት ዐውቅላች

Getahun Moki1

ጌታሁን ሞርኪ

ኋለኹ›› እያለ በርካታ ምእመናንን ባሳሳተበትና ‹‹ንስሐ ገብቻለኹ፤ ቀኖና ተቀብዬአለኹ›› ካለ በኋላ አሁንም አልታረመበትም በሚባለው የጥንቆላ ተግባሩ የተነሣ ከአስተዳዳሪነት ሥልጣኑ ይታገዳል፡፡

የእገዳ ርምጃ የተወሰደበት ጌታሁን ሞርኪ ከቤተ ክርስቲያን መባረሩ ለዓመታት ያሸመቀበትን ዓላማ ለማሳካት የማያስችለው በመኾኑ ‹‹ንስሐ ገብቻለኹ፤ ቀኖና ተቀብዬአለኹ›› በማለት የተለመደ ምልጃውን ይልካል፡፡ ተጠያቂነት እና ሓላፊነት በማይታወቅበት ቤተ ክህነታችንም ጎጠኝነትን የጥቅመኝነት ሽፋኑ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው እና ጠንቋዩ ጌታሁን ሞርኪ የመቂ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ኾኖ ይሾማል፡፡ በገዳሙ ላይ ያለው ጠላትነት ግን በተወሰደበት ርምጃ እየተጠናከረ በመምጣቱ ቀደም ሲል በሥነ ምግባር ችግር ከገዳሙ የተባረረውና አሁን በኢየሩሳሌም የሚገኘው ገብረ ኪዳን የተባለ ‹‹አባ›› ነኝ ባይ እንደሚሰጠው በሚነገረው ምክርና ድጋፍ የተንኰል ድሩን ማድራት ይጀምራል፡፡ ይኸው የተንኰል ድር ተፈጽሟል ከተባለው የግብረ ሰዶም ጥቃት ጋራ የተያያዘ መኾኑን ምንጮቹ ያስረዳሉ፡፡

የጥቃቱ ፈጻሚ መልካሙ ሞርኪ የሚባል ሲሆን የጌታሁን ሞርኪ ታናሽ ወንድም እንደ ኾነ ተነግሯል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመበት ደግሞ በገዳሙ ያደገውና ጌታሁን ሞርኪ ለዓላማው አሳስቶ ከመለመላቸው ወጣቶች አንዱ የነበረው ዲያቆን ማኅደረ ሥላሴ እንዳለ የተባለ ወጣት ነው፡፡ ዲያቆን ማኅደረ ሥላሴ ጥቃቱ በመልካሙ ሞርኪ የተፈጸመበት በመሸተኛው ታላቅ ወንድሙ ጌታሁን ሞርኪ የመጠጥ ግብዣ ራሱን መቆጣጠር እንዲሳነው ከተደረገ በኋላ መኾኑን ጉዳዩን ለማጣራት በቀረበለ

Dn. Mahdere

ማኅደረ ሥላሴ እንዳለ

ትና በፈቃደኝነት ምላሽ በሰጠበት ይፋዊ ቃለ ምልልስ ማረጋገጡን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ይኸው የግብረ ሰዶም ጥቃት በመረጃ ደረጃ የደረሳቸው ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ሁለቱንም ወጣቶች አቅርበው በመጠየቅ የተባለውን ጉዳይ ያረጋግጣሉ፡፡ አስፈላጊውን ተግሣጽ፣ ማስጠንቀቂያና ቀኖና ከሰጡ በኋላም እንዲራራቁ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም መሠረት ከጥቃቱ በኋላ ከገዳሙ እንዲወጣ የተወሰነበት ማኅደረ ሥላሴ ወደ ናዝሬት መድኃኔዓለም፣ የግብረ ሰዶም ሱሰኛው መልካሙ ሞርኪ ደግሞ በጥያቄው መሠረት ከአገር (አገሩን ለመጥቀስ አልተፈለገም) ይወጣል፡፡ ከቤት ያልታረቀ አመል ከቤት ወጥቶ በውጭም ይከተላልና በሰዶማዊ ፍትወት የነደደው መልካሙ ሞርኪ ማኅደረ ሥላሴ ወዳለበት አገር እንዲላክለት በጌታሁን ሞርኪ በኩል ሊቀ ጳጳሱን በተለያዩ ማግባቢያዎች መወትወቱን ይቀጥላል፡፡

ምንጮቹ እንደሚናገሩት ብፁዕነታቸው በዚህ የጌታሁን ሞርኪ ምክር አልተስማሙም፡፡ ውጤቱ ግን ከ1973 ዓ.ም ጀምሮ በገዳሙ መጋቢነትና አስተዳዳሪነት በታማኝነት በማገልገል፣ በኋላም በድንግልናዊ ምንኵስናቸውና በምናኔያዊ ሕይወታቸው ንጽሕ ጠብቀው ለከፍተኛ ማዕርግ ለበቁበት ክብር ‹‹ሰይጣን እንኳ የማያማቸው›› የሚባሉት ብፁዕነታቸው፣ ‹‹በጥብቅ ባወገዙትና በፈጻሚዎቹም ላይ ጥብቅ ርምጃ በወሰዱበት ግብረ ሰዶማዊነት መከሰስ ኾነ፤›› ይላሉ፡፡ አጋጣሚው ስለ ስድስተኛው ፓትርያሪክ ማንነት የተለያዩ ወሬዎች የሚናፈሱበት መኾኑና ብፁዕነታቸውን ከመንበረ ፕትርክናው ተሻሚዎች ጋራ በመደመር ገና ለገና ‹ፓትርያሪክ ከኾኑ› የሚለው ቅዠት እነ ጌታሁን ሞርኪ ለተለያየ ዓላማም ቢሆን ወቅቱ ከፈጠረላቸው አጋሮቻቸው ጋራ በአንድ ጎራ እንዳቆራኛቸው ነው ምንጮቹ የሚያምኑት፡፡

በዚህ ያልተገታው ጌታሁን ሞርኪ አመቺ ነው ብሎ ባሰበው አጋጣሚ ሁሉ ገዳሙን በውስጥ ተባባሪዎቹና በውጭ አጋሮቹ ከማዳከም አልቦዘነም፡፡ ቀደም ሲል እንደተጠቆመው ከቀድሞው ፓትርያሪክ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ ‹‹የብፁዕነታቸው ተሰሚነት ተዳክሟል›› በሚል በጀመረው የጥፋት ተግባር በመቀጠል በነሐሴ ወር 2004 ዓ.ም ገዳሙ ላይ ለሚፈጽመው የጥፋት ተግባር አሳስቶ በመለመለው ዲያቆን ማኅደረ ሥላሴ አማካይነት ገዳሙ ከሐይቁ ውኃ እየሳበ አትክልት የሚያለማበት የውኃ ሞተር እንዲሰረቅ አድርጓል፡፡ ይህንንም የአዳሚ ቱሉ ወረዳ ፍ/ቤት በፋይል ቁጥር 18296 በቀን 21/12/2004 ዓ.ም የተከሳሽ ማኅደረ ሥላሴን ስድስት የሰው መከላከያ ምስክሮች ያዳመጠበት መዝገብ፣ በዚሁ መዝገብ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያሳለፈበትና ውሳኔው ተፈጻሚ እንዲኾን ትእዛዝ የሰጠበት ሰነድ ያረጋግጣል /ሰነዱን ይመልከቱ/፡፡

Advertisements

One thought on “በዝዋይ ገዳም ላይ የተነዛው የግብረ ሰዶማዊነት አሉባልታ ለፓትርያሪክነት የሚካሄደው ሽኩቻ የወለደው የጎጠኛ ቡድኖች ክስ መኾኑ ተጠቆመ

  1. Anonymous January 11, 2013 at 12:39 pm Reply

    አንገት የሚያስደፋ ነዉረኛ ወሬ ነዉ በእዉነቱ በኦረቶዶክስነቴ ያፈርኩበት ። ሀለት ጥያቄች አሉኝ
    1 መላከ ምህረት የክህነት ስም ይምስለኛል ለዚህ ሰዉ ስልጣኑን የሰጠዉ ማን ነዉ? ምክንያቱም ምንም አይነት የክህነት ትምህርት እንደሌለዉ ተጠቅሷል
    2.ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ መሰረት ወንጀል መሆኑ እየታወቀ ወነንጀለኛዉ ወንጀል መስራቱ ከታወቀ በሰአቱ ለህግ ተላልፎ ለምን አልተሰጠም ?ከሀገርስ እንዲወጣ ለምን ድጋፍ ተደረገ ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: